በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክፍል 11 ማስተዋወቂያ

የክፍል 11 ማስተዋወቂያ

ይህ ክፍል ከክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ጋር ያስተዋውቀናል። ኢየሱስ በአንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ ይኖር በነበረ ድሃ ቤተሰብ ውስጥ ተወለደ። ኢየሱስ አናጺ ከሆነው አባቱ ጋር ይሠራ ነበር። የሰውን ዘር የሚያድነው እሱ ነው። ይሖዋ ኢየሱስን የአምላክ መንግሥት ንጉሥ እንዲሆን መርጦታል። ወላጅ ከሆንክ፣ ይሖዋ ኢየሱስ የሚወለድበትን ቤተሰብ በጥንቃቄ የመረጠው እንዴት እንደሆነ ልጅህ እንዲያስተውል እርዳው፤ ይህን ያደረገው ኢየሱስ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድግ አስቦ ነው። ከዚህም ሌላ ሄሮድስ ኢየሱስን እንዳይገድለው ይሖዋ የጠበቀው እንዴት እንደሆነና የይሖዋን ዓላማ ሊያከሽፍ የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ አስረዳው። ይሖዋ ለኢየሱስ መንገድ እንዲጠርግለት ዮሐንስን ልኮታል። ኢየሱስ ከትንሽነቱ ጀምሮ ጥበብ የተንጸባረቀባቸውን የይሖዋን መመሪያዎች እንደሚወድ ያሳየው እንዴት እንደሆነም ጎላ አድርገህ ግለጽ።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ትምህርት 68

ኤልሳቤጥ ልጅ ወለደች

የኤልሳቤጥ ባል ልጁ እስከሚወለድ ድረስ መናገር እንደማይችል የተነገረው ለምንድን ነው?

ትምህርት 69

ገብርኤል ማርያምን አነጋገራት

ሕይወቷን የሚለውጥ አንድ መልእክት ነገራት።

ትምህርት 70

መላእክት ኢየሱስ መወለዱን ተናገሩ

የኢየሱስን መወለድ የሰሙት እረኞች ፈጣን እርምጃ ወሰዱ።

ትምህርት 71

ይሖዋ ኢየሱስን ጠበቀው

አንድ ክፉ ንጉሥ ኢየሱስ እንዲገደል ፈለገ።

ትምህርት 72

ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ

ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ የነበሩትን አስተማሪዎች ያስደነቃቸው እንዴት ነው?

ትምህርት 73

ዮሐንስ ለመሲሑ መንገድ አዘጋጀ

ዮሐንስ ካደገ በኋላ ነቢይ ሆነ። ዮሐንስ መሲሑ እንደሚመጣ ያስተምር ነበር። ሕዝቡ ዮሐንስ ያስተማረውን ትምህርት ሲሰሙ ምን አደረጉ?