የክፍል 5 ማስተዋወቂያ
እስራኤላውያን ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሲና ተራራ ደረሱ። በዚያም ይሖዋ ልዩ ሕዝቡ እንዲሆኑ ከእስራኤላውያን ጋር ቃል ኪዳን ገባ። እስራኤላውያንን ጠብቋቸዋል፤ እንዲሁም የሚያስፈልጋቸውን ነገር በሙሉ አሟልቶላቸዋል፤ የሚበሉት መና፣ የማያረጅ ልብስ እንዲሁም ምንም ሳይፈሩ ተረጋግተው የሚኖሩበት ቦታ ሰጥቷቸዋል። ወላጅ ከሆንክ፣ ልጅህ ይሖዋ ለእስራኤላውያን ሕጉን፣ የማደሪያ ድንኳኑን እንዲሁም የክህነት ሥርዓቱን የሰጣቸው ለምን እንደሆነ እንዲገነዘብ እርዳው። ቃልን መጠበቅ፣ ትሑት መሆን እንዲሁም ምንጊዜም ለይሖዋ ታማኝ መሆን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ።