የክፍል 8 ማስተዋወቂያ
ይሖዋ ሰለሞንን ታላቅ ጥበብ በመስጠት ባረከው፤ ቤተ መቅደሱን የመገንባት መብትም ሰጠው። ሰለሞን ግን ከጊዜ በኋላ ይሖዋን ተወ። ወላጅ ከሆንክ፣ የሐሰት አምልኮ ተከታዮች ሰለሞንን ከአምላክ እንዲርቅ ያደረጉት እንዴት እንደሆነ ለልጅህ አስረዳው። ከሰለሞን የግዛት ዘመን በኋላ የእስራኤል መንግሥት ተከፈለ፤ ከዚያ በኋላ የተነሱት መጥፎ ነገሥታት ሕዝቡ ከሃዲ እንዲሆንና ጣዖት እንዲያመልክ አደረጉት። በዚህ ወቅት በርካታ የይሖዋ ታማኝ ነቢያት ስደት ደርሶባቸዋል፤ እንዲሁም ተገድለዋል። ንግሥት ኤልዛቤል ደግሞ በሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ውስጥ ክህደት ይበልጥ እንዲስፋፋ አደረገች። ይህ ዘመን በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ብዙ መጥፎ ነገሮች የተፈጸሙበት ወቅት ነው። ሆኖም በዚህ ጊዜም ቢሆን በእስራኤላውያን መካከል እንደ ንጉሥ ኢዮሳፍጥና ነቢዩ ኤልያስ ያሉ ይሖዋን በታማኝነት የሚያገለግሉ ሰዎች ነበሩ።