በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሐሰተኛ ነቢያት

ሐሰተኛ ነቢያት

ፍቺ:- ከእውነተኛው አምላክ ያልተገኙና ከተገለጸው ፈቃዱ ጋር የማይስማሙ መልእክቶችን የሚናገሩና መልእክቶቹም ከሰው የበለጠ ኃይል ካለው ምንጭ የመጡ ናቸው ብለው የሚያውጁ ግለሰቦችና ድርጅቶች ናቸው።

እውነተኛ ነቢያትና ሐሰተኛ ነቢያት እንዴት ተለይተው ሊታወቁ ይችላሉ?

እውነተኛ ነቢያት በኢየሱስ እንደሚያምኑ ያሳውቃሉ፤ ይሁን እንጂ የምንሰብከው በኢየሱስ ስም ነው ብሎ መናገር አይበቃም

1 ዮሐ. 4:1–3:- “ወዳጆች ሆይ፣ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና። የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።”

ማቴ. 7:21–23:- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፣ ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች:- ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን . . . ? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም:- ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፣ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።”

እውነተኛ ነቢያት በአምላክ ስም ይናገራሉሆኖም አምላክን እንወክለዋለን ብሎ መናገር ብቻ አይበቃም

ዘዳ. 18:18–20:- “ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ [እንደ ሙሴ] ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፣ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፤ በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ። ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን በስሜ በድፍረት የሚናገር ወይም በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ፣ እርሱ ይገደል።” (ከ⁠ኤርምያስ 14:14፤ 28:11, 15 ጋር አወዳድር።)

ኢየሱስ እንዲህ አለ:- “አባቴ እንዳስተማረኝ እነዚህን [እናገራለሁ] እንጂ ከራሴ አንዳች [አላደርግም።]” (ዮሐ. 8:28) ደግሞም “እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ” ብሏል። (ዮሐ. 5:43) በተጨማሪም “ከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል” ብሏል።—ዮሐ. 7:18

ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች አምላክን እንወክላለን እያሉ በአምላክ የግል ስም ባይጠቀሙና በአንዳንድ እምነት ነክ ጉዳዮች ላይ የአምላክን ሳይሆን የራሳቸውን አስተያየት መግለጽን ልማዳቸው ቢያደርጉ እነዚህ የእውነተኛ ነቢይን ብቃቶች ያሟላሉን?

ታላላቅ ምልክቶች” ወይም ተአምራትን” የማድረግ ችሎታ የግድ የእውነተኛ ነቢይነት ማረጋገጫ አይደለም

ማቴ. 24:24:- “ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፣ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና [“ተአምራትንና” የ1980 ትርጉም፣ ቱኢቨ ] ድንቅ ያሳያሉ።”

2 ተሰ. 2:9, 10 የ1980 ትርጉም:- “የዓመፅ ሰው የሚመጣው በሰይጣን ኀይል አሳሳች ተአምራትንና ምልክቶችን፣ አስደናቂ ነገሮችንም በማድረግ ነው፤ እንዲሁም በሚጠፉት ሰዎች ላይ ልዩ ልዩ ክፉ ማታለል በማድረግ ነው፤ እነዚህ ሰዎች የሚጠፉትም ለመዳን የሚያበቃቸውን እውነት ስላልወደዱ ነው።”

በሌላ በኩል ሙሴ የይሖዋን መመሪያ በመከተል ተአምራት አድርጓል። (ዘጸ. 4:1–9) ይሖዋ ለኢየሱስ ተአምራት የማድረግ ኃይል ሰጥቶታል። (ሥራ 2:22) ይሁን እንጂ ከአምላክ የተላኩ መሆናቸውን ያረጋገጡላቸው ያደረጉአቸው ተአምራት ብቻ አልነበሩም።

 እውነተኛ ነቢያት የተነበዩት ሁሉ መፈጸሙ አይቀርም። ነገር ግን መቼና እንዴት እንደሚፈጸም ላያውቁ ይችላሉ

ዳን. 12:9:- “ዳንኤል ሆይ፣ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ።”

1 ጴጥ. 1:10, 11 አዓት:- “ነቢያት . . . ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር በእነርሱ የነበረ መንፈስ አስቀድሞ ሲመሰክር በምን ወራትና በምን ዓይነት ወቅት እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።”

1 ቆሮ. 13:9, 10:- “ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፣ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።”

ምሳሌ 4:18:- “የጻድቃን መንገድ . . . እንደ ንጋት ብርሃን ነው፣ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።”

ሐዋርያትና ሌሎች የጥንት ክርስቲያን ደቀ መዛሙርት ይሆናሉ ብለው በስህተት የጠበቋቸው ነገሮች ነበሩ። ይሁን እንጂ በዚህ ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ “ከሐሰተኛ ነቢያት” ጋር አልመደባቸውም።—ሉቃስ 19:11፤ ዮሐንስ 21:22, 23፤ ሥራ 1:6, 7⁠ን ተመልከት።

ዳዊት ለይሖዋ የአምልኮ ቤት ለመሥራት በነበረው ሐሳብ እንዲገፋበት ነቢዩ ናታን አበረታትቶት ነበር። በኋላ ግን ይሖዋ ለነቢዩ ናታን ቤቱን የሚሠራው ዳዊት እንዳልሆነ እንዲያስታውቀው ነግሮታል። ነቢዩ ናታን አስቀድሞ የተናገረው ባለመፈጸሙ ምክንያት ይሖዋ ከነቢይነት አልሻረውም። እንዲያውም ነቢዩ ይሖዋ የገለጸለትን በትሕትና ተቀብሎ በመስተካከሉ የበለጠ ተጠቅሞበታል።—1 ዜና 17:1–4, 15

እውነተኛ ነቢይ የሚናገራቸው ነገሮች ለእውነተኛው አምልኮ መጠናከር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፣ እንዲሁም ለሰው ከተገለጠው የአምላክ ፈቃድ ጋር ይስማማሉ

ዘዳ. 13:1–4:- “በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፣ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ፣ እንደ ነገረህም ምልክቱ ወይም ተአምራቱ ቢፈጸም፣ እርሱም:- ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ቢልህ፣ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉ፣ እርሱንም ፍሩ፣ ትእዛዙንም ጠብቁ፣ ቃሉንም ስሙ፣ እርሱንም አምልኩ፣ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።”

መጽሐፍ ቅዱስ “የዓለም ወዳጅ” የሆነ ሁሉ የአምላክ ጠላት ነው ስለሚል ተከታዮቻቸው በዓለም ጉዳዮች ጣልቃ እንዲገቡ የሚገፋፉ ቀሳውስት የእውነተኛውን አምልኮ ዓላማ እያራመዱ ነውን? (ያዕ. 4:4፤ 1 ዮሐ. 2:15–17) እውነተኛው አምላክ አሕዛብ “እኔ ይሖዋ እንደሆንሁ ማወቅ ይኖርባቸዋል” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስም ‘ለስሙ የሚሆንን ሕዝብ’ ከብሔራት መካከል ይወስዳል ይላል። ነገር ግን በአምላክ የግል ስም የመጠቀምን አስፈላጊነት አቃልለው የሚመለከቱ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ለሰው ከተገለጠው ከአምላክ ፈቃድ ጋር ተስማምተው እየሠሩ ናቸውን? (ሕዝ. 38:23 አዓት፤ ሥራ 15:14) ኢየሱስ ለተከታዮቹ የአምላክ መንግሥት እንድትመጣ እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስም ሥጋ በለበሰ ሰው መታመን ተገቢ እንዳልሆነ አስጠንቅቋል። ታዲያ በሰው አገዛዝ ላይ እምነት እንዲጥሉ ሰዎችን የሚገፋፉ ቀሳውስት ወይም የፖለቲካ ድርጅቶች እውነተኛ ነቢያት ናቸውን?—ማቴ. 6:9, 10፤ መዝ. 146:3–6አዓት፤ ከ⁠ራእይ 16:13, 14 ጋር አወዳድር።

 እውነተኛ ነቢያትና ሐሰተኛ ነቢያት በኑሯቸው በሚያሳዩት ፍሬና ተከታዮቻቸው በሚከተሉት አኗኗር ተለይተው ሊታወቁ ይችላሉ

ማቴ. 7:15–20:- “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። . . . መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፣ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። . . . ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።”

አኗኗራቸው ምን ዓይነት ባሕርይ ይንጸባረቅበታል? “የሥጋ ሥራም . . . ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ ጣዖትን ማምለክ፣ ምዋርት፣ ጥል፣ ክርክር፣ ቅንዓት፣ ቁጣ፣ አድመኛነት፣ መለያየት፣ መናፍቅነት፣ ምቀኝነት፣ መግደል፣ ስካር፣ ዘፋኝነት [“ፈንጠዝያ” አዓት ]፣ ይህንም የሚመስል ነው። . . . እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። የ[አምላክ]መንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።”—ገላ. 5:19–23፤ በተጨማሪ 2 ጴጥሮስ 2:1–3⁠ን ተመልከት።

የይሖዋ ምሥክሮች ስህተት የሆኑ ነገሮችን አስተምረው ያውቁ የለምን?

የይሖዋ ምሥክሮች መንፈስ የገለጠልንን አዲስ ነገር የምንናገር ነቢያት ነን አይሉም። የተሳሳቱባቸው ጊዜያት አሉ። እነርሱም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ወደፊት ይሆናሉ ብለው በስህተት የጠበቋቸው ነገሮች ነበሩ።—ሉቃስ 19:11፤ ሥራ 1:6

በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ክርስቶስ ስለሚገኝበት ጊዜ የተገለጹ ነገሮች አሉ። የይሖዋ ምሥክሮችም እነዚህን መግለጫዎች በከፍተኛ ፍላጎት አጥንተዋል። (ሉቃስ 21:24፤ ዳን. 4:10–17) ኢየሱስ ስለ ጊዜው ከተነገሩት ትንቢቶች ጋር ተጣምሮ የሰይጣንን ክፉ ሥርዓት ፍጻሜ የሚያየውን ትውልድ ለመለየት የሚያስችል ብዙ ገጽታ ያለው ምልክት ሰጥቷል። (ሉቃስ 21:7–36) የይሖዋ ምሥክሮች ይህ ምልክት እየተፈጸመ እንዳለ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች አቅርበዋል። የይሖዋ ምሥክሮች በአንዳንድ ዘመናት ፍጻሜ ላይ ስለሚፈጸሙ ነገሮች በነበራቸው ግንዛቤ ረገድ ተሳስተው እንደነበረ አይካድም። ይሁን እንጂ እምነትን የማጣት ወይም የይሖዋ ዓላማዎች የሚፈጸሙበትን ጊዜ ነቅቶ ያለመጠበቅ ስህተት አልፈጸሙም። “ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ” በማለት ኢየሱስ የሰጠውን ምክር ሁልጊዜ ያስታውሳሉ።—ማቴ. 24:42

ከተረዷቸውና ለሕዝብ ካስታወቋቸው በጣም አስፈላጊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ጋር ሲወዳደሩ የአመለካከት ለውጥና እርማት ለማድረግ የተገደዱባቸው ጉዳዮች በጣም ጥቂት ናቸው። በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ:- እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ብቻ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክ አንድያ ልጅ ነው እንጂ አንድነት በሦስትነት ያለው አምላክ ሦስተኛ ክፍል አይደለም። ከኃጢአት ነፃ መውጣት የሚቻለው በክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት በማመን ብቻ ነው። መንፈስ ቅዱስ አንቀሳቃሽ የይሖዋ ኃይል ነው እንጂ የተወሰነ አካል አይደለም። የዚህም መንፈስ ፍሬ በእውነተኛ አምላኪዎች አኗኗር ውስጥ በግልጽ መታየት አለበት። የሰው ነፍስ የጥንት አረማውያን ያምኑ እንደነበረው ዘላለማዊት ሳትሆን ሟች ነች። ወደ ሕይወት የመመለስ ተስፋም በትንሣኤ ላይ ብቻ የተመካ ነው። አምላክ ክፋት እስከ አሁን ድረስ እንዲኖር የፈቀደው በአምላክ ጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነት ላይ በተነሣው ክርክር ምክንያት ነው። የሰው ልጆች ተስፋ የአምላክ መንግሥት ብቻ ናት። ከ1914 ጀምሮ የምንኖረው በዓለም አቀፉ ክፉ ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች ውስጥ ነው። በሰማይ ከክርስቶስ ጋር ነገሥታትና ካህናት የሚሆኑት 144,000 ታማኝ ክርስቲያኖች ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ታዛዥ የሰው ልጆች ግን ገነት በምትሆነው ምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ያገኛሉ።

የይሖዋ ምሥክሮች የሚያስተምሯቸውን ትምህርቶች በተመለከተ ሌላው ግምት ውስጥ ሊገባ የሚገባው ጉዳይ የሚከተለው ነው:- ሰዎች ጥሩ ሥነ ምግባር እንዲይዙ ረድተዋልን? እነዚህን ትምህርቶች ተቀብለው በሥራ የሚያውሉት ሰዎች በአካባቢያቸው በሚገኙት ማኅበረሰቦች ዘንድ በሐቀኝነታቸው የታወቁ ናቸውን? እነዚህን ትምህርቶች ተግባራዊ በማድረግ የቤተሰብ ኑሯቸው ተሻሽሏልን? ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ በመካከላቸው ባለው ፍቅር በቀላሉ ተለይተው እንደሚታወቁ ተናግሯል። (ዮሐ. 13:35) ይህ መለያ ጠባይ በይሖዋ ምሥክሮች ዘንድ ጐልቶ ይታያልን? መልሱን ሐቁ ይናገር ብለን ትተናል።

አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

‘የይሖዋ ምሥክሮች ሐሰተኛ ነቢያት ናቸው ብለው ቄሶች ነግረውናል’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘አንድ ጥያቄ ብጠይቅዎትስ? በምን እንደምናምን ወይም ምን እንደምንሠራና በዚህም ምክንያት ሐሰተኛ ነቢያት መሆናችንን የሚያሳይ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሳይተዋችኋል? . . . መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛ ነቢያትን እንዴት አድርጎ እንደሚገልጻቸው ባሳይዎትስ? (በገጽ  133–136 ከተገለጹት ነጥቦች በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ ተጠቀም።)’

ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘እንደዚህ የመሰለው ከባድ ክስ ግልጽ በሆነ መረጃ መደገፍ አለበት ቢባል እንደሚስማሙ እርግጠኛ ነኝ። ቄሶቹ እንደ ምሳሌ አድርገው የጠቀሱላችሁ ግልጽ የሆነ ነገር አለ? (የቤቱ ባለቤት ይፈጸማሉ ተብለው ሳይፈጸሙ ቀርተዋል የሚባሉ “ትንበያዎችን” የሚጠቅሱ ከሆነ በገጽ  135ና ከገጽ  136 መጀመሪያ እስከ ገጽ 137 መጨረሻ በቀረበው ሐሳብ ተጠቀም።)’

ሌላ አማራጭ:- ‘አንድ ሰው እንደዚህ የመሰለ ክስ በእርስዎ ላይ ቢያቀርብ ቢያንስ አቋምዎን ወይም አመለካከትዎን ለመግለጽ አጋጣሚ ቢሰጥዎት በጣም ደስ እንደሚልዎት እርግጠኛ ነኝ፤ አይደለም እንዴ? . . . እንግዲያውስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ነገር ባሳይዎትስ . . . ?’