በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መስተዳድር

መስተዳድር

ፍቺ:- ሕግ አውጪና አስፈጻሚ የሆነ አካል ነው። የመስተዳድሮች ዓይነት የሚከፋፈለው ብዙውን ጊዜ የሥልጣናቸውን መጠንና ሥልጣናቸውን ያገኙበትን ምንጭ መሠረት በማድረግ ነው። ይሖዋ አምላክ የጽንፈ ዓለም ሉዓላዊ ገዥ ሲሆን እንደፈቃዱና እንደ ዓላማው ለሌሎች ሥልጣን ይሰጣል። ይሁን እንጂ የይሖዋ ሉዓላዊነት ቀንደኛ ተቀናቃኝ የሆነው ሰይጣን ዲያብሎስ “የዚህ ዓለም ገዥ” ነው። ይህም ለተወሰነ ጊዜ ሲሆን የሆነውም አምላክ ስለፈቀደ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የዓለምን ፖለቲካዊ የአገዛዝ ሥርዓት በአውሬ በመመሰል እንዲህ ይላል:- “ዘንዶውም [ሰይጣን ዲያብሎስ] ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን [ለአውሬው] ሰጠው።”—ዮሐ. 14:30፤ ራእይ 13:2፤ 1 ዮሐ. 5:19

ሰዎች ዘላለማዊ ደስታ የሚያመጣ መስተዳድር ለማቋቋም ይችላሉን?

የሰው ልጆች የታሪክ መዝገብ ምን ያሳያል?

መክ. 8:9 አዓት:- “ሰው ሰውን የገዛው ለጉዳቱ ነው።” (አንዳንድ መንግሥታትና ገዥዎች ጥሩ ዓላማ ይዘው ቢነሡም ሰውን መጉዳታቸው የማይቀር ሐቅ ሆኗል።)

“ከዚህ በፊት የተነሡት ሥልጣኔዎች በሙሉ በመጨረሻ ተንኮታኩተው ወድቀዋል። ታሪክ ሳይሳካላቸው የቀሩ ጥረቶች ወይም እውን ሳይሆኑ የቀሩ ምኞቶች ትረካ ነው። . . . ስለዚህ አንድ ሰው ልክ እንደ ታሪክ ተመራማሪ አሳዛኝ ነገሮች መፈጸማቸው እንደማይቀር እየጠበቀ መኖር ይኖርበታል።”—ሄንሪ ኪስንጀር፣ የፖለቲካ ሳይንቲስትና የሥነመንግሥት ፕሮፌሰር፤ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ በተባለው መጽሔት ላይ የተጠቀሰ፣ ጥቅምት 13, 1974፣ ገጽ 30ቢ

ሰዎች በመስተዳድር ረገድ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያደናቅፈው ምንድን ነው?

ኤር. 10:23:- “አቤቱ፣ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፣ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም።” (አምላክ ሰብዓዊ ፍጡሮቹ ከእርሱ ርቀው የራሳቸውን መንገድ በራሳቸው እንዲቀይሱ ሥልጣን አልሰጣቸውም።)

ዘፍ. 8:21:- “የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና።” (ገዥዎች ብቻ ሳይሆኑ ተገዥዎችም ጭምር የሚወለዱት ከኃጢአትና ከራስ ወዳድነት ዝንባሌ ጋር ነው።)

2 ጢሞ. 3:1–4:- “በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፣ ገንዘብን የሚወዱ፣ . . . ዕርቅን የማይሰሙ፣ . . . በትዕቢት የተነፉ፣ . . . ይሆናሉ።” (ዛሬ የሰውን ልጅ ያጋጠሙት ችግሮች በአንድ አገር ጥረት ብቻ የዘለቄታ መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉ አይደሉም። ዓለም በሙሉ መተባበር ይኖርበታል። ይህ ዓይነቱ ትብብር እንዳይኖር ግን የራስ ወዳድነትና የስስት ፍላጎት አደናቅፎታል። ይህ የራስ ወዳድነትና የስስት ፍላጎት በየአገሩ በሚገኙት ድርጅቶች መካከል እውነተኛ ትብብር እንዳይፈጠር ክፉ መሰናክል ሆኗል።)

መጽሐፍ ቅዱስ ከሰው በላይ የሆኑ ኃይላት የሰው ልጆችን ጉዳዮች እንደሚቆጣጠሩ ይገልጻል። “ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።” (1 ዮሐ. 5:19) “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ . . . ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” (ኤፌ. 6:12) “የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፣ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።”—ራእይ 16:14

ሰዎች ከመንግሥት ባለ ሥልጣኖች ምግባረ ብልሹነትና ጭቆና ሊላቀቁ የሚችሉት እንዴት ነው?

ሥልጣን ላይ ያሉትን መለወጥ ችግሩን ይፈታዋልን?

ነፃ ምርጫ በሚደረግባቸው አገሮች ሥልጣን ላይ የሚወጡ ሰዎች ከጥቂት ዓመታት በኋላ በምርጫ ተሸንፈው ከሥልጣናቸው ይወርዱ የለም? ይህ ለምን ሆነ? ይህ የሚሆነው አብዛኞቹ ሰዎች ባለሥልጣኖቹ በሠሩት ሥራ ስላልረኩ ነው።

መዝ. 146:3, 4 አዓት:- “ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ። መንፈሱ ይወጣል፣ ወደ መሬቱም ይመለሳል፤ በዚያ ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።” (ስለዚህ አንዳንድ መሪዎች የጀመሯቸውን የማሻሻያ ፕሮግራሞች ሳይጨርሱ ወዲያው ሌሎች ስለሚረከቧቸው ዳር ሳያደርሷቸው ይቀራሉ።)

መሪው ማንም ይሁን ማን በሰይጣን ቁጥጥር ሥር የሚገኘው የዚህ ዓለም ክፍል ነው።—1 ዮሐ. 5:19

መፍትሔው አብዮታዊ ዓመፅ ነውን?

ብልሹ መሪዎች ከሥልጣን ቢወርዱና ፍትሐዊ ያልሆኑትም ሕጐች ቢሻሩ የአዲሱ መስተዳድር ባለሥልጣኖች የሚውጣጡት ፍጽምና ከጐደላቸው ሰዎች ከመሆኑም በላይ አሁንም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚናገረው በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ካለው የፖለቲካ ሥርዓት ሊወጡ አይችሉም።

ማቴ. 26:52:- “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።” (ኢየሱስ ይህን ቃል ከደቀ መዛሙርቱ ለአንዱ የተናገረው የመንግሥት ሥልጣን በራሱ በአምላክ ልጅ ላይ ፍትሐዊ ያልሆነ ነገር ይፈጽም በነበረበት ጊዜ ነበር። መዋጋት ተገቢ ነገር ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ ሊዋጉለት የሚገባ ትክክለኛ ምክንያት ሊኖር አይችልም ነበር።)

ምሳሌ 24:21, 22:- “ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፣ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ። መከራቸው ድንገት ይነሣልና፤ ከሁለቱ የሚመጣውን ጥፋት ማን ያውቃል?”

ታዲያ ለምግባረ ብልሹነትና ለጭቆና መፍትሔው ምንድን ነው?

ዳን. 2:44:- “በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት [መስተዳድር] ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፣ ለዘላለምም ትቆማለች።”

መዝ. 72:12–14:- “[ይሖዋ የሾመው ንጉሥ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ] ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፣ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና። ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፣ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል። ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል፤ ስማቸው [“ደማቸው” አዓት ] በፊቱ ክቡር ነው።” (በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እንደነዚህ ላሉት ሰዎች ያሳየው አሳቢነት፣ በተአምር መፈወሱ፣ ብዙ ሕዝቦችን መመገቡና ሕይወቱን እንኳን ለእነዚህ ሰዎች ሲል አሳልፎ መስጠቱ ትንቢት የተነገረለት ገዥ እርሱ መሆኑን በትክክል አረጋግጧል።)

በተጨማሪም በገጽ 228–232 ላይ “መንግሥት” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት ስለሚመጣው መስተዳድር ምን እንደሚል ከልብ መመርመር የሚገባን ለምንድን ነው?

ሰብዓዊ ገዥዎች የሰው ልጅ በአስቸኳይ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማቅረብ አልቻሉም

ከዚህ በታች የተገለጹት ነገሮች በየትም ቦታ ለሚኖሩ ሰዎች የሚያስፈልጉ ነገሮች ሲሆኑ ሰብዓዊ መንግሥታት ግን ሊሰጧቸው አልቻሉም። አምላክ ግን እነዚህን ነገሮች እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። እስቲ መርምራቸው:- (1) ከጦርነት ሥጋት ነፃ በሆነ ዓለም ውስጥ መኖር።—ኢሳ. 2:4፤ መዝ. 46:9, 10 (2) ሁሉ ሰው የሚበቃውን ያህል ምግብ ያገኛል።—መዝ. 72:16 አዓት (3) ሁሉም ሰው ምቾት ያለው ቤት ይኖረዋል።—ኢሳ. 65:21 (4) ሁሉም ሰዎች ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው የሚያስፈልጋቸውን ሠርተው የሚያቀርቡበት አስደሳች ሥራ ይኖራቸዋል።—ኢሳ. 65:22 (5) የሕመምና የበሽታ ጥላ የማያጨልመው ሕይወት።—ራእይ 21:3, 4 (6) ፍትሕ፤ ከሃይማኖት፣ ከዘር፣ ከኢኮኖሚና ከብሔር ጥላቻ ነፃ መሆን።—ኢሳ. 9:7፣ 11:3–5 (7) በሕይወትና በንብረት ላይ አደጋ የሚፈጥሩ ወንጀለኞች ሳይኖሩ ያለሥጋት በደስታ መኖር።—ሚክ. 4:4፤ ምሳሌ 2:22 (8) ፍቅር፣ ደግነት፣ ለሌላ ሰው አሳቢ መሆንና እውነተኝነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥበት ዓለም።—መዝ. 85:10, 11፤ ገላ. 5:22, 23

የፖለቲካ መሪዎች በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ለሕዝባቸው የተሻለ ሁኔታ እንደሚያመጡ ተስፋ ሲሰጡ ቆይተዋል። ውጤቱስ ምን ሆነ? በብዙ አገሮች የሚገኙ ሕዝቦች ብዙ ሀብት ቢኖራቸውም ከበፊቱ የበለጠ ደስታ የላቸውም። የሚያጋጥሟቸው ችግሮችም ከጥንቶቹ ችግሮቻቸው የበለጠ ውስብስቦች ሆነውባቸዋል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ትክክልና አስተማማኝ መሆናቸው ተረጋግጧል

የአምላክ ቃል አንድ መቶ ዓመት ያህል ቀደም ብሎ ባቢሎን በዓለም ላይ ገዢ እንደምትሆን፣ በመጨረሻም ኃይሏ እንዴት እንደሚሰባበር፣ ከጠፋች በኋላ መናገሻ ከተማዋ ዳግመኛ የሰው መኖሪያ እንደማይሆን ትንቢት ተናግሮ ነበር። (ኢሳ. 13:17–22) መጽሐፍ ቅዱስ ቂሮስ ከመወለዱ ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ስሙንና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ውስጥ የሚኖረውን ድርሻ በመጥቀስ ትንቢት ተናግሯል። (ኢሳ. 44:28፤ 45:1, 2) ሜዶ ፋርስ የዓለም ኃያል መንግሥት ከመሆኗ በፊት እንዴት ወደ ዓለም ኃያልነት ደረጃ እንደምትደርስ፣ የሁለት አገሮች ጥምር መንግሥት እንደምትሆንና እንዴት እንደምትወድቅ ሳይቀር ትንቢት ተነግሮ ነበር። የግሪክ መንግሥት የዓለም ኃያል መንግሥት ከመሆኑ ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት በመጀመሪያው ንጉሥ አማካይነት ከምን ደረጃ ላይ እንደሚደርስና በኋላም ግዛቱ ለአራት እንደሚከፈል ትንቢት ተነግሮ ነበር።—ዳን. 8:1–8, 20–22

መጽሐፍ ቅዱስ የጊዜያችንን የዓለም ሁኔታ በዝርዝር በቅድሚያ ገልጿል። በተጨማሪም ሁሉም ሰብዓዊ መንግሥታት በአምላክ እጅ እንደሚጠፉና የአምላክ መንግሥት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰው ልጆችን እንደምትገዛ ያስጠነቅቀናል።—ዳን. 2:44፤ 7:13, 14

ይህን የመሰለ አስተማማኝ መረጃ የሚገኝበትን የምክር ምንጭ ልብ ብሎ ማዳመጥ የጥበብ መንገድ አይደለምን?

ለሰው ልጅ ችግሮች እውነተኛ መፍትሔ የምታስገኘው የአምላክ መንግሥት ብቻ ናት

ችግሮቹን ለማስወገድ ከሰው በላይ የሆነ ኃይል፣ ችሎታና ልዩ ባሕርያት ያስፈልጋሉ። አምላክ የሰው ልጆችን ከዲያብሎስና ከአጋንንቱ ተጽዕኖ ማላቀቅ ይችላል። እንደሚያላቅቅም ተስፋ ሰጥቷል። ማንም ሰው ይህን ለማድረግ አይችልም። አምላክ ኃጢአትን በማስወገድ ሞትንና በሽታን ለማጥፋትና ሰዎች ሊሆኑ የሚፈልጉትን እንዲሆኑ ለማስቻል የሚያስፈልገውን ዝግጅት አድርጓል። የሕክምና ሳይንስ በጭራሽ ይህንን ሊፈጽም አይችልም። ፈጣሪ ብዙ ምርት እንዳይመረት የሚከለክለውን ችግር ለመፍታትና አደገኛ የሆኑ ብክለቶችን ለማቆም የሚያስችል (ስለ ምድርና በላይዋ ላይ ስላለው ሕይወት ሁሉ) እውቀት አለው። የሰው ልጅ የሚያደርጋቸው ጥረቶች ግን አብዛኛውን ጊዜ ተጨማሪ ችግሮችን ያስከትላሉ። የአምላክ ቃል የሰዎችን ሕይወት እየለወጠ ነው። ስለዚህም ቃሉ እንዲመራቸው የሚፈቅዱ ሰዎች ደግ፣ ከፍተኛ ሥነ ምግባር ያላቸው፣ ሌላውን ሰው የሚወዱ ሆነዋል። ከሁሉም ብሔሮች፣ ዘሮችና ቋንቋዎች የተውጣጡ ቢሆኑም በሌሎች ሰዎች ላይ መሣሪያ የማያነሡ፣ እውነተኛ ሰላም አግኝተው አንድ ኅብረተሰብ በመሆን በወንድማማችነት የሚኖሩ ሰዎች ሆነዋል።

የአምላክ መንግሥት የአሁኑን ዓለም ሥርዓት የምታስወግደው መቼ ነው? የዘመናት ስሌት” እና “የመጨረሻ ቀኖች” የሚሉትን ዋና ዋና ርዕሶች ተመልከት።