በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መናገር

መናገር

ፍቺ:- የክርስቲያን ጉባኤ እንደተቋቋመ አካባቢ አንዳንድ ደቀ መዛሙርት ከራሳቸው ቋንቋ በተለየ ቋንቋ እንዲሰብኩ ወይም አምላክን እንዲያወድሱ ያስቻላቸው ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ልዩ ችሎታ ነው።

የአምላክ መንፈስ የሚኖራቸው ሁሉ ‘በልሳናት እንደሚናገሩ’ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻልን?

1 ቆሮ. 12:13, 30:- “ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። . . . ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን?” (በተጨማሪ 1 ቆሮንቶስ 14:26)

1 ቆሮ. 14:5:- “ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፣ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጉም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።”

አንድ ሰው ከዚህ በፊት በፍጹም ባልተማረው ቋንቋ በታላቅ ስሜት መናገሩ መንፈስ ቅዱስ እንዳለው ያረጋግጣልን?

‘በልሳናት የመናገር’ ችሎታ ከእውነተኛው አምላክ ውጪ ከሆነ ምንጭ ሊመጣ ይችላልን?

1 ዮሐ. 4:1:- “ወዳጆች ሆይ፣ መንፈስን ሁሉ [ኪጄ፣ ሪስ ] አትመኑ፣ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ።” (በተጨማሪም ማቴዎስ 7:21–23፤ 2 ቆሮንቶስ 11:14, 15)

በዛሬው ጊዜ ‘በልሳናት ከሚናገሩ’ ሃይማኖታውያን መካከል ጴንጠቆስጤዎችና ባፕቲስቶች፣ የሮማ ካቶሊኮች፣ ኤጲስቆጶሳውያን፣ ሜቶዲስ ቶች፣ ሉተራኖችና ፕሪስቢቴሪያኖች ይገኛሉ። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ ‘ደቀ መዛሙርቱን ወደ እውነት ሁሉ’ እንደሚመራቸው ተናግሯል። (ዮሐ. 16:13) የእነዚህ የእያንዳንዱ ሃይማኖት አባላት ‘በልሳናት እንናገራለን’ የሚሉት የሌሎች ሃይማኖት አባላት ‘ወደ እውነት ሁሉ’ የተመሩ መሆናቸውን ያምናሉን? ሁሉም እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ከሆኑ ይህ ሊሆን ይችላልን? ‘በልሳናት እንዲናገሩ’ ያስቻላቸው ምን ዓይነት መንፈስ ነው?

የፋውንቴን ትረስትና የእንግሊዝ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ባወጡት የጋራ መግለጫ “በጥንቆላና በአጋንንታዊ ኃይልም እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል እንገነዘባለን” ሲሉ አምነዋል። (ጎስፕል ኤንድ ስፒሪት (ወንጌልና መንፈስ)፣ ሚያዝያ 1977፣ በፋውንቴን ትረስትና በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊት ጉባኤ የታተመ፣ ገጽ 12) ሪሊጂየስ ሙቭመንትስ ኢን ኮንቴምፐራሪ አሜሪካ (በዛሬዪቱ አሜሪካ የሚገኙ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች) (በአይርቪንግ አይ ዛሬስኪይና ማርክ ፒ ሊዎን የተዘጋጀና ከኤል ፒ ገርላክ የተጠቀሰ) የተባለው መጽሐፍ በሐይቲ ውስጥ ጴንጠቆስጤዎችም ሆኑ የቀድሞ አባቶች አምልኮን የሚያስፋፋው የቩዱ ሃይማኖት ተከታዮች ‘በልሳናት እንደሚናገሩ’ ሪፖርት አድርገዋል።—(ፕሪንስተን፣ ኒው ጀርሲ፣ 1974)፣ ገጽ 693፤ በተጨማሪም 2 ተሰሎንቄ 2:9, 10⁠ን ተመልከት።

 በዛሬው ጊዜ የሚታየውና በመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ያደርጉት የነበረው ‘በልሳናት መናገር’ አንድ ዓይነት ነውን?

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ‘በልሳናት የመናገርን’ ችሎታ ጨምሮ ልዩ ልዩ የመንፈስ ተአምራዊ ስጦታዎች የአምላክ ሞገስ ከአይሁዳውን የአምልኮ ሥርዓት ተወስዶ አዲስ ወደ ተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ የተዘዋወረ መሆኑን አረጋግጠዋል። (ዕብ. 2:2–4) ይህ ዓላማ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የተፈጸመ ስለሆነ በዘመናችንም ይህንኑ ነገር ደጋግሞ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነውን?

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ‘በልሳናት የመናገር’ ችሎታ ኢየሱስ ተከታዮቹ እንዲፈጽሙ ለሰጣቸው ዓለም አቀፍ የምሥክርነት ሥራ ልዩ ግፊት ሰጥቶ ነበር። (ሥራ 1:8፤ 2:1–11፤ ማቴ. 28:19) በዛሬው ጊዜ ‘በልሳናት እንናገራለን’ ባዮቹ አለን የሚሉትን ችሎታ የሚጠቀሙበት ለዚህ ተግባር ነውን?

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ‘በልሳናት በሚናገሩበት’ ጊዜ የሚናገሩት ነገር እነዚያን ቋንቋዎች ለሚያውቁ ሰዎች የሚገባ ነበር። (ሥራ 2:4, 8) ዛሬ ግን ‘በልሳናት የሚናገሩ’ ሰዎች የሚያሰሙት ድምፅ ማንም ሊገባው የማይችል መንተባተብ አይደለምን?

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ጉባኤዎች ከሁለት ወይም ከሦስት የበለጡ ሰዎች በማንኛውም ስብሰባ ላይ ‘በልሳናት እንዲናገሩ’ መፍቀድ እንደማይገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል። እነዚህም ቢሆኑ የሚናገሩት ‘በየተራ’ ሲሆን የሚናገሩትን የሚተረጉም ሰው ካልኖረ ዝም ማለት ነበረባቸው። (1 ቆሮ. 14:27, 28) ዛሬ ግን የሚፈጸመው እንደዚህ ነውን?

በተጨማሪ በገጽ 380, 381 ላይ “መንፈስ” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።

መንፈስ ቅዱስ እነዚህን በተአምራዊ ፈውስ የሚያምኑ ሰዎች በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ወደማይገኙ ድርጊቶች መርቷቸው ሊሆን ይችላልን?

2 ጢሞ. 3:16, 17 የ1980 ትርጉም:- “ቅዱስ መጽሐፍ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው፤ እርሱ እውነትን ለማስተማር፣ የተሳሳቱትን ለመገሠጽ፣ ስሕተትን ለማረምና ለትክክለኛ ኑሮ የሚበጀውን መመሪያ ለመስጠት ይጠቅማል።” (አንድ ሰው በኢየሱስና በሐዋርያቱ በኩል የአምላክ መንፈስ ከገለጻቸው ነገሮች የሚቃረን በመንፈስ የተነገረ መልእክት እንዳለው ቢናገር የመንፈሱ ምንጭ አንድ ነው ለማለት ይቻላልን?)

ገላ. 1:8:- “እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፣ የተረገመ ይሁን።”

‘በልሳናት መናገርን’ የሚደግፉ ድርጅቶች አባላት አኗኗራቸው የአምላክ መንፈስ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ነውን?

በቡድን ደረጃ ሲታዩ እንደ የዋህነትና ራስን መግዛት የመሰሉትን የመንፈስ ፍሬዎች ያንጸባርቃሉን? የአምልኮ ስብሰባዎቻቸው ላይ የሚገኙ ሰዎች እነዚህን ባሕርያት በግልጽ ለመመልከት ይችላሉን?—ገላ. 5:22, 23

በእርግጥ “የዚህ ዓለም ክፍል” ያልሆኑ ናቸውን? በዚህ ምክንያት ለአምላክ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ያደሩ ናቸው ወይስ በዓለም የፖለቲካ ጉዳዮች የተጠላለፉ? በጦርነት ጊዜያት ከደም ወንጀል ራሳቸውን ጠብቀዋልን? በቡድን ደረጃ ከዓለም የሥነ ምግባር ርኩሰት የራቁ ናቸው የሚል ጥሩ ዝና ያተረፉ ናቸውን?—ዮሐ. 17:16፤ ኢሳ. 2:4፤ 1 ተሰ. 4:3–8

በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች ተለይተው የሚታወቁት ‘በልሳናት በመናገር’ ችሎታ ነውን?

ዮሐ. 13:35:- “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”

1 ቆሮ. 13:1, 8:- “በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጽናጽል ሆኜአለሁ። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ።”

ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ በተከታዮቹ ላይ እንደሚወርድና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምሥክሮቹ እንደሚሆኑ ተናግሯል። (ሥራ 1:8) ‘አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ’ አዟቸዋል። (ማቴ. 28:19) በተጨማሪም ‘ይህ የመንግሥት ምሥራች ለምሥክርነት በመላው ዓለም እንደሚሰበክ’ ተንብዮአል። (ማቴ. 24:14) በዛሬው ጊዜ በቡድንም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ይህንን ሥራ የሚሠሩ እነማን ናቸው? ኢየሱስ በተናገረው መሠረት አንድ ቡድን መንፈስ ቅዱስ ያለው መሆኑንና አለመሆኑን የሚያረጋግጠው ይህ ሥራ መሆን አይገባውምን?

‘በልሳናት መናገር’ “ፍጹም” የሆነው እስከሚመጣ ድረስ የሚቆይ ነውን?

በ⁠1 ቆሮንቶስ 13:8 ላይ የተለያዩ የተአምራት ስጦታዎች ተዘርዝረዋል። ከነዚህም መካከል ትንቢት፣ በልሳናት መናገርና እውቀት ተጠቅሰዋል። ቁጥር 9 እንደገና ከእነዚህ ስጦታዎች ስለ ሁለቱ ማለትም ስለ እውቀትና ትንቢት ስለመናገር እንዲህ ይላል:- “ከእውቀት ከፍለን [ከፊሉን] እናውቃለንና፣ ከትንቢትም ከፍለን [ከፊሉን] እንናገራለን።” ወይም በሪስ ላይ እንዲህ ተብሎ ይነበባል:- “እውቀታችን ፍጹም አይደለም፣ ትንቢታችንም ፍጹም አይደለም።” ከዚያም ቁጥር 10 እንዲህ በማለት ይገልጻል:- “ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።” “ፍጹም” የሚለው ቃል የተተረጐመው ቴሊኦን ከሚለው የግሪክኛ ቃል ሲሆን ሙሉ በሙሉ መዳበርን፣ የተሟላ ወይም ፍጹም የመሆንን ሐሳብ ያስተላልፋል። ሮዘ፣ ባይ እና አዓት “የተሟላ” ብለው ተርጉመውታል። ‘ፍጹም ያልሆነ’፣ “ከፍለን” ወይም ከፊል የተባለው በልሳናት የመናገር ስጦታ እንዳልሆነ ልብ ማለት ይገባል። እንዲህ የተባለው ‘ትንቢት መናገር’ ወይም “እውቀት” ነው። በሌላ አነጋገር እነዚህ ተአምራዊ ስጦታዎች ቢኖሩም እንኳ የጥንት ክርስቲያኖች ስለ አምላክ ዓላማ የነበራቸው ግንዛቤ ፍጹም ያልሆነ ወይም ከፊል ብቻ ነበር። ትንቢቶቹ በሚፈጸሙበትና የአምላክ ዓላማ በሚከናወንበት ጊዜ ግን ‘ፍጹም የሆነው’ ወይም የተሟላው ይመጣል። ስለዚህ ይህ ጥቅስ የሚናገረው ‘የልሳናት ስጦታ’ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቀጥል እንዳልሆነ ግልጽ ነው።

ይሁን እንጂ ‘የልሳናት ስጦታ’ የክርስትና ክፍል ሆኖ የሚቆየው እስከ መቼ ድረስ እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደሚያመለክተው ይህ የልሳናት ስጦታም ሆነ ሌሎቹ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ወደ ሌሎች ሰዎች የሚተላለፉት የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት እጃቸውን ሲጭኑ ወይም ሐዋርያት በተገኙበት ቦታ ብቻ ነበር። (ሥራ 2:4, 14, 17፤ 10:44–46፤ 19:6፤ እንዲሁም ሥራ 8:14–18⁠ን ተመልከት።) ስለዚህ ሐዋርያትና በዚህ መንገድ የመንፈስ ስጦታ የተቀበሉት ሰዎች ሞተው ካለቁ በኋላ በአምላክ የመንፈስ አሠራር የተገኙት ተአምራዊ ስጦታዎች አቁመዋል። ይህ አመለካከት በ⁠ዕብራውያን 2:2–4 ላይ ከተገለጸው የእነዚህ ስጦታዎች ዓላማ ጋር ይስማማል።

ማርቆስ 16:17, 18 ‘በአዲስ ቋንቋ የመናገር’ ችሎታ የአማኞች መለያ ምልክት እንደሚሆን ያመለክት የለምን?

እነዚህ ቁጥሮች ‘በአዲስ ቋንቋ ስለመናገር’ ብቻ ሳይሆን እባብ ስለመያዝና የሚገድል መርዝ ስለመጠጣት እንደሚናገሩ ልብ ማለት ይገባል። ‘በልሳናት የሚናገሩ’ ሁሉ እነዚህን ነገሮች ሞክሩ ብለው ያበረታታሉን?

ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን እነዚህን ቁጥሮች እንደማይቀበሏቸው የተሰጠውን አስተያየት በገጽ 159, 160 ላይ “ተአምራዊ ፈውስ” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።

አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

‘በልሳናት በመናገር ታምናላችሁ?’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘የይሖዋ ምሥክሮች በብዙ ቋንቋዎች ይናገራሉ። ይሁን እንጂ በስሜት ገንፍለን ‘በማይታወቁ ልሳናት’ አንናገርም። አንድ ጥያቄ ብጠይቅዎትስ? በዛሬው ጊዜ የሚታየው ‘የልሳናት ንግግር’ በአንደኛው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩት ክርስቲያኖች ይናገሩ ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት ነው ብለው ያምናሉ?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘ለማወዳደር የሚረዱ አንዳንድ ጥሩ ጥሩ ነጥቦችን ልጥቀስልዎት። ( በገጽ 400, 401 ያሉትን ሐሳቦች ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።)’

ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ‘በልሳናት ይናገሩ’ እንደነበረ እናምናለን። በዚያ ዘመን በልሳናት መናገር ያስፈለገባቸው ምክንያቶች ነበሩ። እነዚህ ምክንያቶች ምን እንደነበሩ ያውቃሉ?’ ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘አምላክ ሞገሱን ከአይሁድ ሥርዓት አንሥቶ አዲስ ወደ ተመሠረተው የክርስቲያን ጉባኤ እንዳዛወረ የሚያረጋግጥ ምልክት ሆኖ አገልግሏል። (ዕብ. 2:2–4)’ (2) ‘ምሥራቹን በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሠራጨት የሚያስችል ተግባራዊ ጠቀሜታ ያለው መንገድ ነበር። (ሥራ 1:8)’