በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኃጢአት

ኃጢአት

ፍቺ:- በዕብራይስጥና በግሪክኛው መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ኃጢአት ቃል በቃል ሲተረጐም ደረጃውን አለማሟላት ማለት ነው። የማሰብ ችሎታ ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ ሊጠብቁት የሚገባቸውን “ደረጃ” የሚወስነው አምላክ ራሱ ነው። ይህን ደረጃ ሳይጠብቁ መገኘት ኃጢአት ነው። ኃጢአትም ዓመፅ ወይም ሕገወጥነት ነው። (ሮሜ 3:23፤ 1 ዮሐ. 5:17፤ 3:4) ከአምላክ ባሕርያት፣ የአቋም ደረጃዎች፣ መንገዶችና ፈቃድ ጋር የማይስማማ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ቅዱስ ናቸው። ኃጢአት የሚሠራው መጥፎ ድርጊት በመፈጸም፣ መደረግ የሚገባውን ባለማድረግ፣ ለአምላክ አክብሮት የማያሳይ ቃል በመናገር፣ ንጹሕ ያልሆነ ነገር በማሰብ ወይም በራስ ወዳድነት ላይ የተመሠረቱ ምኞቶችና የውስጥ ዓላማዎች በማስተናገድ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ በውርሻ ምክንያት በመጣው ኃጢአትና በራስ ፈቃድ በሚሠራ ኃጢአት መካከል፤ እንዲሁም ኃጢአት ሠርቶ ንሥሐ በመግባትና ኃጢአት ማድረግን በመቀጠል መካከል ልዩነት ያደርጋል።

አዳም ፍጹም ሰው ከነበረ እንዴት ኃጢአት ሊሠራ ቻለ?

አዳም ፍጹም የነበረ ስለመሆኑ ዘፍጥረት 1:27, 31⁠ን እና ዘዳግም 32:4⁠ን ማንበብ ይቻላል። ይሖዋ አምላክ ምድራዊ ፍጥረቱ በሙሉ፣ አዳምና ሔዋንም ጭምር፣ “እጅግ መልካም” እንደሆኑ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር? ሥራው ሁሉ ፍጹም በሆነው አምላክ ተመዝኖ “እጅግ መልካም” እንደሆነ ከተናገረለት ፍጥረቱ ፍጹም ደረጃዎቹን አሟልቶ ነበር ማለት ነው።

አዳምና ሔዋን ፍጹም በመሆናቸው መጥፎ ነገር ሊያደርጉ አይችሉም ማለት ነበርን? አንድን ሮቦት የሠራ ሰው ሮቦቱ የታቀደለትን ዓላማ እንዲፈጽም ሊጠብቅበት ይችላል። ሆኖም አንድ ፍጹም ሮቦት ፍጹም ሰው ሊሆን አይችልም። እንዲኖራቸው የሚፈለጉባቸው ባሕርያት አንድ አይደሉም። አዳምና ሔዋን ሰዎች ነበሩ እንጂ ሮቦቶች አልነበሩም። አምላክ ለሰው ልጆች ትክክልና ስህተት ከሆነው ነገር፣ ከመታዘዝና ካለመታዘዝ አንዱን የመምረጥ ችሎታ ሰጥቷቸው ነበር። ባጭሩ ሥነ ምግባራዊ ውሳኔዎችን የማድረግ ችሎታ ሰጥቷቸው ነበር። የሰው ልጆች የተሠሩት በዚህ መንገድ ስለነበረ እንደነዚህ ባሉት ነገሮች ላይ ውሳኔዎችን (የጥበብ ውሳኔዎችን) ለማድረግ ባይችሉ ኖሮ ፍጹማን አይደሉም ሊባል ይችል ነበር።—ከ⁠ዘዳግም 30:19, 20​ና ከ​ኢያሱ 24:15 ጋር አወዳድር።

አዳምና ሔዋን ፍጹም ሆነው ስለተፈጠሩ ውሳኔያቸው በሙሉ ትክክል መሆን ይኖርበታልን? እንደዚያ ከተባለ ምንም ምርጫ አልነበራቸውም ማለት ይሆናል። አምላክ ግን በደመ ነፍስ ብቻ እንዲታዘዙት አድርጎ አልፈጠራቸውም። ለእርሱ ባላቸው ፍቅር ተገፋፍተው ብቻ እንዲታዘዙት ስለፈለገ የመምረጥ ችሎታ ሰጥቷቸዋል። ልባቸው በራስ ወዳድነት እንዲመራ ከፈቀዱ ደግሞ ትእዛዙን ሊጥሱ ይችሉ ነበር። አንተ ራስህ ደስ የሚልህ ሰዎች ተገደው አንድ ነገር ሲያደርጉልህ ነው ወይስ ከልባቸው ፈልገው ሲያደርጉልህ?—ከ⁠ዘዳግም 11:1⁠ና ከ⁠1 ዮሐንስ 5:3 ጋር አወዳድር።

እንደነዚህ ያሉት ፍጹማን ሰዎች በራስ ወዳድነት ተነሣሥተው እንዴት ኃጢአት ሊሠሩ ይችላሉ? ሥጋዊ አካላቸው ፍጹም ሆኖ የተሠራ ቢሆንም ተስማሚ ምግብ ካላገኘ ሥራውን አሟልቶ ማከናወን አይችልም ነበር። በተመሳይይም አእምሯቸውን መጥፎ ሐሳቦችን ከመገቡ የሥነ ምግባር ብልሽትና ርኩሰት ያስከትልባቸዋል። ያዕቆብ 1:14, 15 “እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች” በማለት ሁኔታውን ይገልጻል። በሔዋን ውስጥ የተሳሳተ ፍላጎት መብቀል የጀመረው ሰይጣን በእባብ ተጠቅሞ የነገራትን ነገር በስሜት ማዳመጥ በጀመረች ጊዜ ነበር። አዳምም ሚስቱ የተከለከለውን ፍሬ በልቶ እንዲተባበራት ስትጐተጉተው እሺ አላት። ሁለቱም መጥፎውን ሐሳብ ከአእምሮአቸው ከማውጣት ይልቅ እንዲያድግ ፈቀዱለት። በዚህም ምክንያት ኃጢአት ሠሩ።—ዘፍ. 3:1–6

አዳም ኃጢአት መሥራቱ “የአምላክ ዕቅድ” ክፍል ነበርን?

በገጽ 29 ላይ “አዳምና ሔዋን” በሚለው ርዕስ ሥር እንዲሁም በገጽ 142, 143 ላይ “ዕድል” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።

በአሁኑ ጊዜ “ኃጢአት” የሚባል ነገር አለ?

ምሳሌ:- አንድ የታመመ ሰው የሙቀት መለኪያ መሣሪያውን ቢሰብረው ሕመምተኛው ትኩሳት የለውም ማለት ነውን? አንድ ሌባ በሕግ መጽሐፍ ውስጥ የሰፈሩትን ሕጎች አላምንባቸውም ቢል አለማመኑ ከወንጀሉ ነፃ ያደርገዋልን? በተመሳሳይም ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን የብቃት ደረጃዎች መጠበቅ አስፈላጊነቱ አይታየንም ቢሉ ኃጢአት መኖሩ ይቀራል ማለት አይሆንም።—1 ዮሐንስ 1:8⁠ን ተመልከት።

አንዳንድ ሰዎች የአምላክ ቃል የሚከለክለውን ለማድረግ ይመርጡ ይሆናል። ይህን ማድረጋቸው ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት መሆኑን አያረጋግጥም። ገላትያ 6:7, 8:- “አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና” በማለት ያስጠነቅቃል። በሩካቤ ሥጋ የሚተላለፉ በሽታዎች፣ የቤተሰቦች መፈራረስና እነዚህን የመሳሰሉት ነገሮች እንደ ወረርሽኝ መስፋፋታቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው እውነት መሆኑን ያረጋግጣል። ሰውን የፈጠረው አምላክ ነው። እርሱም ዘላቂ ደስታ የሚያመጣልን ምን እንደሆነ ያውቃል። ይህንንም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገልጾልናል። ታዲያ እሱ የሚለውን እሺ ብሎ መስማት ምክንያታዊ አይሆንምን? (አምላክ ስለ መኖሩ ተጨማሪ ማስረጃ ለማግኘት “አምላክ” የሚለውን ዋና ርዕስ ተመልከት።)

ኃጢአት ናቸው የሚባሉት አብዛኞቹ ነገሮች የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ግፊቶች አይደሉምን?

የፆታ ግንኙነት መፈጸም ኃጢአት ነውን? አዳምና ሔዋን የፆታ ግንኙነት በመፈጸማቸው ምክንያት ኃጢአት ሠርተዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ አይልም። ዘፍጥረት 1:28 አምላክ ራሱ አዳምንና ሔዋንን “ብዙተባዙምድርንም ሙሉአት” እንዳላቸው ይናገራል። ለዚህ ደግሞ ሩካቤ ሥጋ መፈጸም ያስፈልጋቸው ነበር፤ አይደለም እንዴ? መዝሙር 127:3 “ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ” እንዲሁም “ዋጋ” እንደሆኑ ይናገራል። ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ የበላችው ብቻዋን ሳለች እንደሆነና ለአዳም እንዲበላ የሰጠችው በኋላ እንደነበረ ማስታወስ ተገቢ ነው። (ዘፍ. 3:6) የተከለከለው ፍሬ የበቀለበት ዛፍ ቃል በቃል ዛፍ እንደነበረ ግልጽ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚከለክለው በባልና በሚስት መካከል የሚደረገውን ትክክለኛ የፆታ ግንኙነት ሳይሆን እንደ ዝሙት፣ ምንዝር፣ ግብረ ሰዶም ያሉትን ድርጊቶችና ከእንስሳት ጋር የሚፈጸመውን ሩካቤ ሥጋ ነው። እነዚህን ድርጊቶች በመፈጸም ምክንያት የሚመጡትን መጥፎ ፍሬዎች ስንመለከት እንዲህ ያለ እገዳ መደረጉ እንዴት እንደተሠራን የሚያውቀው አምላካችን በፍቅር እንደሚያስብልን ያሳያል።

ዘፍ. 1:27:- “እግዚአብሔርሰውን [አዳምን ] በመልኩ ፈጠረበእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው።” (ስለዚህ አዳም የአምላክን ቅዱስ ባሕርያት ማንጸባረቅና የአምላክን መመሪያዎች በአድናቆት መቀበል ተፈጥሯዊ ፍላጎቱ ነበር። ይህን ሳያደርግ ከቀረ የሚጠበቅበትን ደረጃ አላሟላም ወይም ኃጢአት ሠራ ማለት ነበር። ሮሜ 3:23⁠ን ተመልከት። በተጨማሪም 1 ጴጥሮስ 1:14–16⁠ን ተመልከት።)

ኤፌ. 2:1–3:- “[እናንተ ክርስቲያኖች] በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፣ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፣ የሥጋችንንና የልቦናችንን ፈቃድ እያደረግን፣ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።” (የኃጢአተኛው አዳም ልጆች በመሆናችን በኃጢአት ውስጥ ተወልደናል። ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ ልባችን ወደ ጥፋት ያዘነበለ ነው። እነዚህን ክፉ ዝንባሌዎች ካልተቆጣጠርን ከጊዜ በኋላ ኃጢአት ልማድ ሊሆንብን ይችላል። በአካባቢያችን ያሉ ሌሎች ሰዎች እነዚህን ነገሮች ስለሚያደርጉ ድርጊቶቹ “ትክክል” መስለው ሊታዩን ይችላሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ በሰው አፈጣጠርና አምላክ ለሰው ልጆች በነበረው ዓላማ መሠረት በአምላክ አመለካከት ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር ይገልጻል። አምላክ የሚነግረንን ብናዳምጥና በፍቅር ብንታዘዝ ሕይወታችን ከዚህ በፊት በማናውቀው መጠን አመርቂና ትርጉም ያለው ይሆንልናል። ለወደፊትም የዘላለም ሕይወት ተስፋ ይኖረናል። ፈጣሪያችን እርሱ ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ እንድንቀምስ ሞቅ ባለ መንፈስ ይጋብዘናል።—መዝ. 34:8)

ኃጢአት አንድ ሰው ከአምላክ ጋር ያለውን ዝምድና የሚነካበት እንዴት ነው?

1 ዮሐ. 3:4, 8:- “ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፣ ኃጢአትም ዓመፅ ነው። ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው።” (እንዴት ያለ ጠንካራ ማሳሰቢያ ነው! ሆን ብለው የኃጢአትን መንገድ የሚመርጡና የሚገፉበት ሁሉ በአምላክ ዘንድ እንደ ወንጀለኞች ተደርገው ይታያሉ። የመረጡት አካሄድ ሰይጣን ራሱ ከተከተለው አካሄድ ጋር አንድ ዓይነት ነው።)

ሮሜ 5:8, 10:- “ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና . . . ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት [ታረቅን።]” (ኃጢአተኞች የአምላክ ጠላቶች ተብለው መጠራታቸውን ልብ በል። ስለዚህ አምላክ ከእርሱ ጋር እንድንታረቅ ባዘጋጀው መንገድ መጠቀም ምንኛ ጥበብ ነው!)

1 ጢሞ. 1:13:- “ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ [በማለት ሐዋርያው ጳውሎስ ተናግሯል።]” (ትክክለኛውን መንገድ ጌታ ካሳየው በኋላ ግን ያንን መንገድ ከመከተል ወደኋላ አላለም።)

2 ቆሮ. 6:1, 2:- “አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናችኋለን፤ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፣ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላል። እነሆ፣ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፣ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (የመዳን አጋጣሚ ክፍት የሆነበት ጊዜ አሁን ነው። አምላክ እንዲህ ያለውን የማይገባ ደግነት ለኃጢአተኞቹ የሰው ልጆች ለዘላለም እንደዘረጋ አይኖርም። ስለዚህ የዚህን ደግነት ዓላማ እንዳንስት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገናል።)

ከኃጢአተኝነታችን ነፃ ልንወጣ የምንችለው እንዴት ነው?

ቤዛ” የሚለውን ዋና ርዕስ ተመልከት።