በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርማጌዶን

አርማጌዶን

ፍቺ:- ከዕብራይስጥ የተወሰደውና ብዙ ተርጓሚዎች “አርማጌዶን” የሚሉት ሐርማጌዶን የተባለ የግሪክኛ ቃል ትርጉሙ “የመጊዶ ተራራ” ወይም “የወታደራዊ ሠራዊት መሰብሰቢያ ተራራ” ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ስም የሚሰጠው ለአንድ የኑክሌር እልቂት ሳይሆን “ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላክ” ለሚያመጣው ዓለም አቀፍ “ታላቅ የጦርነት ቀን” ነው። (ራእይ 16:14, 16 አዓት ) ይህ ስም በተለይ ምድራዊ የፖለቲካ ገዥዎች ይሖዋንና በኢየሱስ ክርስቶስ የሚመራውን መንግሥቱን በመቃወም የሚሰበሰቡበትን “ቦታ” [በግሪክኛ ቶፖን፣ ማለትም “ሁኔታ”] ያመለክታል። ይህም ተቃውሞ የሚገለጸው የአምላክ መንግሥት የሚታዩ ወኪሎች በሆኑት በይሖዋ ምድራዊ አገልጋዮች ላይ ወደፊት በሚወሰደው ዓለም አቀፋዊ እርምጃ ነው።

አንዳንድ ሰዎች “ተርሞ ኑክሌር አርማጌዶን” ብለው በሚጠሩት እልቂት ሰዎች ምድርን እንዲያጠፉ አምላክ ይፈቅዳልን?

መዝ. 96:10:- “እግዚአብሔር ነገሠ በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን [በዕብራይስጥ ቴቬል፣ ይኸውም ምድርን፣ ለምና የሰው መኖሪያ የሆነውን ክፍል፣ የሰው መኖሪያ ሊሆን የሚችለውን መሬት] እርሱ አጸናው።”

መዝ. 37:29:- “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፣ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ።”

ራእይ 11:18:- “አሕዛብ ተቆጡ፣ ቁጣህም [የይሖዋ ቁጣ] መጣ፣ . . . ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው አርማጌዶን ምንድን ነው?

ራእይ 16:14, 16:- “ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፣ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ። በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ አስከተቱአቸው።”—ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

አርማጌዶን በመካከለኛው ምሥራቅ ብቻ የሚደረግ ጦርነት ነውን?

የሁሉም ብሔራት ገዥዎችና ወታደሮች አምላክን በመቃወም ይሰበሰባሉ

ራእይ 16:14:- “በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።”—ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

ራእይ 19:19:- “በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና [ሰብዓዊው የፖለቲካ አገዛዝ በአጠቃላይ] የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።”

ኤር. 25:33:- “በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ።”

አርማጌዶን (ሐር–ማጌዶን) የሚል ስም መሰጠቱ ጦርነቱ ቃል በቃል በመጊዶ ተራራ ላይ እንደሚደረግ ሊያመለክት አይችልም

ቃል በቃል የመጊዶ ተራራ የሚባል ቦታ የለም። ዛሬ የጥንቱ መጊዶ ፍርስራሽ በሚገኝበት ቦታ ላይ የሚታየው 21 ሜትር ከፍታ ያለው ጉብታ ብቻ ነው።

ከመጊዶ በታች የሚገኘው የኤስድራኤሎን ሜዳ ‘የመላዋን ምድር’ ነገሥታትና ወታደራዊ ኃይሎች ሊይዝ አይችልም። ይህ ሜዳ ሦስት ጐን ያለው ሆኖ ርዝመቱ 32 ኪሎሜትር፣ ጐኑ ደግሞ በስተምሥራቅ ጫፍ 29 ኪሎ ሜትር ነው።—ዘ ጂኦግራፊ ኦቭ ዘ ባይብል (ኒው ዮርክ፣ 1957)፣ ዴንስ ባሊ፣ ገጽ 148

መጊዶ ብዙ ታሪካዊ ክንውኖች የታዩበት ቦታ በመሆኑ አርማጌዶን የሚለው ስም ከመጊዶ መወሰዱ ተገቢ ነው፤ ከመጊዶ በታች ያለው ሜዳ ወሳኝ የሆኑ ጦርነቶች ተደርገውበታል

ይሖዋ በዚህ ቦታ ላይ የከነዓን ጦር ሠራዊት አለቃ ሲሣራ በመስፍኑ በባራቅ እንዲሸነፍ አደርጓል።—መሳ. 5:19, 20፤ 4:12–24

የግብፅ ፈርዖን የነበረው ተትሞስ ሣልሳዊ እንዲህ ብሎ ነበር:- “መጊዶን መማረክ ማለት አንድ ሺህ ከተሞች መማረክ ማለት ነው!”—ኤንሸንት ኒር ኢስተርን ቴክስትስ ሪሌቲንግ ቱ ዘ ኦልድ ቴስታመንት (ፕሪንስተን፣ ኒው ጀርሲ፣ 1969) በጀምስ ፕሪቻርድ የተዘጋጀ፣ ገጽ 237

አርማጌዶን የሁሉም ብሔራት ገዥዎች፣ ደጋፊዎቻቸውና ወታደሮቻቸው የሚካፈሉበት የዓለም ሁኔታ ስለሆነ (“የወታደራዊ ሠራዊት መሰብሰቢያ” የሚል ትርጉም ካለው) መጊዶ ከተባለው ቃል መወሰዱ ተገቢ ነው።

አርማጌዶን ላይ የሚጠፋው ማን ወይም ምንድን ነው?

ዳን. 2:44:- “የሰማይ አምላክ . . . መንግሥት ያስነሣል፤ . . . እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፣ ለዘላለምም ትቆማለች።”

ራእይ 19:17, 18:- “አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፣ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ:- መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎቹንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።”

1 ዮሐ. 2:16, 17:- “በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም . . . እንጂ ከአባት [አይደለም።] ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።”

ራእይ 21:8:- “የሚፈሩና የማያምኑ የርኩሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛ ሞት ነው።”

ጥፋቱ ዘላለማዊ ይሆናልን?

ማቴ. 25:46:- “እነዚያም [ለክርስቶስ “ወንድሞች” መልካም ያላደረጉት] ወደ ዘላለም ቅጣት፣ [“መቆረጥ” አዓት] . . . ይሄዳሉ።”

2 ተሰ. 1:8, 9:- “እግዚአብሔርን [የማያውቁት፣] ለጌታችን ለኢየሱስ ወንጌል [የማይታዘዙት] . . . በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።”

ከጥፋቱ የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉን?

ሶፎ. 2:3:- “እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ ጽድቅንም ፈልጉ፣ ትሕትናንም ፈልጉ፤ ምናልባት በእግዚአብሔር ቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።”

ሮሜ 10:13:- “የጌታን [“የይሖዋን” አዓት ] ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”

መዝ. 37:34 አዓት:- “ይሖዋን ተስፋ አድርግ፣ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድርን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።”

ዮሐ. 3:16:- “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን [ሰጥቷል።]”

ራእይ 7:9, 10, 14:- “አየሁ፣ እነሆም፣ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤ በታላቅም ድምፅ እየጮኹ:- በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ። . . . እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው።”

ትንንሽ ሕፃናት በአርማጌዶን ጊዜ ምን ይሆናሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጥያቄ በቀጥታ አይመልስም፤ እኛም በዚህ ጉዳይ ላይ ፍርድ ለመስጠት አንችልም። ይሁን እንጂ አምላክ የእውነተኛ ክርስቲያኖችን ትናንሽ ልጆች “የተቀደሱ” አድርጎ እንደሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። (1 ቆሮ. 7:14) በተጨማሪም አምላክ በጥንት ጊዜ ክፉዎችን ሲያጠፋ ትናንሽ ልጆቻቸውንም ጨምሮ እንዳጠፋ መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል። (ዘኁ. 16:27, 32፤ ሕዝ. 9:6) አምላክ ማንም ሰው እንዲጠፋ አይፈልግም። በዚህም ምክንያት ለወላጆችና ለሕፃናት በማሰብ በአሁኑ ጊዜ ማስጠንቀቂያ እያስነገረ ነው። ታዲያ ወላጆች አሁንም ሆነ ወደፊት በአርማጌዶን ጊዜ የአምላክን ሞገስ ለልጆቻቸው የሚያስገኝላቸውን መንገድ ቢከተሉ ጥበብ አይሆንምን?

አምላክ ክፉዎችን ማጥፋቱ የፍቅር ጠባዩን የሚጻረር ድርጊት ነውን?

2 ጴጥ. 3:9:- “ጌታ [“ይሖዋ” አዓት ] . . . ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።”

ሉቃስ 18:7, 8:- “እግዚአብሔር . . . ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፣ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል።”

2 ተሰ. 1:6:- “[ለእናንተ ለአገልጋዮቹ] መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፣ . . . ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።”

በዚህ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ አቋም መያዝ ይቻላልን?

2 ተሰ. 1:8:- “እግዚአብሔርን [በራሳቸው ምርጫ] የማያውቁትን፣ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል።”

ማቴ. 24:37–39:- “የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ . . . የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉንም እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፣ የሰው ልጅ መምጣት [መገኘት አዓት ] ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።”

ማቴ. 12:30:- “ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፣ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።”

ከ⁠ዘዳግም 30:19, 20 ጋር አወዳድር።

ብሔራትን ከአምላክ ጋር ለመዋጋት ወደሚያደርሳቸው የዓለም ሁኔታ እየነዳቸው ያለው የማን ግፊት ነው?

ራእይ 16:13, 14 አዓት:- “ከዘንዶውም [ከሰይጣን ዲያብሎስ፤ ራእይ 12:9] አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጉንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤ ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና። ሁሉን ማድረግ ወደሚችል አምላክ ታላቅ የጦርነት ቀን ሊሰበስቧቸው ወደ ምድር ነገሥታት ይሄዳሉ።”

ከ⁠ሉቃስ 4:5, 6፤ 1 ዮሐንስ 5:19፤ እንዲሁም ከ⁠ሥራ 5:38, 39፤ 2 ዜና መዋዕል 32:1, 16, 17 ጋር አወዳድር።