በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኢየሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ ክርስቶስ

ፍቺ:- ይሖዋ ብቻውን የፈጠረው የአምላክ አንድያ ልጅ። ይህ ልጅ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው። በሰማይና በምድር ያሉት ነገሮች ሁሉ የተፈጠሩት በእርሱ አማካኝነት ነው። በጽንፈ ዓለም ውስጥ ሁለተኛውን ከፍተኛ የሥልጣን ደረጃ የያዘ እርሱ ነው። ሕይወቱን ለሰው ልጆች ቤዛ አድርጎ እንዲሰጥ ይሖዋ ወደ ምድር የላከው ይህንን ልጅ ነው። በዚህም እምነት ለሚያሳዩት የአዳም ልጆች የዘላለም ሕይወት መንገድ ተከፈተላቸው። ይህ ልጅ ወደ ሰማያዊ ክብር ተመልሶ አሁን ንጉሥ ሆኖ ይገዛል። ክፉዎችን ሁሉ ለማጥፋትና አባቱ ለምድር ያለውን የመጀመሪያ ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል። ኢየሱስ የሚለው የዕብራይስጡ ስም “ይሖዋ አዳኝ ነው” ማለት ነው። ክርስቶስ በዕብራይስጥ ማሺያህ (መሲሕ) ከሚለው አጠራር ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ትርጉሙም “የተቀባ” ማለት ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በታሪክ ውስጥ በእርግጥ የነበረ ሰው ነውን?

ኢየሱስ ክርስቶስ በታሪክ ውስጥ በእርግጥ በሕይወት የኖረ ሰው ለመሆኑ ዋነኛው ማስረጃ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ነው። በወንጌሎች ተመዝግቦ የሚገኘው ታሪክ በማይታወቅ ጊዜና ቦታ የተፈጸሙ ድርጊቶችን የሚያወራ የተድበሰበሰ ትረካ አይደለም። የተመዘገበው ታሪክ ነገሮች የተፈጸሙበትን ጊዜና ቦታ ለይቶ የሚገልጽ ዘገባ ነው። ለምሳሌ ያህል በ⁠ሉቃስ 3:1, 2, 21–23 ላይ የተገለጸውን ተመልከት።

የመጀመሪያው መቶ ዘመን አይሁዳዊ ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ “የኢየሱስ (በኋላ ክርስቶስ የተባለው) ወንድም ያዕቆብ” በድንጋይ ተወግሮ ስለመሞቱ ጽፏል። (ዘ ጂዊሽ አንቲኩቲስ፣ ጆሴፈስ፣ 20ኛው መጽሐፍ፣ ክፍል 200) በ18ኛው መጽሐፍ ክፍል 63, 64 ላይ ስለ ኢየሱስ የተጠቀሰው ቀጥተኛ የሆነና ኢየሱስን በተሻለ መልክ የሚያቀርበው ሐተታ በኋላ የተጨመረ ወይም ክርስቲያኖች ሌሎችን ለመሳብ ብለው የጨመሩት ሳይሆን አይቀርም በማለት አንዳንዶች ክርክር አስነስተውበታል። ሆኖም ግን ቃላቱና የአጻጻፍ ስልቱ የጆሴፈስ መሆናቸው ታውቋል፤ እንዲሁም ምንባቡ በሌሎች የብራና ጽሑፎች ውስጥ ይገኛል።

በአንደኛው መቶ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ይኖር የነበረው ሮማዊው ታሪክ ጸሐፊ ታሲተስ እንዲህ በማለት ጽፏል:- “[ክርስቲያን] ለሚለው ስም መገኛ የሆነው ክራይስቱስ [በላቲን “ክርስቶስ” ማለት ነው] በጢባርዮስ የንግሥና ዘመን ከአስተዳዳሪዎቻችን አንዱ በነበረው በጰንጤናዊው ጲላጦስ እጅ ከፍተኛ ቅጣት ተቀብሏል።”—ዘ ኮምፕሊት ወርክስ ኦቭ ታሲተስ (የታሲተስ ሙሉ ሥራዎች)፣ (ኒው ዮርክ፣ 1942) “ዘ አናልስ 15ኛው መጽሐፍ፣ ገጽ 44

ከክርስትና ጽሑፎች ውጭ ስለ ኢየሱስ የሚናገሩ ጥንታውያን የታሪክ ማስረጃዎችን በተመለከተ ዘ ኒው ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ:- “በ18ኛው መቶ ዘመን መጨረሻ፣ በ19ኛው መቶ ዘመንና በ20ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ በእርግጥ በሕይወት የኖረና ታሪክ ያለው ሰው ስለመሆኑ በአንዳንድ ጸሐፊዎች ያለ በቂ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ክርክር ቢያስነሱም፣ ሌላው ቀርቶ የክርስትና እምነት ተቃዋሚዎች እንኳ በፍጹም ተጠራጥረው እንደማያውቁ እነዚህ ነፃ ዘገባዎች ያረጋግጣሉ” በማለት ይገልጻል።—(1976)፣ ማክሮፔድያ፣ ጥራዝ 10፣ ገጽ 145

ኢየሱስ እንዲያው ጥሩ ሰው ብቻ ነበርን?

ኢየሱስ የጥሩነት መለኪያ አባቱ እንጂ እርሱ አለመሆኑን ያውቅ ስለነበር “ጥሩ መምህር” በማለት የተናገረውን ሰው ገሥጾታል። (ማርቆስ 10:17, 18 አዓት) ይሁን እንጂ ኢየሱስ ሰዎች በአጠቃላይ ጥሩ ሰው ነው የሚሉት ዓይነት ሰው ከነበረ እውነተኛ ሰው መሆን ይኖርበታል። ጠላቶቹ እንኳ ሳይቀሩ እውነተኛ ሰው እንደነበር አምነዋል። (ማር. 12:14) ኢየሱስ ራሱ ሰው ከመሆኑ በፊት በሕይወት ይኖር እንደነበረ፣ ብቸኛው የአምላክ ልጅ እንደሆነ፣ በዕብራውያን ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ይመጣል ተብሎ ትንቢት የተነገረለት መሲሕ እንደሆነ ተናግሯል። ስለዚህ ኢየሱስ ስለራሱ የተናገረው እውነት መሆን ይኖርበታል። ካልሆነ ደግሞ ኢየሱስ በጣም አታላይ ሰው ነበር ማለት ነው። ሁለቱም አማራጭ ኢየሱስ እንዲያው ጥሩ ሰው ብቻ ነበር የሚለውን አመለካከት አይደግፍም።—ዮሐ. 3:13፤ 10:36፤ 4:25, 26፤ ሉቃስ 24:44–48

ኢየሱስ ከሙሴ፣ ከቡድሃ፣ ከመሐመድና ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ጋር የሚተካከል ሥልጣን የነበረው ነቢይ ብቻ ነበርን?

ኢየሱስ ራሱ የአምላክ ብቸኛ ልጅ እንደሆነ (ዮሐ. 10:36፤ ማቴ. 16:15–17)፣ ይመጣል የተባለለት መሲሕ እንደሆነ (ማር. 14:61, 62)፣ በሰማይ ቅድመ ሰብዓዊ ኅልውና እንደነበረው (ዮሐ. 6:38፤ 8:23, 58) እንደሚገደልና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ሰማያት እንደሚመለስ አስተምሯል። (ማቴ. 16:21፤ ዮሐ. 14:2, 3) እነዚህ አባባሎች እውነተኛ ነበሩን? እርሱስ ከሌሎች የአምላክ እውነተኛ ነቢያት የተለየ፣ ራሳቸውን የሃይማኖት መሪዎች ካደረጉት ሰዎች በምንም መልኩ የማይመሳሰል ነበርን? ሐቁ እርሱ በሞተ በሦስተኛው ቀን ግልጽ ሊሆን ነው። አምላክ በዚህ ቀን ከሞት አስነሣውን? በዚህ መንገድ ኢየሱስ እውነት እንደተናገረና የአምላክ ብቸኛ ልጅ እንደነበረ ይረጋገጣል። (ሮሜ 1:3, 4) ከ500 የበለጡ ምሥክሮች ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ በሕይወት አይተውታል፤ ታማኝ ሐዋርያቱም ወደ ሰማይ ተመልሶ ሲሄድና በደመና ውስጥ ከዓይናቸው ሲሰወር ስለተመለከቱ የዓይን ምሥክሮች ነበሩ። (1 ቆሮ. 15:3–8፤ ሥራ 1:2, 3, 9) ብዙዎቹ ኢየሱስ ከሞት እንደተነሣ ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች ስለነበሩ ስለ ትንሣኤው ለሌሎች ለመናገር ሲሉ ሕይወታቸውን አሳልፈው እስከመስጠት ደርሰዋል።—ሥራ 4:18–33

አይሁዳውያን በአጠቃላይ ኢየሱስን እንደ መሲሕ አድርገው ያልተቀበሉት ለምን ነበር?

ዘ ኢንሳይክሎፔድያ ጁዳይካ እንዲህ ይላል:- “በሮማውያን ዘመን ይኖሩ የነበሩ አይሁዳውያን [መሲሑ] የአረማውያንን ቀንበር ለመስበርና እንደገና በምትቋቋመው የእስራኤል መንግሥት ላይ ለመግዛት አምላክ እንደሚያስነሣው አድርገው ያምኑ ነበር።” (ኢየሩሳሌም፣ 1971፣ ጥራዝ 11፣ ዓምድ 1407) እነርሱ የፈለጉት ከሮማውያን ቀንበር መላቀቅ ነበር። በ⁠ዳንኤል 9:24–27 ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው መሲሐዊ ትንቢት መሠረት በአንደኛው መቶ ዘመን እዘአ መሲሑ ይመጣል ብለው ይጠባበቁ የነበሩ አይሁዶች እንደነበሩ የአይሁድ ታሪክ ያረጋግጣል። (ሉቃስ 3:15) ይሁን እንጂ ይህ ትንቢት የመሲሑን መምጣት ‘ኃጢአትን ከመደምሰስ’ ጋር አያይዞታል። ኃጢአትን ለመደምሰስ ደግሞ መሲሕ እንደሚሞት ኢሳይያስ ምዕራፍ 53 ያሳያል። ይሁን እንጂ አይሁዳውያን በአጠቃላይ ለኃጢአታቸው የሚሞትላቸው ሰው እንደማያስፈልጋቸው ተሰምቷቸው ነበር። የአብርሃም ዘር በመሆናቸው ብቻ በአምላክ ፊት የጽድቅ አቋም እንዳላቸው ያምኑ ነበር። ኤ ራቢኒክ አንቶሎጂ የተባለ መጽሐፍ “አብርሃም የሠራው [መልካም ሥራ] እጅግ ታላቅ ስለሆነ እስራኤላውያን በዚህ ዓለም የሚፈጽሟቸውን ከንቱ ሥራዎችና የሚናገሯቸውን ውሸቶች በሙሉ ለማስተሰረይ ይችላል” ይላል። (ለንደን፣ 1938፣ ሲ ሞንቲፎር እና ኤች ሎዌ፣ ገጽ 676) አይሁዳውያን ኢየሱስን መሲሕ አድርገው ባለመቀበላቸው ስለ እርሱ አስቀድሞ የተነገረውን:- “እርሱ ተናቀ፣ እኛም አላከበርነውም” የሚለውን ትንቢት ፈጽመዋል።—ኢሳ. 53:3 ጁፓ

ሙሴ ከመሞቱ በፊት የእስራኤል ሕዝብ ከእውነተኛው አምልኮ ዘወር እንደሚልና ከዚህም የተነሣ መዓት እንደሚመጣባቸው ተንብዮ ነበር። (ዘዳግም 31:27–29⁠ን አንብብ) ይህ በተደጋጋሚ እንደደረሰ የመሳፍንት መጽሐፍ ያረጋግጣል። በነቢዩ ኤርምያስ ዘመን የእስራኤላውያን ብሔር በአጠቃላይ የታመነ ሆኖ ባለመገኘቱ በግዞት ወደ ባቢሎን እንዲወሰድ አድርጓል። አምላክ ኢየሩሳሌምና ቤተ መቅደሷ ዳግመኛ በ70 እዘአ በሮማውያን እንዲጠፉ ለምን ፈቀደ? አምላክ የእስራኤል ሕዝብ በእርሱ ይታመን በነበረበት ጊዜ ያደርግ እንደነበረው ከጥፋት ያላዳናቸው ምን በደል ቢፈጽሙ ነው? የኢየሱስን መሲሕነት አንቀበልም ያሉት በ70 እዘአ ከመጥፋታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ነበር።

ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ራሱ ነውን?

ዮሐ. 17:3 የ1980 ትርጉም:- “[ኢየሱስ ወደ አባቱ እንዲህ ብሎ ጸለየ:-] የዘላለም ሕይወትም፣ ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተንና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ነው።” (ኢየሱስ “እውነተኛ አምላክ” ያለው ራሱን ሳይሆን አባቱን እንደሆነ ልብ ማለት ይገባል።)

ዮሐ. 20:17:- “ኢየሱስም:- [መግደላዊት ማርያምን] ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ:- እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።” (ስለዚህ አብ ለመግደላዊት ማርያም አምላኳ እንደነበረ ሁሉ ከሞት ለተነሣው ኢየሱስም አምላኩ ነበር። በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አንድም ጊዜ ቢሆን አብ ወልድን “አምላኬ” ብሎ የጠራበት ቦታ አናገኝም።)

በተጨማሪ በገጽ 410, 415–417 ላይ “ሥላሴ” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።

ዮሐንስ 1:1 ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣልን?

ዮሐ. 1:1:- “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። [እንዲሁም ሪስ፣ ኪጄጀባዱዌይኖክስ፣ ኒአባ ]” ኒኢ እንዲህ ይላል:- “እግዚአብሔር የነበረውን ሁሉ ቃልም እንደዚያው ነበረ።” ሞፋት “ሎጎስ መለኮት ነበረ” ይላል። አት እና ሾድ “ቃል መለኮት ነበረ” ይላሉ። የኤዳ ኢንተርሊኒየር ትርጉም “ቃል አምላክ (a god) ነበረ” ይላል። አዓት “ቃል አምላክ (a god) ነበረ” ይላል፤ ኒቴኢ ተመሳሳይ አባባል ይጠቀማል።

ከእነዚህ ተርጓሚዎች አንዳንዶቹ “ቃል እግዚአብሔር ነበረ” ብለው ያልተረጎሙት በግሪክኛው ጽሑፍ ውስጥ ምን ያስተዋሉት ነገር ቢኖር ነው? በመጀመሪያው ቴኦስ (አምላክ ወይም እግዚአብሔር) ላይ ዘ (the) የሚለው ጠቃሽ አመልካች ሲጨመር በሁለተኛው ቴኦስ ላይ ግን አልተጨመረም። (በግሪክኛው ዐረፍተ ነገር ውስጥ) ይህ ቃል ጠቃሽ አመልካች ሲጨመርበት ማንነትን ወይም አንድን የተወሰነ አካል የሚያመለክት ሲሆን (ጠቃሽ አመልካች ያልተጨመረበት) ኢርቱዕ ተሳቢ ሆኖ በሚያገለግልበት ጊዜ ግን የአንድን አካል ባሕርይ ወይም ጠባይ ያመለክታል። ስለዚህ ጥቅሱ ቃል (ኢየሱስ) አምላክ መሰል፣ መለኮት፣ አምላክ (a god) እንደነበረ ያመለክታል እንጂ አብሮት ከነበረው እግዚአብሔር ጋር አንድ መሆኑን አያመለክትም። (አዓት የ1984 ባለማጣቀሻ እትም፣ ገጽ 1579)

ሐዋርያው ዮሐንስ፣ ዮሐንስ 1:1⁠ን ሲጽፍ ምን ለመግለጽ ፈልጎ ነበር? ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ወይም ምናልባት ኢየሱስ ከአብ ጋር አንድ አምላክ እንደሆነ መግለጹ ነበርን? በዚያው ምዕራፍ ቁጥር 18 ላይ ዮሐንስ እንዲህ በማለት ጽፏል:- “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ [“ማንም ሰው” ኪጄ፣ ዱዌይ ] የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ [“አንድያ ልጅ ሆኖ የተወለደው አምላክ (god)” አዓት ] ተረከው።” ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየው ሰው ነበር? አዎ! በእርግጥ ሰዎች አይተውታል። እንግዲያውስ ዮሐንስ እዚህ ላይ ኢየሱስ እግዚአብሔር ነበር ማለቱ ነውን? አይደለም። ዮሐንስ በወንጌሉ መጨረሻ አካባቢ ጉዳዩን እንዲህ በማለት አጠቃልሎታል:- “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ [እግዚአብሔር እንደሆነ አይልም] ታምኑ ዘንድ . . . ይህ ተጽፎአል።”—ዮሐ. 20:31

በዮሐንስ 20:28 ላይ የተመዘገበው የቶማስ አነጋገር ኢየሱስ በእውነት እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ያረጋግጣልን?

ዮሐንስ 20:28 እንዲህ ይላል:- “ቶማስም:- ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።”

ቶማስ ሊናገር የፈለገው ኢየሱስ “አምላክ” መሆኑን ከነበረ አምላኬ ብሎ መጥራቱ የሚያከራክርበት ምንም ምክንያት የለም። ይህ አባባል ኢየሱስ ራሱ ከመዝሙር መጽሐፍ ጠቅሶ ኃያላን ሰዎችና ፈራጆች “አማልክት” እንደተባሉ ከገለጸው ጋር ይስማማል። (ዮሐ. 10:34, 35፤ መዝ. 82:1–6) በእርግጥ ክርስቶስ ከእነዚህ ሰዎች በጣም ከፍ ያለ ሥልጣን አለው። በይሖዋ ዘንድ ልዩ የሆነ ቦታና ሥልጣን ስላለው በ⁠ዮሐንስ 1:18 (አዓት ) ላይ “አንድያ ልጅ ሆኖ የተወለደ አምላክ” ተብሎ ተጠርቷል። (በተጨማሪ ሮዘ እና ባይ ተመልከት።) እንዲሁም ኢሳይያስ 9:6 ሁሉን ቻይ አምላክ ሳይሆን “ኃያል አምላክ” መሆኑን በመግለጽ ተንብዮለታል። ይህ ሁሉ በ⁠ዮሐንስ 1:1 ላይ (አዓት፣ አት ) ኢየሱስ “አምላክ (a god)” ወይም “መለኮት” ከመባሉ ጋር ይስማማል።

ከጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ ከዚህ ትክክለኛ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ይረዳናል። ኢየሱስ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ “ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንክ” በማለት ወደ አባቱ ሲጸልይ ቶማስ ሰምቶ ነበር። (ዮሐ. 17:3 አዓት ) ኢየሱስ ከትንሣኤው በኋላ ለሐዋርያቱ፣ ለቶማስም ጭምር፣ “ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ” የሚል መልእክት ልኮላቸው ነበር። (ዮሐ. 20:17) ሐዋርያው ዮሐንስ፣ ቶማስ ከሞት የተነሣውን ክርስቶስን በተመለከተና በነካው ጊዜ የሆነውን ነገር ከጻፈ በኋላ “ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል” ብሎአል። (ዮሐ. 20:31) አንድ ሰው ከቶማስ ንግግር ኢየሱስ ራሱ ‘ብቻውን እውነተኛ የሆነው አምላክ’ ወይም የሥላሴ አንዱ ክፍል የሆነው “እግዚአብሔር ወልድ” ነው በማለት ቢደመድም ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን (በቁጥር 17 ላይ) እንዲሁም ሐዋርያው ዮሐንስ በግልጽ የተናገረውን መደምደሚያ (ቁጥር 31⁠ን) እንደገና መመልከት ያስፈልገዋል።

ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ እግዚአብሔር እንደነበረ ማቴዎስ 1:23 ያሳያልን?

ማቴ. 1:23:- “እነሆ፣ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል . . . ትርጓሜውም:- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር [“አምላክ ከእኛ ጋር ነው” ኒኢ ] የሚል ነው።”

የይሖዋ መልአክ ኢየሱስ እንደሚወለድ ባስታወቀ ጊዜ የሚወለደው ልጅ ራሱ እግዚአብሔር ነው ብሏልን? አላለም። “ታላቅ ይሆናል፣ የልዑል ልጅ ም ይባላል” ነው ያለው። (ሉቃስ 1:32, 35፤ ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) ኢየሱስ ራሱ “የአምላክ ልጅ ” እንደሆነ እንጂ እርሱ ራሱ ሁሉን የሚችለው አምላክ እንደሆነ ተናግሮ አያውቅም። (ዮሐ. 10:36፤ ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) ኢየሱስን ወደ ዓለም የላከው አባቱ ነው። በመሆኑም አምላክ በዚህ አንድያ ልጁ አማካኝነት ከሰዎች ጋር ሆኖአል።—ዮሐ. 3:17፤ 17:8

በዕብራይስጥ ስሞች ላይ አምላክ የሚለውን ቃል ወይም የአምላክን የግል ስም ምኅጻረ ቃል መጨመሩ ያልተለመደ ነገር አልነበረም። ለምሳሌ ኤልያታ ማለት “አምላክ መጣ”፤ ኢዩ ማለት “ይሖዋ እርሱ ነው”፤ ኤልያስ “ይሖዋ አምላኬ ነው” የሚሉ ትርጉሞች አሏቸው። ነገር ግን ከእነዚህ ስሞች አንዱም ቢሆን የስሙ ባለቤት አምላክ እንደነበረ አላመለከቱም።

የዮሐንስ 5:18 ትርጉም ምንድን ነው?

ዮሐ. 5:18:- “ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ:- እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፣ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።”

ኢየሱስ አምላክ አባቱ እንደሆነ በመናገር ራሱን ከአምላክ ጋር እኩል ለማድረግ ሞክሯል ብለው ያሰቡት ያላመኑት አይሁዶች ነበሩ። ኢየሱስ እግዚአብሔር አባቱ እንደሆነ ቢናገርም ከአምላክ ጋር እኩል ነኝ አላለም። ለአይሁዳውያን “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ አይችልም” በማለት በቀጥታ መልስ ሰጥቷቸዋል። (ዮሐ. 5:19፤ በተጨማሪ ዮሐንስ 14:28፤ ዮሐንስ 10:36⁠ን ተመልከት።) ኢየሱስ ሰንበትን ሽሯል ያሉትም እነዚያው የማያምኑ አይሁዶች ነበሩ፤ ነገር ግን እዚህም ላይ ቢሆን ተሳስተው ነበር። ኢየሱስ ሕጉን አሟልቶ ጠብቋል፤ “በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል” በማለትም ተናግሯል።—ማቴ. 12:10–12

ኢየሱስ የሚሰገድለት መሆኑ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣልን?

በ⁠ዕብራውያን 1:6 ላይ መላእክት ለኢየሱስ “ይስገዱ” ተብለው ታዝዘዋል። ሪስ፣ ቱኢቨ፣ ኪጄ፣ ጀባ እና ኒአባ ከዚሁ ጋር በሚመሳሰል መንገድ ተርጉመውታል። አዓት ላይ “ይስገዱ” ይላል። ሪስ፣ ቱኢቨ፣ ኪጄ በ⁠ማቴዎስ 14:33 ላይ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን “አመለኩት” ይላሉ። ሌሎች ትርጉሞች “አክብሮት አሳዩት” (ኒአባ )፣ “በፊቱ ወድቀው ሰገዱ” (ጀባ )፣ “ከእግሩ ላይ ወደቁ” (ኒኢ )፣ “ሰገዱለት” (አዓት ) ይላሉ።

“መስገድ” ተብሎ የተተረጐመው የግሪክኛ ቃል ፕሮስካይኒኦ ነው። ኤ ግሪክ ኢንግሊሽ ሊክሲከን ኦፍ ዘ ኒው ቴስታመንት ኤንድ አዘር ኧርሊ ክርስቲያን ሊትረቸር (የአዲስ ኪዳንና የሌሎች የጥንት የክርስትና ጽሑፎች ግሪክኛ–እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ) እንዲህ ይላል:- “ቃሉ ጎንበስ ብሎ የአንድን ሰው ጫማ ወይም ልብስ ወይም መሬቱን የመሳምን ባሕል ለማመልከት ያገለግል ነበር።” (ቺካጐ፣ 1979፣ ባወር፣ አርንድት፣ ጊንግሪች፣ ዳንከር፤ ሁለተኛው የእንግሊዝኛ እትም፣ ገጽ 716) ይህ ቃል በ⁠ማቴዎስ 14:33 ላይ ደቀ መዛሙርቱ በኢየሱስ ፊት ያደረጉትን ለመግለጽ፤ በ⁠ዕብራውያን 1:6 ላይ መላእክቱ ለኢየሱስ ማድረግ ያለባቸውን ለማመልከት፤ በ⁠ዘፍጥረት 22:5 በግሪክኛው ሴፕቱጀንት (ሰባ ) ትርጉም ላይ አብርሃም ለይሖዋ ያደረገውን ለመግለጽና በ⁠ዘፍጥረት 23:7 አብርሃም በጊዜው ከነበረው ልማድ ጋር በመስማማት በአካባቢው ይኖሩ ለነበሩት ሰዎች ያደረገውን ለመግለጽ አገልግሏል። በሰባ ሊቃናት ውስጥ በ⁠1 ነገሥት 1:23 ላይ ነቢዩ ናታን ወደ ንጉሥ ዳዊት በቀረበ ጊዜ ያደረገውን ለመግለጽ ያገለገለው ይኸው ቃል ነው።

በ⁠ማቴዎስ 4:10 ላይ ኢየሱስ “ለጌታ [“ለይሖዋ” አዓት] ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ [ፕሮስካይኒኦ ከሚለው የተተረጎመ]” በማለት ተናግሯል። (ኢየሱስ እዚህ ላይ የጠቀሰው በ⁠ዘዳግም 6:13 ላይ የሚገኘውን የአምላክን የግል ስም የሚወክሉትን ቴትራግራማተን ነው።) በዚህ መሠረት ለአምላክ ብቻ የሚቀርበው ፕሮስካይኒኦ ልዩ በሆነ የልብና የአእምሮ ዝንባሌ የሚቀርብ አክብሮት ነው።

ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት እርሱ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ያረጋግጣሉን?

ሥራ 10:34, 38:- “ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ:- . . . እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፣ . . . እርሱም መልካም እያደረገና ለዲያብሎስ የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና።” (ስለዚህ ጴጥሮስ የተመለከታቸውን ተአምራት መሠረት በማድረግ ኢየሱስ አምላክ ነው አላለም፤ ከዚህ ይልቅ የተናገረው አምላክ ኢየሱስ ጋር እንደነበረ ነው። ከማቴዎስ 16:16, 17 ጋር አወዳድር።)

ዮሐ. 20:30, 31:- “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት [“ተአምራት” ቱኢቨ፣ ኖክስ ] በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።” (ስለዚህ ኢየሱስ ካደረጋቸው ተአምራት የምንደርስበት ትክክለኛ ድምዳሜ እርሱ “ክርስቶስ”፣ መሲሕ፣ “የአምላክ ልጅ” እንደሆነ ነው። “የእግዚአብሔር ልጅ” የሚለው አገላለጽ “እግዚአብሔር ወልድ” ከሚለው በጣም የተለየ ነው።)

ከክርስትና ዘመን በፊት የነበሩት እንደ ኤልያስና ኤልሣዕ የመሳሰሉት ነቢያት ኢየሱስ ካደረጋቸው ጋር የሚመሳሰሉ ተአምራት ፈጽመዋል። ይሁን እንጂ ተአምራት ማድረጋቸው አምላክ እንደነበሩ አያረጋግጥም።

ኢየሱስ “በብሉይ ኪዳን” ውስጥ ከተጠቀሰው ይሖዋ ጋር አንድ ነውን?

ገጽ 198, 199 ላይ “ይሖዋ” በሚለው ዋና ርዕስ ሥር ተመልከት።

ለመዳን የሚያስፈልገው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ብቻ ነውን?

ሥራ 16:30–32:- “ጌቶች ሆይ፣ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? አላቸው። እነርሱም [ጳውሎስና ሲላስ]:- በጌታ ኢየሱስ እመን፣ አንተና ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ አሉት። ለእርሱና በቤቱ ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል [ኒአባ፣ ጀባ እና ኒኢ የግርጌ ማስታወሻ፤ “የእግዚአብሔርን መልዕክት” አት፤ “የጌታን ቃል” ሪስ ] ተናገሩአቸው።” (ይህ ሰው ‘በጌታ ኢየሱስ ማመኑ’ ከልቡ እንደሚያምን መናገሩ ብቻ ነበርን? ጳውሎስ እምነት ብቻ እንደማይበቃ፣ እውቀትና የአምላክን ቃል መቀበል ጭምር እንደሚያስፈልጉ አመልክቶአል። ይህንንም ጳውሎስና ሲላስ ለእስር ቤት ዘበኛው ሰብከውለታል። አንድ ሰው ኢየሱስ ያመለከውን አምላክ ካላመለከ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባቸው ያስተማረውን ትምህርት በተግባር ካላዋለ ወይም ኢየሱስ ተከታዮቹ እንዲሠሩ ያዘዛቸውን ሥራ የማይሠራ ከሆነ ይህ ሰው በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት እውነተኛ ሊሆን ይችላልን? መዳን የሥራችን ደሞዝ ሆኖ ሊከፈለን አይችልም። መዳን የሚገኘው በኢየሱስ ሰብዓዊ ሕይወት መሥዋዕታዊ ዋጋ በማመን ነው። ችግር ሊያስከትልብን የሚችል ቢሆንም አኗኗራችን አለን ከምንለው እምነት ጋር መስማማት ይኖርበታል። በማቴዎስ 10:22 ላይ ኢየሱስ “እስከ መጨረሻ የሚጸና . . . እርሱ ይድናል” ብሏል።)

ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት በሰማይ ይኖር ነበርን?

ቆላ. 1:15–17:- “እርሱም [ኢየሱስ] የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ . . . ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው።”

ዮሐ. 17:5:- “[ኢየሱስ ሲጸልይ እንዲህ አለ:-] አባት ሆይ፣ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።” (በተጨማሪ ዮሐንስ 8:23)

ኢየሱስ ሥጋዊ አካሉን ወደ ሰማይ ይዞት ሄዷልን?

1 ቆሮ. 15:42–50:- “የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው። በመበስበስ ይዘራል፣ ባለመበስበስ ይነሣል፤ . . . ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፣ መንፈሳዊ አካል ይነሣል። . . . እንዲሁ ደግሞ:- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም [እንደ መጀመሪያው አዳም ፍጹም ሰው የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ] ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። . . . ወንድሞች ሆይ፣ ይህን እላለሁ:- ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፣ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም።” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።)

1 ጴጥ. 3:18:- “ክርስቶስ . . . አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ [“መንፈስ” ኒኢ፣ አት፣ ጀባ፣ ዱዌይ ] ግን ሕያው ሆነ።” (ገጽ 333, 334⁠ን ተመልከት)

ምሳሌ:- አንድ ሰው ለአንድ ጓደኛው ዕዳውን ከከፈለለት በኋላ የከፈለውን ገንዘብ መልሶ ቢወስድ ዕዳው አልተከፈለም። በተመሳሳይ ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ የቤዛውን ዋጋ ለመክፈል መሥዋዕት የሆነውን ሥጋና ደም መልሶ ከወሰደ ታማኝ ሰዎችን ከኃጢአት ዕዳ ለማላቀቅ ያደረገው ዝግጅት ምን ውጤት ይኖረዋል?

ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ ሥጋዊ መልክ ይዞ ለደቀ መዛሙርቱ መታየቱ እውነት ነው። ይሁን እንጂ ደቀ መዛሙርቱ በተለያዩ ጊዜያት ወዲያው እንዳዩት ኢየሱስ መሆኑን ሊያውቁ ያልቻሉት ለምን ነበር? (ሉቃስ 24:15–32፤ ዮሐ. 20:14–16) አንድ ጊዜ ለቶማስ ሲል በእጆቹ ላይ በምስማር የተወጋበት ምልክት፣ ጎኑ ላይ በጦር የተወጋበት ቁስል ያለበትን አካል ለብሶ ታይቷል። ታዲያ በዚያን ጊዜ በሮቹ ተቆልፈው ሳሉ በድንገት በመካከላቸው እንዴት ሊገኝ ቻለ? (ዮሐ. 20:26, 27) ባለፉት ዘመናት መላእክት ለሰዎች ለመታየት ሲሉ ያደርጉት እንደነበረው ኢየሱስም በእነዚህ አጋጣሚዎች በሥጋዊ አካል መልክ ታይቷል። ኢየሱስ ከሙታን በተነሣ ጊዜ የኢየሱስን ሥጋዊ አካል ከቦታው ማስወገድ ለአምላክ አስቸጋሪ አይሆንበትም። አምላክ የኢየሱስን ሥጋዊ አካል በመቃብር ውስጥ አልተወውም። (ይህንንም ያደረገው ኢየሱስ በእርግጥ እንደተነሣ የደቀ መዛሙርቱን እምነት ለማጠናከር ሲል መሆኑን ከሁኔታው ለመረዳት ይቻላል።) ከተልባ እግር የተሠራው የተከፈነበት ልብስ በመቃብሩ ውስጥ ቀርቶ ነበር፤ ሆኖም ከሞት የተነሣው ኢየሱስ ሁልጊዜ ይታይ የነበረው ሙሉ በሙሉ ልብስ ለብሶ ነበር።—ዮሐ. 20:6, 7

ኢየሱስ ክርስቶስ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነውን?

ሚካኤል የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው አምስት ጊዜ ብቻ ነው። ይህን ስም የያዘው አስደናቂ መንፈሳዊ ፍጡር “ከዋነኞቹ አለቆች [“መሳፍንት” አዓት ] አንዱ”፤ “ስለ ሕዝብህ [ስለ ዳንኤል ሕዝብ] የሚቆመው ታላቁ አለቃ [“መስፍን” አዓት ]”፣ “የመላእክት አለቃ” ተብሎ ተጠርቷል። (ዳን. 10:13፤ 12:1፤ ይሁዳ 9) ሚካኤል ማለት “እንደ አምላክ ያለ ማን ነው?” ማለት ነው። ይህ ስም ሚካኤል የይሖዋን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥና የአምላክን ጠላቶች ለማጥፋት በሚወሰደው እርምጃ ግንባር ቀደም እንደሚሆን በግልጽ ያሳያል።

በ⁠1 ተሰሎንቄ 4:16 ላይ ኢየሱስ ትንሣኤ እንዲጀመር የሚሰጠው ትእዛዝ “በመላእክት አለቃ ድምፅ” ተብሎ ተገልጿል። ይህ የመላእክት አለቃ ሚካኤል መሆኑን ይሁዳ 9 ይገልጻል። ይህን የትእዛዝ ድምፅ ከኢየሱስ ያነሰ ሥልጣን ያለው ፍጡር ያስተላልፋል ብሎ ማሰብ ተገቢ ይሆናልን? እንግዲያውስ ምክንያታዊ ሆነን ነገሩን ከተመለከትን የመላእክት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ “የመላእክት አለቃ” የሚለው አገላለጽ ብዙ ቁጥር እንደሚያመለክት ሆኖ የገባበት ቦታ አለመኖሩ ይህ ቃል የሚያመለክተው እርሱን ብቻ መሆኑን ያሳያል።)

ራእይ 12:7–12 ክርስቶስ ንጉሣዊ ሥልጣኑን በሚቀበልበት ጊዜ ስለሚሆነው ነገር ሲናገር ሚካኤልና መላእክቱ ከሰይጣን ጋር እንደሚዋጉና ሰይጣንንና ክፉ መላእክቱን ከሰማይ እንደሚወረውሯቸው ይናገራል። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የሰማይ ሠራዊትን በመምራት ከዓለም መንግሥታት ጋር እንደሚዋጋ ተገልጿል። (ራእይ 19:11–16) “የዚህ ዓለም ገዥ” በማለት በገለጸው በሰይጣን ዲያብሎስ ላይ እርምጃ የሚወስደው ኢየሱስ መሆኑ ምክንያታዊ አይደለምን? (ዮሐ. 12:31) ዳንኤል 12:1 ሚካኤል እርምጃ ለመውሰድ ‘መቆሙን’ “ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን” ከተባለለት ጊዜ ጋር ያያይዘዋል። ክርስቶስ ሰማያዊ ፍርድ አስፈጻሚ ሆኖ በአሕዛብ ላይ የሚወስደው እርምጃ በእርግጥም ይህን የመሰለ የመከራ ዘመን ይሆናል። የአምላክ ልጅ ወደ መሬት ከመምጣቱ በፊት ይታወቅ የነበረው ሚካኤል ተብሎ ሲሆን ወደ ሰማይ ከተመለሰበት ጊዜ ጀምሮ ተጨማሪ ክብር የተቀዳጀ የአምላክ መንፈሳዊ ልጅ ሆኖ በሚኖርበት በሰማይም የሚታወቀው በዚሁ ስም እንደሚሆን ማስረጃው ያሳያል።

አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

‘እናንተ በኢየሱስ አታምኑም’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘እርስዎ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰው መሆንዎን ከጥያቄዎ መረዳት ይቻላል። እኔም አምናለሁ። ይህ ባይሆን ዛሬ በርዎን አላንኳኳም ነበር።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘በኢየሱስ ማመን በእርግጥ አስፈላጊ እንደሆነ ታትመው በሚወጡት ጽሑፎቻችን ላይ ጐላ ተደርጎ ተገልጿል። (ለማበርከት ከያዝከው መጽሐፍ ከአንዱ ላይ ተስማሚ የሆነውን ምዕራፍ አውጥተህ ኢየሱስ በንጉሥነቱ ምን ዓይነት የሥራ ድርሻ እንደሚኖረው አብራራ። ወይም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ገጽ 2 ላይ ያለውን የመጽሔቱን ዓላማ አንብብላቸው።)’

ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ለምን እንዲህ እንደተሰማዎት ብጠይቅዎት?’

ሌላ አማራጭ:- ‘ይህን ያሉት ከሰው ሰምተው ይመስለኛል። ይሁን እንጂ በኢየሱስ አታምኑም የሚለው አባባል እውነት አይደለም፤ እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በጣም ጠንካራ እምነት አለን።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ሆኖም ሰዎች ስለ ኢየሱስ የሚናገሩትን ነገር ሁሉ አንቀበልም። ለምሳሌ አንዳንዶች ኢየሱስ ጥሩ ሰው ብቻ እንጂ የአምላክ ልጅ አልነበረም ይላሉ። ይህን አንቀበልም፤ እርስዎስ? . . . መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ብሎ አያስተምርም።’ (2) ‘አንዳንድ ሃይማኖቶች ኢየሱስ በአባቱ ዘንድ ስላለው ቦታ የተናገረውን በመቃረን የሚያስተምሩትንም ትምህርት አንቀበልም። (ዮሐ. 14:28) ዛሬ አባቱ የሁላችንንም ሕይወት የሚነካ የመግዛት ሥልጣን ለኢየሱስ ሰጥቶታል። (ዳን. 7:13, 14)’

‘ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ትቀበለዋለህን?’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንዲህ ይላል:- . . . (ሥራ 4:12⁠ን ጥቀስ።) ይህንን አምናለሁ። ነገር ግን ከዚህ ጋር አብሮ የሚሄድ ከባድ ኃላፊነት እንዳለም ተገንዝቤአለሁ። ይህስ ምንድን ነው? በእርግጥ በኢየሱስ የማምን ከሆነ የማምነው ሁኔታው እስከተመቸኝ ድረስ ብቻ ሊሆን አይችልም።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘መሥዋዕት የሆነው ፍጹም ሕይወቱ የኃጢአት ይቅርታ አስገኝቶልናል። ስለዚህ ክርስቲያን እንደመሆናችን ስላሉብን ኃላፊነቶች እርሱ የሰጠንን መመሪያዎች መከተል አስፈላጊ እንደሆነም አውቃለሁ። (ሥራ 1:8፤ ማቴ. 28:19, 20)’

ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘(ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለሚያምኑበትም ሁሉ ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን ካረጋገጥህለት በኋላ . . . ) ኢየሱስ ጥንት ላደረጋቸው ነገሮች ብቻ ሳይሆን አሁንም ለሚያደርጋቸው ነገሮች አድናቆት ማሳየት ያስፈልገናል። (ማቴ. 25:31–33)’

‘ኢየሱስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብዬዋለሁ’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ዛሬ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ያደረገልንን ነገር ከቁም ነገር ስለማይቆጥሩ እርስዎ በኢየሱስ እንደሚያምኑ በመስማቴ ደስ ብሎኛል። በ⁠ዮሐንስ 3:16 ላይ ያለውን ጥቅስ በሚገባ እንደሚያውቁት አልጠራጠርም፤ አይደለም? . . . እነዚህ ሰዎች ለዘላለም የሚኖሩት የት ነው? አንዳንዶች በሰማይ ከክርስቶስ ጋር ይሆናሉ። ነገር ግን ሁሉም ጥሩ ሰዎች ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል እንዴ? (ማቴ. 6:10፤ 5:5)’