በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የልደት ቀን

የልደት ቀን

ፍቺ:- አንድ ሰው የተወለደበት ቀን ወይም ልደቱ የሚከበርበት ቀን የልደት ቀን ይባላል። በአንዳንድ ሥፍራዎች የልደት ቀን በተለይም ሕፃናት የተወለዱበት ቀን በድግስና ስጦታ በመስጠት ይከበራል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማድ አይደለም።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ልደት ቀን መከበር የሚናገሩት ጥቅሶች ነገሩ ጥሩ ልማድ መሆኑን ያመለክታሉን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልደት ቀን መከበር የሚገልጸው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው:-

ዘፍ. 40:20–22:- “በሦስተኛውም ቀን ፈርዖን የተወለደበት ቀን ነበረ፣ . . . ግብር አደረገ . . . የጠጅ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ ስፍራው መለሰው፣ . . . የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ ሰቀለው።”

ማቴ. 14:6–10:- “ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፣ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤ ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት። እርስዋም በእናትዋ ተመክራ:- የመጥምቁ የዮሐንስን ራስ በወጭት ስጠኝ አለችው። . . . ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።”

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ የሚገኝ ማናቸውም ነገር ያለ ምክንያት አይጻፍም። (2 ጢሞ. 3:16, 17) የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክ ቃል የልደት ቀን ማክበርን እንደ ጥሩ ልማድ አድርጎ እንደማያቀርበው ስለሚገነዘቡ ከዚህ አድራጎት ይርቃሉ።

የጥንት ክርስቲያኖችና በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች የልደት ቀን አከባበርን እንዴት ይመለከቱት ነበር?

የልደት ቀንን የማክበር ሐሳብ በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ አይታወቅም ነበር።”ዘ ሂስትሪ ኦቭ ዘ ክርስቲያን ሪሊጅን ኤንድ ቸርች ዲዩሪንግ ዘ ስሪ ፈርስት ሴንቸሪስ (የክርስትና ሃይማኖትና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በመጀመሪያዎቹ ሦስት መቶ ዘመናት)፣ (ኒው ዮርክ፣ 1848)፣ አውጉስተስ ኒያንደር (በሄነሪ ጆን ሮስ የተተረጐመ)፣ ገጽ 190

“በኋለኞቹ ዘመናት ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች የልደት ቀን ማክበርን የጣዖት አምልኮ ክፍል አድርገው ይመለከቱት ነበር። ይህም አመለካከታቸው ትክክል መሆኑ የልደት ቀኖች በሚከበሩባቸው ጊዜያት ሲፈጸሙ በሚመለከቱአቸው ነገሮች ሊረጋገጥ ይችል ነበር።”—ዘ ኢምፔሪያል ባይብል ዲክሽነሪ (ለንደን፣ 1874) በፓትሪክ ፌርቤን የተዘጋጀ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 225

ከልደት ቀን አከባበር ጋር ግንኙነት ያላቸው የታወቁ ልማዶች ከየት የተገኙ ናቸው?

“በዛሬው ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች የልደት በዓላቸውን የሚያከብሩባቸው የተለያዩ ልማዶች ረጅም ታሪክ ያላቸው ናቸው። መነሻቸው ጥንቆላና ሃይማኖት ነው። በጥንት ዘመን በልደት ቀኖች እንኳን ደስ አለህ የሚባለው፣ ስጦታ የሚሰጠውና ሻማ በማብራት ቀኑ የሚከበረው ልደቱ የሚከበርለትን ሰው ከአጋንንት ይጠብቀዋል፣ ለሚመጣው ዘመንም የሕይወት ዋስትና ይሰጠዋል የሚል አስተሳሰብ ስለነበረ ነው። . . . እስከ አራተኛ መቶ ዘመን ድረስ የክርስትና እምነት የልደት ቀንን ማክበር የአረማውያን ልማድ እንደሆነ በመቁጠር አልተቀበለውም ነበር።”—እሽቨቢሸ ሳይቱንግ (ሳይት ኡንድ ቬልት በተባለው መጽሔት ላይ ተጨምሮ የወጣ)፣ ሚያዝያ 3/4፣ 1981፣ ገጽ 4

“ግሪኮች እያንዳንዱ ሰው በሚወለድበት ጊዜ በቦታው ተገኝቶ የሚጠብቀውና በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ከክፉ ነገር የሚከላከልለት አንድ መንፈስ ወይም ዴሞን አለ ብለው ያምኑ ነበር። ይህ መንፈስ ሰውዬው በተወለደበት ቀን ከተወለደ አንድ አምላክ ጋር ምሥጢራዊ ግንኙነት አለው። ሮማውያንም ይህን ሐሳብ ተቀብለውት ነበር። . . . እንደ ውቃቢ አምላክ፣ የክርስትና እናትና፣ ጠባቂ መልአክ የመሰሉት እምነቶች የመጡት ከዚህ አስተሳሰብ ነው። የበራ ሻማ በኬክ ላይ የማስቀመጥ ልማድ የተጀመረው በግሪኮች ነው። . . . እንደ ጨረቃ ክብ ሆነው ከማር የተዘጋጁ ኬኮች የበራ ሻማ ተደርጎባቸው በ[አርጤምስ] ቤተ መቅደስ መሠዊያ ላይ ይቀመጡ ነበር። . . . የልደት ቀን ሻማ ልዩ የሆነ ምኞትን የማስፈጸም ምትሃታዊ ኃይል አለው ብለው ያምኑ ነበር። . . . የሰው ልጅ ለአምላኮቹ መሠዊያ መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ለሻማዎችና ለመሥዋዕት እሳት ልዩ የሆነ ምሥጢራዊ ትርጉም ሲሰጥ ቆይቷል። ስለዚህ በልደት ቀን የሚበሩት ሻማዎች ልደቱን ለሚያከብረው ልጅ ክብርና ሞገስ የሚያስገኝለት ሲሆን ጥሩ ዕድልም ያመጡለታል ተብሎ ይታመን ነበር። . . . በልደት ቀን የሚሰጠው የመልካም ምኞት መግለጫም የዚህ በዓል ዋነኛ ክፍል ነው። . . . ይህ ልማድ በመጀመሪያ የመነጨው ከጥንቆላ ሥራ ነው። . . . ልደቱን የሚያከብረው ሰው በዚያ ቀን ወደ መንፈሳዊው ዓለም በጣም ስለሚጠጋ በልደት ቀን የሚሰጠው የመልካም ምኞት መግለጫ ጥሩ ወይም መጥፎ ነገር ለማምጣት የሚያስችል ኃይል አለው።”—ዘ ሎር ኦቭ በርዝዴይስ (የልደት አከባበር ልማድ)፣ (ኒው ዮርክ፣ 1952)፣ ራልፍና አደሊን ሊንተን፣ ገጽ 8, 18–20

አብሮ ለመብላት፣ ለመጠጣትና ለመጫወት ሲባል ቤተሰቦችና ጓደኞች በሌላ ጊዜ መሰባሰባቸው ስህተት የለበትም

መክ. 3:12, 13:- “ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ። ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።”

በተጨማሪ 1 ቆሮንቶስ 10:31⁠ን ተመልከት።