በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ፀረ ክርስቶስ

ፀረ ክርስቶስ

ፍቺ:- ፀረ ክርስቶስ ማለት ክርስቶስን የሚቃወም ወይም የክርስቶስ ምትክ ሆኖ የቆመ ማለት ነው። ይህ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገረውን የሚክዱትን፣ መንግሥቱን የሚቃወሙትንና በተከታዮቹ ላይ መከራ የሚያደርሱትን ሰዎች ያመለክታል። እንዲሁም ቃሉ ክርስቶስን እንወክላለን ብለው በውሸት የሚናገሩትን ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ብሔራት ወይም ሳይገባቸው የመሲሑን ቦታ ለራሳቸው የሚያደርጉትን ሁሉ ይጨምራል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ስለ አንድ ፀረ ክርስቶስ ብቻ ነውን?

1 ዮሐ. 2:18:- “ልጆች ሆይ፣ መጨረሻው ሰዓት ነው፣ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህ የመጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።”—ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

2 ዮሐ. 7:- “ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።” (በ⁠1 ዮሐንስ 2:18 ላይ “ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች” የተባሉት እዚህ ላይ “የክርስቶስ ተቃዋሚ” በሚል ነጠላ ስም ተጠቃለው እንደተጠሩ ልብ በል።)

ፀረ ክርስቶስ ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚመጣው ገና ወደፊት ነውን?

1 ዮሐ. 4:3:- “ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፣ አሁንም እንኳ በዓለም አለ። ” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) (ይህ የተጻፈው እዘአ በአንደኛው መቶ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ነው።)

1 ዮሐ. 2:18:- “አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) (ዮሐንስ “መጨረሻው ሰዓት” ያለው የሐዋርያት ዘመን ሊያበቃ መቃረቡን ለማመልከት ነበር። በዚህ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ሞተው አልቀው ነበር። ዮሐንስ ራሱም በጣም ሸምግሎ ነበር።)

ፀረ ክርስቶስ እንደሆኑ ተለይተው ከሚታወቁት ጥቂቶቹ:-

ኢየሱስ እውነተኛ መሲሕ መሆኑን የሚክዱ ሰዎች

1 ዮሐ. 2:22:- “ክርስቶስ [ወይም መሲሕ፣ ወይም የተቀባ] አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? . . . ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።”

ኢየሱስ ብቸኛው የአምላክ ልጅ መሆኑን የሚክዱ ሁሉ

1 ዮሐ. 2:22:- “አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።”

ከ⁠ዮሐንስ 10:36 እና ሉቃስ 9:35 ጋር አወዳድር።

ከእምነት ያፈነገጡ ከሃዲዎች

1 ዮሐ. 2:18, 19:- “ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ . . . ከእኛ ዘንድ ወጡ፣ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም።”— ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

የክርስቶስን እውነተኛ ተከታዮች የሚቃወሙ

ዮሐ. 15:20, 21:- “እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ . . . ዳሩ ግን . . . ይህን ሁሉ ስለ ስሜ ያደርጉባችኋል።”

የክርስቶስን ንግሥና የሚቃወሙ ወይም መሲሑ የሚፈጽማቸውን ነገሮች እንፈጽማለን ብለው በሐሰት የሚናገሩ ግለሰቦችና ብሔራት

መዝ. 2:2:- “የምድር ነገሥታት ተነሡ፣ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ [ወይም በክርስቶስ] ላይ . . . ተማከሩ።”

በተጨማሪ ራእይ 17:3, 12–14፤ 19:11–21⁠ን ተመልከት።

ማቴ. 24:24:- “ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፣ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።”