በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ፅንስ ማስወረድ

ፅንስ ማስወረድ

ፍቺ:- ፅንስ ማስወረድ ማለት ከማኅፀን ውጭ ለመኖር የማይችለውን ሽል ወይም ፅንስ ከማኅፀን ማስወጣት ማለት ነው። በአደጋ ወይም በሰብዓዊ አለፍጽምና ምክንያት ድንገተኛ ውርጃ ሊያጋጥም ይችላል። የማይፈለግ ልጅ እንዳይወለድ ሲባል ሆን ብሎ ፅንስ ማስወረድ ግን የሰውን ሕይወት በራስ ፈቃድ ማጥፋት ማለት ነው።

የሰው ሕይወት ምንጭ ማን መሆኑን ማወቃችን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለንን አመለካከት እንዴት ሊነካው ይገባል?

ሥራ 17:28:- “በእርሱ [በአምላክ] ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን፣ እንኖርማለን።”

መዝ. 36:9:- “የሕይወት ምንጭ ከአንተ [ከይሖዋ አምላክ] ዘንድ ነውና።”

ሮሜ 14:12:- “እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።”

ከፅንስ በኋላ ባሉት በመጀመሪያዎቹ የዕድገት ደረጃዎች የሚገኝን የአንድ ሕፃን ሕይወት ይሖዋ ልክ እንደማንኛውም ሕይወት ክቡር አድርጎ ይመለከተዋልን?

መዝ. 139:13–16:- “አቤቱ [ይሖዋ፣] አንተ . . . በእናቴ ሆድ ሰውረኸኛል፤ . . . ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ እንኳን ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።”

በማኅፀን ውስጥ ባለ ፅንስ ላይ ጉዳት ያደረሰ ሰው ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ አምላክ ተናግሮ ያውቃልን?

ዘጸ. 21:22, 23 አዓት:- “ሁለት ሰዎች ቢጣሉና አንዲትን ያረገዘች ሴት እስክትጨነግፍ ድረስ ቢጎዱአት፣ በሕይወት ላይ ግን የደረሰ ጉዳት ባይኖር የሴቲቱ ባል የጫነበትን ያህል ካሣ ይስጥ። በፈራጆችም በኩል ይስጥ። በአደጋው ምክንያት ሕይወት ከጠፋ ግን ሕይወት በሕይወት ይከፈል።” (አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በዚህኛው ለእስራኤል በተሰጠ ሕግ ላይ አሳሳቢው ጉዳይ በፅንሱ ሳይሆን በእናቲቱ ላይ የሚደርሰው ጉዳት እንደሆነ በሚያስመስል መንገድ ይህን ጥቅስ አስቀምጠውታል። የዕብራይስጡ በኩረ ጽሑፍ ግን በእናቲቱም ሆነ በፅንሱ ላይ የሚደርሰውን የሕይወት ጉዳት ያመለክታል።)

አምላክ ባልፈቀደው ምክንያት ሆን ብሎ ሰብዓዊ ሕይወት ማጥፋት የቱን ያህል ከባድ በደል ነው?

ዘፍ. 9:6:- “የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።”

1 ዮሐ. 3:15:- “ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ [አይኖርም።]”

ዘጸ. 20:13:- “አትግደል።”

እርግዝናው እስከ መውለጃዋ ቀን ድረስ እንዲቀጥል ቢደረግ ለእናቲቱ ጤና አደገኛ እንደሚሆን ዶክተር ቢናገር ፅንሱን ማስወረድ ትክክል ይሆናልን?

አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች የሚሰጡት አስተያየት ሊሳሳት ይችላል። ይሳሳታልም። አንድ ሰው በሌሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችል ይሆናል ተብሎ ቢገደል አድራጎቱ ትክክል ይሆናልን? በወሊድ ጊዜ ከእናቲቱ ወይም ከሕፃኑ ሕይወት የአንዳቸውን ለማዳን የሚያስገድድ ሁኔታ ቢፈጠር የማናቸውን ሕይወት ማዳን እንደሚሻል ምርጫ ማድረግ ነገሩ የሚመለከታቸው ግለሰቦች ጉዳይ ነው። ሆኖም በብዙ አገሮች የሕክምና ጥበብ እየተሻሻለ በመሄዱ እንዲህ ያለው አደገኛ ሁኔታ ብዙ ጊዜ አያጋጥምም።

አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

‘የራሴን ሰውነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመወሰን መብት አለኝ’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘እንዲህ ሊሰማዎት የቻለው ለምን እንደሆነ ይገባኛል። በአሁኑ ጊዜ ብዙ መብቶቻችን በሌሎች ሰዎች ይረገጣሉ። ብዙ ሰዎች በሌሎች ሰዎች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ደንታ ቢሶች ናቸው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ እኛን ከአደጋ ሊጠብቁ የሚችሉ መመሪያዎች ይሰጠናል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጣቸውን ጥቅሞች ለማግኘት ኃላፊነቶችንም መቀበል ይኖርብናል።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ብዙ አባቶች ልጅ የወለዱላቸውን እናቶች ጥለው ሄደዋል። ይሁን እንጂ ባልና ሚስት ሁለቱም የመጽሐፍ ቅዱስን የአቋም ደረጃዎች እየጠበቁ በሚኖሩበት ቤት ውስጥ ባል ሚስቱንና ልጆቹን ይወዳል፤ በታማኝነትም አብሯቸው ይኖራል፤ የሚያስፈልጋቸውንም ሠርቶ ያቀርባል። (1 ጢሞ. 5:8፤ ኤፌ. 5:28–31)’ (2) ‘እኛ በግላችን ፍቅርና አክብሮት ለማግኘት ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስ ያወጣቸውን የአቋም ደረጃዎች ለቤተሰባችን በምናሳየው ዝንባሌ ማሳየት አለብን። የወለድናቸውን ልጆች እንዴት መመልከት እንዳለብን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይናገራል? (መዝ. 127:3፤ ከ⁠ኢሳይያስ 49:15 ጋር አወዳድር)’