በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መግቢያ

መግቢያ

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የመላው አጽናፈ ዓለም ጌታ ነው። የአሁኑም ሆነ የወደፊቱ ሕይወታችን በእሱ ላይ የተመካ ነው። እሱ፣ መልካም ላደረጉ ሰዎች ወሮታ የመክፈል፣ ክፉ ያደረጉ ሰዎችን ደግሞ የመቅጣት ሥልጣን አለው። በተጨማሪም ሕይወት መስጠትም ሆነ ሕይወት መንሳት ይችላል። የአምላክን ሞገስ ካገኘን ሕይወታችን ስኬታማ ይሆናል፤ የእሱን ሞገስ ካጣን ግን ለውድቀት እንዳረጋለን። ስለዚህ አምልኳችን በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱ በጣም አስፈላጊ ነው!

ሰዎች አምልኳቸውን የሚያከናውኑበት መንገድ ይለያያል። ሃይማኖትን በመንገድ እንመስለው ብንል ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ አምላክ ያደርሳሉ ማለት ይቻላል? በፍጹም። የአምላክ ነቢይ የነበረው ኢየሱስ ሁለት መንገዶች ብቻ እንዳሉ አመልክቷል። እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “ወደ ጥፋት የሚወስደው በር ትልቅ፣ መንገዱም ሰፊ ነው፤ በዚያ የሚሄዱም ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው በር ግን ጠባብ፣ መንገዱም ቀጭን ነው፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።”—ማቴዎስ 7:13, 14

ስለሆነም ያሉት ሃይማኖቶች ሁለት ዓይነት ብቻ ናቸው ሊባል ይችላል፦ አንዱ ወደ ሕይወት የሚወስድ ሲሆን ሌላው ደግሞ ወደ ጥፋት የሚወስድ ነው። የዚህ ብሮሹር ዓላማ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ እንድታገኝ መርዳት ነው።