በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 2

ስለ አምላክ እውነቱን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

ስለ አምላክ እውነቱን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

1, 2. የተለያዩ ሃይማኖታዊ አመለካከቶች ትክክል መሆን አለመሆናቸውን ለማወቅ አንድ መሥፈርት እንደሚያስፈልግ በምሳሌ ማስረዳት የሚቻለው እንዴት ነው?

ስለ አምላክ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? የተለያዩ ሃይማኖቶች የሚያስተምሯቸውን ትምህ ርቶች በሙሉ መመርመር ያስፈልገናል? ይህ የማይቻል ነገር ነው። እንዲህ ማድረግ ብንችል እንኳ ትክክለኛው ትምህርት የቱ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

2 በእርግጥም ሰዎች አምላክን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ከመሆኑ አንጻር እውነቱን የምንለይበት አንድ የጋራ መሥፈርት ሊኖረን ይገባል። ነገሩን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ በአንድ የገበያ ቦታ ስለ አንድ ብትን ጨርቅ ርዝመት ክርክር ተነሳ እንበል። ሻጩ ‘ርዝመቱ ሦስት ሜትር ነው’ ሲል ገዢው ግን ‘አይ፣ ሦስት ሜትር አይሞላም’ ይላል። ታዲያ ጉዳዩ እልባት ማግኘት የሚችለው እንዴት ነው? ጨርቁን በሜትር በመለካት ነው።

3. መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ለምንድን ነው?

3 ታዲያ አንድ ሃይማኖታዊ አመለካከት ትክክል መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል መለኪያ ወይም መሥፈርት ይኖራል? አዎ አለ፤ እሱም መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አምላክ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲጻፍ ያደረገው በየትኛውም የምድር ክፍል የሚኖሩ ሰዎች ስለ እሱ እውነቱን እንዲያውቁ ብሎ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በቢሊዮን በሚቆጠሩ ቅጂዎች ታትሟል። በሙሉም ሆነ በከፊል ከ2,600 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል፣ መጽሐፍ ቅዱስን በራሱ የአፍ መፍቻ ቋንቋ በማንበብ ስለ አምላክ እውነቱን ማወቅ ይችላል።

4. መጽሐፍ ቅዱስ ምን ዓይነት መረጃዎች ይዟል?

4 መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የተገኘ ውድ ስጦታ ነው። በሌላ በምንም መንገድ ልናውቅ ስለማንችላቸው ነገሮች ይገልጻል። በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ስለሚኖሩ መንፈሳዊ አካላት ይነግረናል። የአምላክን ሐሳብ፣ ባሕርይና ዓላማ ይገልጽልናል። ከዚህም ሌላ ባለፉት በሺህ የሚ ቆጠሩ ዓመታት ውስጥ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር ስለ ነበረው ግንኙነት ይተርክልናል። ወደፊት ስለሚሆኑ ነገሮች ይነግረናል። ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድም ያሳየናል።

በመጽሐፍ ቅዱስ እንድታምን የሚያደርጉህ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

5. መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ ጋር እንደሚስማማ የትኛው ምሳሌ ያሳያል?

5 መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል ነው ብለን እንድናምን የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች አሉ። አንደኛው ምክንያት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ ጋር የሚስማማ መሆኑ ነው። በጥንት ዘመን በመላው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ምድርን ደግፎ የያዛት ነገር እንዳለ አድርገው ያስቡ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ አንዳንዶች በአንድ ትልቅ የባሕር ዔሊ ላይ የቆሙ አራት ዝሆኖች ምድርን ደግፈው እንዳቆሟት አድርገው ያምኑ ነበር። ይሁንና ከ3,500 ከሚበልጡ ዓመታት በፊት አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ “ምድርንም ያለ ምንም ነገር አንጠልጥሏል” በማለት አሁን ካለው ሳይንስ ጋር የሚስማማ ሐሳብ አስፍሯል።—ኢዮብ 26:7

6. መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈው አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጠው ትልቁ ማስረጃ ምንድን ነው?

6 መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ያስጻፈው መጽሐፍ ነው ብለን እንድናምን የሚያደርገን ትልቁ ማስረጃ ስለ ወደፊቱ ጊዜ በትክክል የሚተነብይ መሆኑ ነው። አምላክ ስለ ወደፊቱ ጊዜ እንተነብያለን ከሚሉ ሰብዓዊ ሊቃውንት በተለየ ወደፊት የሚሆነውን ነገር በትክክል ያውቃል፤ ደግሞም የሚናገረው ሁሉ ምንጊዜም በትክክል ይፈጸማል።

7. ፍጻሜያቸውን ያገኙ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የትኞቹ ናቸው?

7 በጥንት ዘመን ፍጻሜያቸውን ያገኙ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች አሉ። ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኢየሱስ በቤተልሔም ከተማ እንደሚወለድ 700 ዓመት አስቀድሞ ተንብዮ ነበር፤ ትንቢቱም በትክክል ተፈጽሟል። (ሚክያስ 5:2፤ ማቴዎስ 2:3-9) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስን አስመልክቶ ከተነገሩት ሌሎች በርካታ ትንቢቶች መካከል ከአንዲት ድንግል እንደሚወለድና ከጊዜ በኋላ በ30 የብር ሳንቲሞች አልፎ እንደሚሰጥ የሚገልጹት ትንቢቶች ይገኙበታል። እነዚህም ትንቢቶች በትክክል ተፈጽመዋል። ማንም ሰው እንዲህ ያሉ ትንቢቶችን ሊተነብይ እንደማይችል የተረጋገጠ ነው።—ኢሳይያስ 7:14፤ ዘካርያስ 11:12, 13፤ ማቴዎስ 1:22, 23፤ 27:3-5

8. በዛሬው ጊዜ ፍጻሜያቸውን በማግኘት ላይ ያሉ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የትኞቹ ናቸው? ምንስ ያረጋግጣሉ?

8 ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በዘመናችን ፍጻሜያቸውን እያገኙ ነው። አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፦

  • “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ [ለጦርነት] ይነሳል። ታላላቅ የምድር ነውጦች ይከሰታሉ፤ በተለያየ ስፍራም የምግብ እጥረትና ቸነፈር ይሆናል።”—ሉቃስ 21:10, 11

  • ‘ክፋት እየበዛ ይሄዳል።’—ማቴዎስ 24:12

  • “በመጨረሻዎቹ ቀናት . . . ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ . . . ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ . . . ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ፣ . . . በኩራት የተወጠሩ፣ ከአምላክ ይልቅ ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ ይሆናሉ።”—2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

እነዚህ ትንቢቶች አሁን እየተፈጸሙ ናቸው ቢባል አትስማማም? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ትንቢቶች እውነተኝነትና ትክክለኛነት መጽሐፍ ቅዱስ ተራ መጽሐፍ አለመሆኑን ያረጋግጣል። መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ መሪነት የተጻፈ የአምላክ ቃል ነው።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

መጽሐፍ ቅዱስ ተለውጧል?

9, 10. አምላክ፣ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረውን መልእክት እንዲለውጡት እንደማይፈቅድ የሚያሳየው ምንድን ነው?

9 ለምሳሌ ያህል የአንድ ፋብሪካ ባለቤት ነህ እንበል፤ ሠራተኞችህ እንዲያከብሩ የምት ፈልጋቸውን ደንቦች ዝርዝር አውጥተህ ለጠ ፍክ። አንድ ጠላት መጥቶ አንተ የጻፍከውን ቢለውጥብህ ምን ታደርጋለህ? የተለወጠውን ነገር አታስተካክልም? በተመሳሳይም አምላክ፣ ሰዎች በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚ ገኘውን እውነት እንዲለውጡት አይፈቅድም።

10 በአምላክ ቃል ውስጥ ያሉትን ትምህ ርቶች ለመለወጥ የሞከሩ ሰዎች አልተሳካላ ቸውም። ዛሬ በእጃችን የሚገኘውን መጽ ሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ ከሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ጋር ስናነጻጽር አንድ ዓይነት ሆኖ እናገኘዋለን። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ በጊዜ ሂደት እንዳልተለወጠ ያሳያል።