ክፍል 2
“ይሖዋ ፍትሕን ይወዳል”
ዛሬ ምድራችን በግፍ ተሞልታለች። ብዙ ሰዎች ደግሞ ለዚህ ተጠያቂው አምላክ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ “ይሖዋ ፍትሕን ይወዳል” ሲል ይገልጻል። (መዝሙር 37:28) በዚህ ክፍል ውስጥ፣ ይሖዋ በእርግጥም ፍትሕን እንደሚወድ ያሳየው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን። ይህም ለመላው የሰው ዘር ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው።
በዚህ ክፍል ውስጥ
ምዕራፍ 14
ይሖዋ “በብዙ ሰዎች ምትክ . . . ቤዛ” አዘጋጀ
ቀላል ሊመስል ቢችልም ከምናስበው በላይ አስገራሚ የሆነው ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወደ አምላክ እንድትቀርብ ይረዳሃል።
ምዕራፍ 15
ኢየሱስ ‘ፍትሕን በምድር ላይ ያሰፍናል’
ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ፍትሕ ያሰፈነው እንዴት ነው? ዛሬስ ፍትሕ እያሰፈነ ያለው እንዴት ነው? ወደፊትስ የሚያሰፍነው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 16
‘ፍትሕን በማድረግ’ ከአምላክ ጋር መሄድ
ፍትሕ፣ ትክክል እና ስህተት ስለሆነው ነገር ያለንን አመለካክት እንዲሁም ሌሎችን የምንይዝበትን መንገድ ያካትታል።