የምትመርጠው ሙዚቃና ውዝዋዜ
ምዕራፍ 17
የምትመርጠው ሙዚቃና ውዝዋዜ
1–3. (ሀ) በተፈጥሮ አካባቢያችን ውስጥ ፈጣሪያችን ሙዚቃን ማቀነባበሩን የምናየው በምን መንገዶች ነው? (ለ) መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን ወይም የሰውነት ውዝዋዜን መቀበሉን እንደሚናገር የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ስጥ።
የሰው ፈጣሪ የሰውን ልጅ አካባቢ በሙዚቃ ቅንብር ሞልቶታል። ይህም ከወፎች ጒሮሮ የሚፈልቀው የጠራውና የሚንቆረቆረው ዜማ ብቻ ሳይሆን የጅረቶች ድምፅ፣ በዛፎች ውስጥ የሚንሾካሾከው ነፋስ፣ የፌንጣዎች ጫጫታ፣ የዕንቁራሪቶች ጩኸትና ሌሎች ብዙ የምድር ፍጥረታት የሚያሰሙት ድምፅ በሙሉ የሙዚቃ ድምፅ አለው። እንግዲያውስ በሙዚቃ መሣሪያዎች መጠቀም የጀመረው በሰው ልጅ ታሪክ መባቻ መሆኑ ምንም አያስደንቅም።
2 ዘፈንና ጭፈራ ጥንታዊ ታሪክ አለው። በእስራኤላውያን ዘመን የሙሴ እህት ሚርያም “በከበሮና በዘፈን” ግንባር ቀደም ሆና ሴቶችን መርታለች። በተጨማሪም አምላክ ንጉሥ ዳዊትን ወራዳ ጠላቶችን ድል እንዲያደርጋቸው ከረዳው በኋላ “እየዘመሩና እየዘፈኑ . . . ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።” ኢየሱስ ክርስቶስም ዘጸዓት 15:20፤ 1 ሳሙኤል 18:6፤ ሉቃስ 15:25 የ1980 ትርጉም
ስለ ኰብላዩ ልጅ በተናገረው ምሳሌ ላይ ዘፈንን የግብዣው ክፍል አድርጎ ስለጠቀሰው ውዝዋዜ ተገቢ ቦታ እንዳለው አድርጎ እንደሚያይ ግልጽ ነው። ኰብላዩ ልጅ በተመለሰ ጊዜ “የሙዚቃና የዘፈን” ዝግጅት እንደ ተደረገ ኢየሱስ ተናግሯል። መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንዱ ውዝዋዜ በግለሰቦች ወይም በወንዶችና በሴቶች ቡድኖች እንደተደረገ ያሳያል። —3 ይህ ማለት ግን ሁሉም ዓይነት ሙዚቃና ውዝዋዜ ጥሩ ነው ማለት ነውን? ወይስ በምታዳምጠው ሙዚቃና በምትካፈልበት የውዝዋዜ ዓይነት ረገድ መራጭ መሆን ያስፈልግሃል? በዚህ ጉዳይ ላይ ለመወሰን ሊረዳን የሚችለው ምንድን ነው? ጉዳዩስ በእርግጥ ምን ያህል ልዩነት ያመጣል?
በዘፈንና በጭፈራ ረገድ ምርጫ ማድረግ
4–6. (ሀ) አንዳንድ ውዝዋዜዎችን ለክርስቲያኖች የማይገቡ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? (ቆላስይስ 3:5, 6) (ለ) አንዳንድ ዘመናዊ ውዝዋዜዎች ከጥንታዊ የመዋለድ ውዝዋዜዎች ጋር የሚመሳሰሉት ለምንድን ነው?
4 ‘ዎልትስ’ ከሚባለው የደስ ደስ ያለውና የዝግታ ምት ያላቸው ዳንሶች አንስቶ ወንድና ሴት እየሆኑ የሚጨፍሩባቸው የቦሄሚያ ዳንሶች የሆኑት ሞቅ ያለ ምት እስካላቸው ‘ፖልካስ’ ድረስ ብዙ ዓይነት ውዝዋዜዎች አሉ። የላቲን አሜሪካ ኮንጋ፣ ሩምባና ሳምባ እንዲሁም አብዛኞቹ አፍሪካዊ አመጣጥ ያላቸው ማሪንጌ፣ ቡጊና ቦሳ ኖቫ አሉ። ሮክን ሮል የተባለውና ሌሎችም በቅርቡ የመጡ ውዝዋዜዎችም አሉ። ከእነዚህ የሰውነት ውዝዋዜዎች አንዳንዶቹን ላለመቀበል በቂ ምክንያት ይኖርሃልን?
5 ዘፈኑ ወይም ውዝዋዜው ፍትወትን የሚቀሰቅስና የጾታ ብልግና እንድትፈጽም የሚፈትንህ ከሆነ ውዝዋዜውን ላለመቀበል በቂ ምክንያት አለህ። ምክንያቱም ብዙ ችግሮች ሊያደርስብህ ይችላል።
6 ለምሳሌ የጥንት የመዋለድ ጭፈራዎች ሆን ተብሎ ፍትወተ ሥጋን ለመቀስቀስ የሚደረጉ ነበሩ። አንዳንድ ዘመናዊ ውዝዋዜዎችም እነሱን ይመስላሉ። ከጥቂት ዓመታት በፊት ታይም መጽሔት የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቷል:-
“ትዊስት የተባለው ውዝዋዜ በመጀመሪያ ጉዳት የሌለው ዳንስ ነበር። . . . ሆኖም በኒው ዮርክ ከተማ በሚገኝ አንድ የማታ ክበብ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ለአካለ መጠን የመድረስ ጥንታዊ በዓል ቅጂ እንዲመስል በማድረግ አደሱት።”
7–10. (ሀ) አንድ ሰው በእንደነዚህ ዓይነቶቹ የሰውነት ውዝዋዜዎች ከተካፈለ ሌሎች በዚህ ሰው የሚማረኩት በምን መሠረት ይሆናል? ተቃራኒ ጾታዎችን ለመማረክ የምትፈልጊው በዚህ መሠረት ነውን? (ለ) ወንድና ሴት ተወዛዋዦች ተያይዘው የሚወዛወዙበት ለስላሳ ዳንስም እንኳን ቢሆን ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
7 በቅርብ ዓመታት የመጡ ብዙ ዳንሶች የትዊስት ቅጂዎች ናቸው። ጨፋሪዎቹ እርስ በርሳቸው አይነካኩም፤ ሆኖም ዳሌዎችና ትከሻዎች ፍትወትን በሚቀሰቅስ ሁኔታ ይወዛወዛሉ። ሰውነት እነዚህን ውዝዋዜዎች ሲያደርግ በመመልከት የአንድ ወጣት የፆታ ስሜት በቀላሉ ሊቀሰቀስ ይችላል። ለምሳሌ አንዲት ልጃገረድ በዳንሱ ውዝዋዜ ላይ ብቻ በማተኮሯ ውዝዋዜዋ የሚያስከትለው ውጤት ምንም ላይታወቃት ይችላል። ይሁን እንጂ ለኒው ዮርክ ታይምስ መጽሔት አዘጋጅ የተጻፈ የሚከተለው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ውዝዋዜዋ በተመልካቾች ላይ የሚያመጣውን ውጤትና ስለእርስዋ ምን ሊሰማቸው እንደሚችል መዘንጋት የለባትም:- “ወጣት የትዊስት ተወዛዋዦቻችን (በጣም ወጣት ያልሆኑትም ጭምር) ሰውነታቸው ዋሽቶ ነው እንጂ በውስጣዊ ሐሳባቸው የሚያስቡት በውጪ ዳሌዎቻቸውና ሽንጦቻቸው እንደሚያሳዩት አይደለም ብለን ተስፋ እናድርግ።”
8 አንቺ የተሳሳተ ውስጣዊ ዓላማ ባይኖርሽም እንደነዚህ ባሉት ውዝዋዜዎች የምትካፈይ ከሆነ ለሌሎች ወጣቶች ምን ዓይነት መስሕብ ልትሆኚ እንደምትችዪ ብታስቢበት አስተዋይነት ነው። ለምሳሌ ያህል ሰዎቹ ጠባብና የሚወጣጥሩ ልብሶች ለብሰው ዳሌያቸውን ከሚያሽከረክሩና ፍትወት የሚቀሰቅስ የተለያየ ዓይነት የሰውነት ንቅናቄ ከሚያደርጉ ሴቶች የሚያገኙትን ዓይነት የፆታ ስሜት ቀስቃሽነት ከአንቺም ስላገኙ ተማርከዋልን? ሰዎችን ለመማረክ የምትፈልጊው በዚህ መሠረት ነውን? ወይስ የምትፈልጊው በማንነትሽ ማለትም በሕይወትሽ ውስጥ ቅድሚያ በምትሰጫቸው ነገሮችና በአነጋገርሽ የሚወዱሽን ሰዎች ነው? አንቺ የምትወጂው አንዳንድ ነገሮችን ለአንቺ በማድረጉ የሚደሰተውን ነው ወይስ ከአንቺ በሚያገኘው ነገር ብቻ የሚደሰተውን?
9 ተወዛዋዦቹ ወንድና ሴት እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚደንሱበት በተዋበ የአካል እንቅስቃሴ የታጀበ የእግር አጣጣልን የሚያጎላ ለስላሳ ዳንስም እንኳን ቢሆን በአካል መነካካት ምክንያት አንዳንድ ጊዜ የፆታ ስሜት የሚቀሰቅስ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አንቺ በእንደነዚህ ዓይነቶቹ ዳንሶች የምትካፈይ ከሆነ በዳንሱ የፆታ ስሜትሽ እስኪቀሰቀስ ድረስ የተቀራረብሽ መስሎ ባይሰማሽም ከአንቺ ጋር በዳንሱ የሚካፈሉት ሰዎች ግን ተገቢ ባልሆነ መንገድ የፆታ ስሜታቸው ሊቀሰቀስ እንደሚችል በአሳቢነት ተገንዘቢ።
10 አብዛኛዎቹ ዳንሶች ተገቢ ናቸው ወይም አይደሉም ተብለው ሊመደቡ እንደማይችሉ የታወቀ ነው። ብዙዎቹ ጨዋ የሆኑና በተገቢ መንገድ ሊደረጉ፣ አለዚያም ንጹሕና ጤናማ በሆነ መንገድ እንዲደረጉ የሚመክረውን የአምላክን ቃል በሚጥስ መንገድ የሚከናወኑ ሊሆኑ ይችላሉ።
የሙዚቃ ምርጫ
11, 12. ሙዚቃ ኃይል ያለው እንዴት ነው? ምሳሌዎችን ጥቀስ።
11 እንደ ዳንስ ወይም ውዝዋዜ ሁሉ የምትሰማውን ሙዚቃ ስትመርጥ ጥንቃቄና ማስተዋል ያስፈልግሃል። ለምን? ምክንያቱም ሙዚቃ ኃይል ስላለው ነው። እንደ ማንኛውም ኃይል ሁሉ የሙዚቃ ኃይልም ሊጠቅም ወይም ሊጐዳ ይችላል።
12 ለሙዚቃ ኃይል የሚሰጠው ምንድን ነው? በሰዎች ላይ አንድ ዓይነት ስሜት፣ ዝንባሌ ወይም መንፈስ ለመቀስቀስ ያለው ችሎታ ነው። ሙዚቃ ሊያዝናናና ሊያረጋጋ ወይም ሊያነቃቃና ሊቀሰቅስ ወይም ሊነሽጥ ይችላል። በኃይለኛ ማርሽና በለስላሳ እንጒርጒሮ መካከል ያለው ልዩነት ጉልህ ከመሆኑ የተነሳ ልዩነቱ “ይሰማሃል”። ሙዚቃ ማናቸውንም የሰው ስሜት ይኸውም ፍቅር፣ ርኅራኄ፣ አክብሮት፣ ኀዘን፣ ቁጣ፣ ጥላቻና ፍትወት ሊቀሰቅስ ይችላል። በታሪክ ዘመናት በሙሉ ሰዎች የሙዚቃን ኃይል በመረዳት ሌሎችን በአንዳንድ መንገዶች ለማነሳሳት ተጠቅመውበታል። ለምሳሌ ያህል አንድ ጸሐፊ “አስደንጋጩ የጦርነት ጥሪ” ብለው የጠሩት ላ ማርሴይዝ የተሰኘው መዝሙር ለፈረንሳይ
አብዮት ድል በከፊል አስተዋጽኦ እንዳደረገ ብዙ ጊዜ ይነገራል። ትምህርት ቤቶችም ብዙውን ጊዜ ከአትሌቲክ ውድድሮች በፊት የሚጠቀሙባቸው “የግጥሚያ ዘፈኖች” አሏቸው።13–16. (ሀ) የመጽሐፈ ምሳሌ 4:23 ምክር ከአንድ ሰው የሙዚቃ ምርጫ ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው? (ለ) ሙዚቃ አንዳንድ ጊዜ ዘላቂ የሆነ ጎጂ ውጤት የሚያስከትል “ካታሊስት” ወይም አገናኝ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
13 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ ከስሜትና ከውስጣዊ ዓላማ ጋር በጥብቅ ተያይዞ ተገልጿል። ስለዚህም የአምላክ ቃል “አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና” የሚል ምክር ይሰጣል። (ምሳሌ 4:23) ሙዚቃ ስሜትን ለመቀስቀስ ያለው ኃይል እርግጠኛ ስለሆነ ልባችንን ለመጠበቅ ስለምናዳምጠው ሙዚቃ መራጭ መሆንን ይጠይቅብናል።
14 እውነት ነው የሙዚቃ የቀስቃሽነት ኃይል ጊዜያዊ ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ወደሆነ አቅጣጫ ቁርጠኛ ግፊት ለመስጠት ወይም አንድን ዓይነት አምሮት ወይም ተፈታታኝ ነገር ለመቋቋም ያለንን ኃይል ዝቅ ለማድረግ በቂ ርዝማኔ ይኖረዋል። በትምህርት ቤት ኬምስትሪ ተምረህ ከሆነ “ካታሊስት” ስለሚባሉት ኬሚካሎች አጥንተሃል። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ኬሚካሎችን ለማዋሃድ ኬሚካሎቹን ሊያቀራርባቸው የሚችል ሌላ ቅመም መጠቀም እንደሚቻል ተምረሃል። ያም ቅመም “ካታሊስት” ነው። ሁላችንም አንዳንድ ድክመቶችና የተሳሳቱ ዝንባሌዎች አሉብን። ስለዚህም አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት የሆኑ ነገሮችን ለመፈጸም ግፊት ያድርብናል። ኃጢአት የሆነውን አድራጐት እንድትፈጽም ሁኔታዎች ተመቻቹ እንበል። ሙዚቃ “ካታሊስት” ሆኖ ምኞትንና ሁኔታዎቹን ያገናኝና በኋላ በምሬት የምትጸጸትበትን ነገር የሚያስከትል ድርጊት እንድትፈጽም ያደርጋል። የብልግና ስነ ጽሑፎችን ለመመርመር በተቋቋመ አንድ የመንግሥት ኮሚሽን ውስጥ ተመራማሪ የሆኑ አንዲት ወይዘሮ በጥናታቸው ላይ ተመሥርተው እንዲህ ብለዋል:-
15 “ሙዚቃ የልጃገረዶችን የፍቅርና የመውደድ ስሜት በማነሳሳት ብዙውን ጊዜ የፍቅር ካታሊስት ሆኖ የኮረዶችን የፆታ ስሜት ይቀሰቅሳል . . . ሙዚቃው ይህ ውስጣዊ ስሜት በግልጽ እንዲወጣ ያደርጋል።”
16 አዎን፤ ሙዚቃ የሚሰጠው ግፊት ጊዜያዊም ቢሆን ዘላቂ የሆነ ወይም ዘላቂ መዘዞችን የሚያመጣ አኗኗርን መከተል እንድትጀምር ሊያደርግህ ይችላል። እንግዲያው በሙዚቃ ረገድ አስተዋይ መሆን አይበጅህምን?
ውሳኔ የማድረግ ችግር
17, 18. አንድን ሙዚቃ በማዳመጥ ለአንተ ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ልትወስን የምትችለው እንዴት ነው?
17 የቱ ሙዚቃ ጥሩ እንደሆነና የቱ ደግሞ መጥፎ እንደሆነ በቅጽበት ሊያሳውቅህ የሚችል ዝርዝር ሊሰጥህ የሚችል ሰው የለም፤ ምክንያቱም ማንኛውንም ዓይነት ሙዚቃ ብንወስድ “ሙሉ በሙሉ ጥሩ” ወይም “ሙሉ በሙሉ መጥፎ” ተብሎ ሊመደብ የሚችል ሙዚቃ የለም። የአንድን ሙዚቃ ጥሩነት ለይተህ ለማወቅ አእምሮህንና ልብህን መጠቀምና ቀደም ብሎ በተሰጡት መሠረታዊ ሥርዓቶች መመራት ይኖርብሃል። የምታደርገው ምርጫም ምን ዓይነት ሰው እንደሆንክ ለሌሎች የሚናገረው ነገር አለ።
ኢዮብ 12:11) ስለዚህ የአንተም ጆሮ ሙዚቃን መለየት ይችላል። ግጥሞቹን ሳትሰማም እንኳ ብዙውን ጊዜ አንድ ሙዚቃ ምን ዓይነት ስሜት ወይም መንፈስ ለመፍጠር ታስቦ እንደተዘጋጀ፣ ምን ዓይነት ጠባይን እንደሚያበረታታ ለመናገር ትችላለህ። ሙሴ ከሲና ተራራ ወርዶ ወደ እስራኤል ሰፈር በቀረበ ጊዜ ሙዚቃ ሲሰማ የተፈጸመው ይኸው ነበር። ሙሴ ለኢያሱ “ይህ [የድል ነሺዎች] ወይም የድል ተነሺዎች [የሙሾ] ድምፅ አይደለም፣ ነገር ግን የዘፈን ድምፅ እሰማለሁ” ብሎታል። ዘፈኑ ቅጥ የለሽና በጣዖት አምልኮ የተሞላ የብልግና ድርጊት ያንፀባርቅ ነበር። — ዘጸአት 32:15–19, 25
18 በጥንት ጊዜ ኢዮብ “ምላስ መብልን እንደሚቀምስ ጆሮ ቃልን የሚለይ አይደለምን?” በማለት ጠይቋል። (19–22. (ሀ) ክላሲካል ሙዚቃን የሚወዱ ሰዎች መጠንቀቅ የሚያስፈልጋቸው ከምንድን ነው? (ለ) የጃዝና የሮክ ሙዚቃዎችን ውጤት በተመለከተ በአስተዋይነት ልናስብባቸው የሚገቡን ምን እውነቶች አሉ?
19 የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎችንም እንውሰድ። ለምሳሌ ያህል ክላሲካል ሙዚቃ በአጠቃላይ የተከበረና አንዳንድ ጊዜም ግርማ ሞገስ ያለው ድምፅ አለው። አብዛኛውን ጊዜ በሰው አስተሳሰብ ላይ ጥሩ ውጤት ቢኖረውም ጥቂቱ ግን አስነዋሪውን ወይም ራስ ወዳድነት ያለበትን የሕይወት ገጽታ የሚያሞጋግስ ነው። ዝነኛ የነበሩ ብዙዎች የክላሲካል ሙዚቃ ደራሲዎች የብልግናና የቅሌት ኑሮ እንደኖሩ ማስታወሱ ይበጃል። አብዛኛው ድርሰታቸው የተደረሰው ‘የሕይወትን ጥሩ ነገሮች ያደንቃል’ ለሚባለው አድማጭ ቢሆንም ብልሹ አመለካከታቸውና ስሜታቸው በቃልም ይሁን ያለ ቃል በሙዚቃዎቻቸው ውስጥ ብቅ ማለቱ የማይቀር ነው። ስለዚህ የአእምሮአችንንና የልባችንን ጤንነት ለመጠበቅ የምንፈልግ ከሆነ “ቁም ነገር አዘል” ነው የሚባለውን ሙዚቃም ቢሆን ሳንመረምር መቀበል አንችልም።
20 ከክላሲካል ሙዚቃ ተቃራኒ የሆኑትን የጃዝና የሮክ ሙዚቃ እናገኛለን። እዚህም ላይ ቢሆን ለዛ ያለውና ለስለስ ያለ አንዳንድ ሙዚቃ ይገኛል። አንዳንዱ ግን መረን የለቀቀና ጆሮ የሚያደነቁር ነው። ሙዚቀኞች የጃዝና የሮክ ሙዚቃን “ለስላሳና” “ሞቅ ያለ” “ኃይለኛ” ወይም “አሲድ” ብለው እንደ ዓይመዝሙር 69:12፤ ኢሳይያስ 23:15, 16) ዛሬስ እንዴት ነው?
ነቱ የሚለዩት ለዚህ ነው። ሙዚቃው ምን ዓይነት ጠባይን እንደሚደግፍ መለየት ይገባሃል። ይህንም ጆሮህ፣ አእምሮህና ልብህ ሊነግሩህ ይገባል። ያንዳንድ ሙዚቃ ቃላት ወይም ዜማ በጣም ግልጽ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች በቀላሉ ከአንድ ዓይነት ተግባር ወይም ሰዎች ጋር ያያይዙታል። ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “ጠጪዎች” ዘፈንና ስለ “ጋለሞታ ዘፈን” ይናገራል። (21 ለምሳሌ በጋዜጣ ላይ ስለ አንድ የሙዚቃ ትርኢት ወይም ድግስ ብታነብና ሪፖርቱ ሰዎቹ እንደጮኹ፣ ልጃገረዶች ሕሊናቸውን እንደሳቱ፣ አደንዛዥ መድኃኒት ወይም ዕፅ እንደተወሰደና፣ የቴያትር አዳራሹን ሥርዓት ለማስጠበቅ ፖሊሶች እንደተጠሩ ቢገለጽ በዚያ ትርዒት ላይ ምን ዓይነት ሙዚቃ እንደቀረበ ታስባለህ? ዝነኛ ዘፋኝ ወይም ሙዚቀኛ አደንዛዥ መድኃኒት ወይም ዕፅ ከመጠን በላይ በመውሰዱ/በመውሰዷ ምክንያት እንደሞተ /እንደሞተች ብትሰማ በምን ዓይነት ሙዚቃ የሠለጠኑ ይመስልሃል?
22 ብዙ ወጣቶች የሮክ ሙዚቃ ግጥሞች በዙሪያቸው ያለውን ዓለም እውነታዎችና ችግሮች ስለሚገልጽ በእርሱ እንደሚማረኩ ሳታውቅ አትቀርም። በሕዝብ ከሚወደዱ ከሌሎቹ ሙዚቃዎች ሁሉ ሮክ ሙዚቃ ሊያስተላልፈው የሚሞክር አንድ መልዕክት አለ:- በታዳጊዎች ላይ ስለሚኖሩ ችግሮች፣ በወላጆችና በልጆች መካከል ስላለው የትውልድ ልዩነት፣ ስለ አደንዛዥ ዕፅ፣ ስለ ጾታ፣ ስለ ሕዝባዊ መብት፣ ስለ አድማ፣ ስለ ድህነት፣ ስለ ጦርነትና መሰል አርዕስቶች መልእክት ለማስተላለፍ ይሞክራል። ብዙ ወጣቶች ስለ ፍትሕ መጓደል የሚሰማቸውን ቅሬታና ለተሻለ ዓለም ያላቸውን አስተሳሰብ ለመግለጽ ይሞክራል። ይሁን እንጂ አጠቃላዩ ውጤት ምን ሆነ? ለአብዛኞቹ ወጣቶችስ ምን አደረገላቸው? ፍልስፍናዎቹስ ምን እውነተኛ መፍትሔ አመጡላቸው? እንደዚህ ዓይነት ሙዚቃዎች እውነታዎችን ቁልጭ አድርገው ለማሳየት የታሰቡ ከሆነ አብዛኞቹ ከአደንዛዥ መድኃኒቶች ወይም ዕፅ ጋር የተያያዙ የሆኑትና አንዳንዶቹ ግጥሞች ሊስተዋሉ የሚችሉት በአደንዛዥ ዕፅ ወሳጆች ብቻ የሆነው ለምንድን ነው? እነዚህ ጥያቄዎች ሊታሰብባቸው የሚገቡ ናቸው።
23–25. (ሀ) ከሙዚቃ ጋር በተያያዘ በመክብብ 7:5 ላይ ያለው ምክር ፍሬ ነገሩ ምንድን ነው? (ለ) ሙዚቃና የውዝዋዜ ዓይነቶችን ስንመርጥ ለእነማን ማሰብ ይገባናል? ለምንስ? (1 ቆሮንቶስ 10:31–33፤ ፊልጵስዩስ 1:9, 10) (ሐ) እንግዲያው የሙዚቃና የውዝዋዜ ምርጫችን በቀላሉ የሚታይ ያልሆነው ለምንድን ነው?
መክብብ 7:5 “ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገርለት “ስንፍና” የአእምሮ ፈዛዛነት ማለት ሳይሆን ሥነ ምግባራዊ ስንፍና፤ ለወደፊቱ ከችግር በቀር ሌላ ሊያመጣ የማይችል አካሄድን መከተል ማለት ነው።
23 እንግዲያውስ የሙዚቃ ምርጫህ በቀላሉ የሚታይ ነገር አይደለም። ከብዙሐኑ ጋር በመንጎድ ብቻ በሕዝብ የተወደደውን በመምረጥ ማለትም ብዙውን ሕዝብ የሚማርከውን በመምረጥ የሙዚቃ ምርጫህን በሚመለከት ሌሎች እንዲወስኑልህ ልትፈቅድ ትችላለህ። ወይም ደግሞ ራስህ ልትወስንና ምርጫ በምታደርግበት ጊዜ ጸንቶ በሚኖረውና ብልጫ ባለው በአምላክ ቃል ውስጥ በሚገኘው ጥበብ ተመርተህ ጥንቃቄ ልታደርግ ትችላለህ።24 እውነትና ትክክል ከሆነው ጋር የሚቃረኑ ቃላት የያዘ፣ ስሜታዊ የሆነና የሚያንቧርቅ ድምፅ ያለው ሙዚቃ ልትሰማ እንደምትችልና በዚህም እንደማትለወጥ ሊሰማህ ይችላል። ስለምትጨፍረው የውዝዋዜ ዓይነትም ተመሳሳይ ስሜት ይኖርህ ይሆናል። ይሁን እንጂ አንተ በሌሎች ላይ ምን ዓይነት ግፊት እያሳደርክ ነው? ለሌሎች እንቅፋት እንዳይሆን ሥጋ መብላትን የመሰለ ተገቢ ነገር እንኳን ለመተው ፈቃደኛ መሆኑን እንደተናገረው እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ይሰማሃልን? የምትመርጠው ሙዚቃ ከምን ዓይነት ሰዎች ጋር ያስመድብሃል?
25 እንግዲያውስ የምታዳምጠው ሙዚቃና የምትካፈልበት ዘፈንና ጭፈራ ፍላጎትህ “አስደሳች” እየተባለ የሚጠራ ጊዜ ከማሳለፍና የአምላክን ሞገስ አግኝተህ ዘላለማዊ የሆነ ጥሩ ሕይወት ከማግኘት የትኛው መሆኑን ያሳያል።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 124 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ዘፈንና ጭፈራ ረዥም ታሪክ አለው