በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ኢዮብ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ኢዮብ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ኢዮብ

የኢዮብ ሕይወት ምስቅልቅሉ ወጥቷል። በመጀመሪያ ንብረቱ በሙሉ ወደመ። ከዚያም ልጆቹ ሁሉ አለቁ። ይህ እንዳይበቃው ደግሞ ጤንነቱ ተቃወሰ። ይህ ሁሉ መዓት የወረደበት በድንገት ነበር። በመሆኑም ኢዮብ በከፍተኛ ሐዘን ተውጦ “ሕይወቴን እጅግ ጠላሁ” እንዲሁም “ውርደትን ተከናንቤአለሁና፤ በመከራም ተዘፍቄአለሁ” ብሏል። (ኢዮብ 10:1, 15) ኢዮብ ይህ ሁሉ መከራ ቢደርስበትም ለፈጣሪው እስከ መጨረሻው ታማኝ ሆኗል። (ኢዮብ 2:10) በሕይወቱ ውስጥ ያጋጠሙት ለውጦች አቋሙን እንዲለውጥ አላደረጉትም። በመሆኑም ኢዮብ በጽናት ረገድ ግሩም ምሳሌ ትቷል።

አንተም ችግሮች ሲያጋጥሙህ ‘ሕይወትህን ትጠላ’ ይሆናል። ያም ቢሆን ልክ እንደ ኢዮብ ይሖዋን በታማኝነት በማገልገል ልትጸና ትችላለህ፤ በሕይወትህ ውስጥ ለውጦች ቢያጋጥሙህም አቋምህን ሳትለውጥ መቀጠል ትችላለህ። ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “እነሆ፣ የጸኑትን ደስተኞች ብለን እንጠራቸዋለን። ስለ ኢዮብ ጽናት ሰምታችኋል፤ በውጤቱም ይሖዋ ያደረገለትን አይታችኋል፤ በዚህም ይሖዋ ከአንጀት የሚራራና መሐሪ እንደሆነ ተመልክታችኋል።” (ያዕቆብ 5:11) ይሖዋ ኢዮብን እንደረዳው ሁሉ አንተንም ይረዳሃል!