በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የውስጥ ሽፋን

የውስጥ ሽፋን

የውስጥ ሽፋን

ከልብ ለምንወዳችሁ ወጣቶች

የሰማዩ አባታችሁ ይሖዋ አምላክ በጣም ይወዳችኋል። ደስተኛ እንድትሆኑም ይፈልጋል። ይሁን እንጂ ‘በዛሬው ጊዜ እየኖሩ ደስተኛ መሆን ይቻላል?’ ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። ይህ ጥሩ ጥያቄ ነው። ምክንያቱም ሁላችንም በሕይወታችን ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል። እንዲያውም ደስታችንን የሚያሳጡ ችግሮች በየቀኑ እንደሚገጥሙን ይሰማን ይሆናል። ደስ የሚለው ግን አፍቃሪው አባታችን ምንጊዜም በችግራችን ይደርስልናል! መጽሐፍ ቅዱስ፣ በማዕበል እንደሚናወጥ ባሕር በሆነው በዚህ ዓለም ውስጥ ሕይወታችንን ለመምራት የሚያስፈልገንን መመሪያ ይሰጠናል። የአምላክ ቃል የተጻፈው ከረጅም ጊዜ በፊት ቢሆንም በውስጡ የሚገኘው ምክር ዛሬም ይሠራል።—መዝሙር 119:98, 99፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17

ይህን መጽሐፍ ያዘጋጀነው ስለምንወዳችሁ ነው። ደስተኞች እንድትሆኑና ከሁሉ የተሻለ ሕይወት እንድትመሩ እንፈልጋለን። በመሆኑም ይህን መጽሐፍ አንድ ጊዜ ከዳር እስከ ዳር አንብባችሁ ብቻ ከማስቀመጥ ይልቅ ችግሮች ባጋጠሟችሁ ጊዜ ሁሉ በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙትን ሐሳቦች መለስ ብላችሁ እንድትመለከቱ እናበረታታችኋለን። ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀበት አንዱ ዓላማ ከወላጆቻችሁ ጋር የልባችሁን አውጥታችሁ እንድትነጋገሩ ለመርዳት ነው። ስለሆነም ይህን መጽሐፍ ከወላጆቻችሁ ጋር እንደምታነብቡት አልፎ ተርፎም አንዳንዶቹን ክፍሎች አብራችሁ እንደምታጠኑ ተስፋ እናደርጋለን። ወላጆቻችሁ ካካበቱት ተሞክሮና ጥበብ ለመጠቀም ጥረት አድርጉ።

መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኋለን።

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል