በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ሦስቱ ዕብራውያን

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ሦስቱ ዕብራውያን

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​ሦስቱ ዕብራውያን

አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ በባቢሎን ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ዱራ ሜዳ ላይ ቆመዋል። በዙሪያቸው ያሉት ሰዎች በሙሉ በአንድ ትልቅ ምስል ፊት ተደፍተው እየሰገዱ ነው። እነዚህ ወጣቶች ግን ለእኩዮቻቸው ተጽዕኖና ለንጉሡ ማስፈራሪያ ሳይበገሩ በአቋማቸው ጸንተዋል። ይሖዋን ለማገልገል ያደረጉትን ውሳኔ ለድርድር እንደማያቀርቡት አክብሮት በተሞላበት ሆኖም ቁርጥ ባለ መንገድ ለናቡከደነፆር ነገሩት።​—ዳንኤል 1:6፤ 3:17, 18

እነዚህ ወጣቶች በግዞት ወደ ባቢሎን ሲወሰዱ ልጆች ነበሩ። በአምላክ ሕግ ውስጥ የተከለከሉ ሊሆኑ የሚችሉ ምግቦችን ለመብላት ፈቃደኞች ባለመሆን ልጆች ሳሉ ያሳዩት ታማኝነት ከጊዜ በኋላ ያጋጠሟቸውን ከበድ ያሉ ፈተናዎች ለመወጣት አዘጋጅቷቸዋል። (ዳንኤል 1:6-20) ይሖዋን መታዘዝ የጥበብ አካሄድ መሆኑን በሕይወታቸው ውስጥ ካጋጠሟቸው ነገሮች ተምረው ነበር። አንተስ በተመሳሳይ እኩዮችህ ተጽዕኖ ቢያደርጉብህም የአምላክን መሥፈርቶች በጥብቅ ለመከተል ቁርጥ ውሳኔ አድርገሃል? ወጣት እያለህ ቀላል በሚመስሉ ነገሮች ይሖዋን መታዘዝን ከተማርክ ከጊዜ በኋላ በሕይወትህ ውስጥ ከባድ ፈተናዎች ሲያጋጥሙህ በታማኝነት ለመጽናት ይበልጥ ዝግጁ ትሆናለህ።​—ምሳሌ 3:5, 6፤ ሉቃስ 16:10