በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ዳዊት

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ዳዊት

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ዳዊት

ዳዊት ሙዚቃ በጣም ይወዳል። የተዋጣለት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ከመሆኑም ሌላ ግጥምና ዜማ የመድረስ ተሰጥኦ አለው። ሌላው ቀርቶ የራሱን የሙዚቃ መሣሪያ ሠርቷል። (2 ዜና መዋዕል 7:6) ዳዊት የተካነ ሙዚቀኛ በመሆኑ የእስራኤል ንጉሥ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ሙዚቃ እንዲጫወት አስጠራው። (1 ሳሙኤል 16:15-23) ዳዊትም ግብዣውን ተቀበለ። ይሁንና ዳዊት ይህን መብት በማግኘቱ አልኮራም፤ እንዲሁም ሙዚቃ ሕይወቱን እንዲቆጣጠረው አልፈቀደም። ከዚህ በተቃራኒ ችሎታውን ይሖዋን ለማወደስ ተጠቅሞበታል።

አንተስ ሙዚቃ ትወዳለህ? የሙዚቃ መሣሪያ የመጫወት ተሰጥኦ አይኖርህ ይሆናል፤ ያም ቢሆን የዳዊትን ምሳሌ መከተል ትችላለህ። እንዴት? ሙዚቃ ሕይወትህን እንዲቆጣጠረው አትፍቀድ፤ እንዲሁም በአስተሳሰብህና በድርጊትህ ላይ መጥፎ ተጽዕኖ በማሳደር አምላክን በማያስከብር መንገድ እንድትመላለስ እንዳያደርግህ ተጠንቀቅ። ከዚህ በተቃራኒ ሙዚቃን ሕይወትህን ይበልጥ አስደሳች ለማድረግ ተጠቀምበት። አዳዲስ ሙዚቃዎችን መፍጠርና በሙዚቃ መደሰት ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ ነው። (ያዕቆብ 1:17) ዳዊት ይህን ስጦታ ይሖዋን በሚያስደስት መንገድ ተጠቅሞበታል። አንተስ እንደዚህ ታደርጋለህ?