በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሚያጋጥሙህ ለውጦች

የሚያጋጥሙህ ለውጦች

ክፍል 2

የሚያጋጥሙህ ለውጦች

በሰውነትህ ላይ የምታየው ለውጥ ያስጠላሃል?

□ አዎ □ አይ

በጉርምስና ወቅት የሚከሰቱ ለውጦች ብቸኝነት፣ ግራ መጋባት ወይም ፍርሃት እንዲሰማህ አድርገውሃል?

□ አዎ □ አይ

ነጋ ጠባ የምታስበው ስለ ተቃራኒ ፆታ ነው?

□ አዎ □ አይ

ከላይ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ለየትኛውም ቢሆን የሰጠኸው መልስ “አዎ” ቢሆን ሁኔታው ሊያስጨንቅህ አይገባም፤ በሕይወትህ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ለውጥ መከሰቱ ችግር እንዳለብህ የሚያሳይ አይደለም! በጉርምስና ወቅት የሚያጋጥሙህ አካላዊም ሆኑ ስሜታዊ ለውጦች በአንድ በኩል በደስታ ስሜት እንድትዋጥ በሌላ በኩል ደግሞ እንድትጨነቅ እንዲሁም የተዘበራረቀ ስሜት እንዲሰማህ ሊያደርጉህ ይችላሉ። ትልቅ ሰው መሆን ስትመኘው የነበረ ነገር ቢሆንም ነገሩ እውነት ሲሆን ግን ሊያስፈራህ ይችላል! ከ6 እስከ 8 ያሉት ምዕራፎች በሕይወትህ ውስጥ የሚያጋጥሙህን ለውጦች እንዴት ማስተናገድ እንደምትችል እንድትገነዘብ ይረዱሃል።

[በገጽ 56 እና 57 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]