በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሽፋኑ የውስጥ ገጽ

የሽፋኑ የውስጥ ገጽ

የሽፋኑ የውስጥ ገጽ

ውድ አንባቢ

ጠቢቡ ንጉሥ ሰለሞን እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል።” (መክብብ 11:9) በወጣትነትህ ጊዜ፣ ሕይወት አስደሳች በሆኑና በሚያጓጉ ነገሮች የተሞላ ሊሆን ይችላል፤ እኛም ጥሩ የወጣትነት ጊዜ እንድታሳልፍ እንፈልጋለን። በሌላ በኩል ደግሞ የወጣትነት ጊዜህን ይሖዋ አምላክን በሚያስደስት መንገድ እንድታሳልፈው እናበረታታሃለን። ይሖዋ በሕይወትህ ውስጥ የምታከናውናቸውን ነገሮች እንደሚመለከትና በዚያም መሠረት ፍርድ እንደሚሰጥህ ፈጽሞ አትዘንጋ። እንግዲያው ሰለሞን “በወጣትነትህ ጊዜ፣ ፈጣሪህን አስብ” በማለት የሰጠውን ተጨማሪ ምክር በተግባር ማዋልህ የጥበብ አካሄድ ነው!​—መክብብ 12:1

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት ሐሳቦች፣ በዛሬው ጊዜ ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን ተጽዕኖዎችና ፈተናዎች ለመቋቋም እንዲረዱህ እንዲሁም ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚስማሙ ውሳኔዎችን ማድረግ የምትችልባቸውን መንገዶች እንዲጠቁሙህ ልባዊ ጸሎታችን ነው። እነዚህን ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ የይሖዋን ልብ ደስ ማሰኘት ትችላለህ።—ምሳሌ 27:11

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል