በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጪው ጊዜያችሁ

መጪው ጊዜያችሁ

ክፍል 10

መጪው ጊዜያችሁ

የዘመኑ ወጣቶች ምንም ዓይነት የወደፊት ሕይወት እንደሌላቸው በማሰብ ያደጉ ናቸው። የኑክሌር ጦርነት፣ የሥነ ምሕዳር ወይም የኢኮሎጂ ቀውስና የኢኮኖሚ ዝብርቅ በአድማሳችን ላይ እያንዣበቡ ነው። ይሁን እንጂ የሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ አያሳስባችሁ ይሆናል። እናንተን የሚያሳስባችሁ ከዛሬ 10, 20 ወይም 30 ዓመት በኋላ የምትኖሩበት ሁኔታ ሊሆን ይችላል።

ስለመጪው ሕይወታችሁ ብሩሕ ተስፋ እንዲኖራችሁ የሚያስችል በቂ ምክንያት አለ። ነገር ግን ይህን ብሩሕ ተስፋ ልትጨብጡ የምትችሉት በአሁኑ ጊዜያችሁ በሚገባ ከተጠቀማችሁ ነው።