በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በቤት ውስጥ:-ከቤተሰብ አባሎች ጋር ተስማምቶ መኖር

በቤት ውስጥ:-ከቤተሰብ አባሎች ጋር ተስማምቶ መኖር

ክፍል 1

በቤት ውስጥ፦ ከቤተሰብ አባሎች ጋር ተስማምቶ መኖር

“ማን እንደ ቤት!” ይህ የታወቀ አባባል በአሁኑ ጊዜ ዘመን ያለፈበት መስሎ መታየቱ በእጅጉ ያሳዝናል። ብዙ ቤቶች ማባሪያ በሌለው የቤተሰብ ግጭት ምክንያት የለየላቸው የጦር አውድማዎች በመሆን ላይ ናቸው። ተነጋግሮ ለመግባባት አለመቻል አብዛኛውን ጊዜ ሰላም ለመመሥረት የሚደረገውን ማንኛውንም ጥረት እንዳይሳካ ያደርጋል።

ቤታችሁ ሰላም የሰፈነበት ሥፍራ እንጂ የጥላቻ ችግኝ የሚፈላበት ማሳ እንዳይሆን ትፈልጋላችሁን? እውነት ነው፣ የተቀሩት የቤተሰባችሁ አባሎችም የበኩላቸውን ማድረግ አለባቸው። ይሁን እንጂ ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በማወቅና ተግባራዊ በማድረግ ለቤታችሁ ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለማበርከት ትችላላችሁ።