በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት ቤትና ሥራ

ትምህርት ቤትና ሥራ

ክፍል 5

ትምህርት ቤትና ሥራ

ወደዳችሁም ጠላችሁ፣ ከዕድሜያችሁ 12 ዓመት የሚያክለውን የምታሳልፉት በትምህርት ቤት ነው። እነዚህ ዓመታት በጣም አሰልቺ አለበለዚያም በርካታ እውቀት የሚገኝባቸው ዓመታት ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ በአብዛኛው የሚመካው በትምህርት ቤት የምታሳልፉትን ጊዜ በምትጠቀሙበት ሁኔታ ላይ ነው። ስለዚህ በዚህ ክፍል ስለ ትምህርት ቤት፣ ስለ ቤት ሥራ፣ ስለ ማርክና ስለ መምህራን ጠለቅ ብለን እንመለከታለን። ትምህርት የጨረሳችሁ ከሆናችሁ ደግሞ ሥራ በታጣበት በዚህ ዘመን እንዴት ሥራ ልታገኙ እንደምትችሉ የሚጠቁም ጠቃሚ ምክር እንሰጣለን።