በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 114

የክፋት ሁሉ ፍጻሜ

የክፋት ሁሉ ፍጻሜ

ሥዕሉ ላይ ምን ታያለህ? አዎ፣ በነጫጭ ፈረሶች ላይ የተቀመጠ ሠራዊት ይታያል። ሆኖም ከየት እየመጡ እንዳሉ ተመልከት። ፈረሶቹ ከሰማይ ወደ ምድር በደመና ላይ እየጋለቡ ነው! በሰማይ ፈረሶች አሉ እንዴ?

የሉም፤ እነዚህ የእውነት ፈረሶች አይደሉም። እንዲህ የምንለው ፈረሶች በደመና ላይ መጋለብ ስለማይችሉ ነው፤ ይችላሉ እንዴ? ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ ስላሉ ፈረሶች ይናገራል። ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?

በአንድ ወቅት ፈረሶች በጦርነቶች ላይ በጣም ያገለግሉ ስለነበረ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ከሰማይ ወደ ምድር ስለሚጋልቡ ፍጥረታት የሚናገረው አምላክ ምድር ላይ ካሉ ሰዎች ጋር ለመዋጋት ጦርነት እንደሚያካሄድ ለማመልከት ነው። ይህ ጦርነት የሚካሄድበት ቦታ ምን ተብሎ እንደሚጠራ ታውቃለህ? አርማጌዶን ይባላል። ይህ ጦርነት ክፋትን ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ ያጠፋል።

በአርማጌዶን በሚካሄደው በዚህ ጦርነት ፊት ፊት እየመራ የሚዋጋው ኢየሱስ ነው። ይሖዋ በመንግሥቱ ላይ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ኢየሱስን እንደሆነ አስታውስ። ኢየሱስ የንጉሥ ዘውድ ያደረገው ለዚህ ነው። ሰይፉ ደግሞ የአምላክን ጠላቶች በሙሉ እንደሚገድል ያሳያል። አምላክ ክፉ ሰዎችን በሙሉ የሚያጠፋ መሆኑ ሊያስደንቀን ይገባል?

ወደ 10ኛው ታሪክ መለስ በልና ተመልከት። እዚያ ላይ ምን ትመለከታለህ? አዎ፣ ክፉ ሰዎችን ያጠፋው ታላቅ ጎርፍ ይታያል። ይህን ጎርፍ ያመጣው ማን ነው? ይሖዋ አምላክ ነው። አሁን ደግሞ 15ኛውን ታሪክ ተመልከት። እዚያ ላይ ምን ነገር ሲከናወን ይታያል? ሰዶምና ገሞራ ይሖዋ ባወረደው እሳት ሲጠፉ ያሳያል።

ሠላሳ ሦስተኛውን ታሪክ አውጣ። የግብፃውያን ፈረሶችና የጦር ሰረገሎች ምን እየደረሰባቸው እንዳለ ተመልከት። ውኃው በላያቸው ላይ እንዲመለስ ያደረገው ማን ነው? ይሖዋ ነው። ይህን ያደረገው ሕዝቡን ለመጠበቅ ሲል ነው። 76ኛውን ታሪክ ተመልከት። እዚያ ላይ ይሖዋ የራሱ ሕዝብ የነበሩትን እስራኤላውያን እንኳን ሳይቀር በክፉ ሥራቸው ምክንያት እንዲጠፉ እንዳደረገ ማየት ትችላለህ።

እንግዲያው ይሖዋ ክፋትን ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ ለማጥፋት ሰማያዊ ሠራዊቱን የሚልክ መሆኑ ሊያስደንቀን አይገባም። ሆኖም ይህ ሲፈጸም የሚኖረውን ሁኔታ አስብ! እስቲ ገጹን ግለጥና እንመልከት