በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 3

እስራኤላውያን ከግብፅ ነፃ ከወጡበት እስከ መጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ

እስራኤላውያን ከግብፅ ነፃ ከወጡበት እስከ መጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ

ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ነፃ አውጥቶ አምላክ ሕጎቹን ለእነርሱ ወደሰጠበት ወደ ሲና ተራራ ወሰዳቸው። ከጊዜ በኋላ ሙሴ የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ 12 ሰዎችን ላከ። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሰዎች መካከል አሥሩ መጥፎ ወሬ ይዘው ተመለሱ። ሕዝቡ ወደ ግብፅ የመመለስ ፍላጎት እንዲያድርበት አደረጉ። እምነት በማጣታቸው የተነሣ አምላክ እስራኤላውያንን ለ40 ዓመታት በምድረ በዳ እንዲቅበዘበዙ በማድረግ ቀጣቸው።

በመጨረሻም ኢያሱ እስራኤላውያንን እየመራ ወደ ከነዓን ምድር እንዲያስገባ ተመረጠ። ይሖዋ ምድሪቱን መውሰድ እንዲችሉ ለመርዳት ተአምራት ፈጸመ። የዮርዳኖስ ወንዝ መፍሰሱን እንዲያቆም፣ የኢያሪኮ ግንብ እንዲፈራርስና ፀሐይ ለአንድ ሙሉ ቀን እንድትቆም አድርጓል። ከስድስት ዓመታት በኋላ ከነዓናውያንን አስለቅቀው ምድሪቱን ወሰዱ።

እስራኤል ከኢያሱ ጀምሮ ለ356 ዓመታት በመሳፍንት ተገዝታለች። ባርቅን፣ ጌዴዎንን፣ ዮፍታሔን፣ ሳምሶንንና ሳሙኤልን ጨምሮ ስለ ብዙዎቹ መሳፍንት እንማራለን። በተጨማሪም እንደ ረዓብ፣ ዲቦራ፣ ኢያኤል፣ ሩት፣ ናዖሚና ደሊላ ስለ መሳሰሉት ሴቶችም የምንማረው ነገር ይኖራል። በክፍል ሦስት ውስጥ በጠቅላላው 396 ዓመታት የፈጀ ታሪክ ተካቷል።