በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 71

አምላክ ገነት እንደሚያመጣ ቃል ገብቷል

አምላክ ገነት እንደሚያመጣ ቃል ገብቷል

ይህ የገነት ሥዕል ነው፤ አምላክ ይህን የመሰለውን የገነት ገጽታ ለነቢዩ ኢሳይያስ ሳያሳየው አይቀርም። ኢሳይያስ የኖረው ዮናስ ከሞተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው።

ገነት ማለት “የአትክልት ቦታ” ወይም “መናፈሻ ቦታ” ማለት ነው። ቀደም ሲል በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያየነው አንድ ነገር ትዝ አለህ? ይሖዋ አምላክ ለአዳምና ለሔዋን ካዘጋጀላቸው ውብ የአትክልት ቦታ ጋር አንድ ነው፤ አይደለም እንዴ? ይሁን እንጂ መላዋ ምድር ገነት ትሆን ይሆን?

ይሖዋ ነቢዩ ኢሳይያስ የአምላክ አገልጋዮች ወደፊት ስለሚወርሱት አዲስ ገነት እንዲጽፍ ነግሮታል። እንዲህ ብሏል:- ‘ተኩላዎችና በጎች አንድ ላይ በሰላም ይኖራሉ። ጥጃዎችና የአንበሳ ግልገሎች አንድ ላይ ይበላሉ፤ ትንንሽ ልጆችም ይጠብቋቸዋል። ሌላው ቀርቶ አንድ ሕፃን በአንድ መርዘኛ እባብ አጠገብ ቢጫወት እንኳ አይጎዳውም።’

ብዙዎች ‘ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም። በምድር ላይ ምን ጊዜም ችግር አለ፤ ወደፊትም ችግር ይኖራል’ ይላሉ። ይሁን እንጂ እስቲ አስበው:- አምላክ ለአዳምና ለሔዋን የሰጣቸው መኖሪያ ምን ዓይነት ነበር?

አምላክ አዳምንና ሔዋንን በገነት አስቀመጣቸው። ውብ መኖሪያቸውን ያጡት፣ ያረጁትና በኋላም የሞቱት የአምላክን ትእዛዝ በመጣሳቸው ብቻ ነበር። አምላክ እሱን ለሚወዱት ሰዎች አዳምና ሔዋን ያጡትን ነገር መልሶ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል።

በመጪዋ አዲስ ገነት የሚጎዳም ሆነ የሚያጠፋ ነገር አይኖርም። ፍጹም ሰላም ይኖራል። ሰዎች ሁሉ ጤናሞችና ደስተኞች ይሆናሉ። አምላክ በመጀመሪያ እንዲሆን ፈልጎት የነበረው ነገር ሁሉ ይሆናል። ይሁን እንጂ አምላክ ይህን የሚያመጣው እንዴት እንደሆነ ቆየት ብለን እንማራለን።