በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 5

ከባቢሎን ምርኮ የኢየሩሳሌም ግንቦች እስከ ተሠሩበት

ከባቢሎን ምርኮ የኢየሩሳሌም ግንቦች እስከ ተሠሩበት

እስራኤላውያን ተማርከው በባቢሎን እያሉ እምነታቸውን የሚፈትኑ ብዙ ነገሮች አጋጥመዋቸዋል። ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ በኃይል በሚነድድ እሳት ውስጥ ተጣሉ፤ ሆኖም አምላክ በሕይወት አተረፋቸው። ከዚያም ቆየት ብሎ ባቢሎን በሜዶናውያንና በፋርሳውያን ድል ከተደረገች በኋላ ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ፤ ሆኖም አምላክ የአንበሶቹን አፍ በመዝጋት እርሱንም አዳነው።

በመጨረሻ፣ የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ እስራኤላውያንን ነፃ አወጣቸው። ተማርከው ወደ ባቢሎን በተወሰዱ ልክ በ 70 ዓመታቸው ወደ ትውልድ አገራቸው ተመለሱ። ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ መጀመሪያ ካደረጓቸው ነገሮች አንዱ የይሖዋን ቤተ መቅደስ መገንባት ነበር። ይሁን እንጂ ጠላቶቻቸው ወዲያውኑ ሥራውን አስቆሟቸው። ስለዚህ ቤተ መቅደሱ በመጨረሻ ተሠርቶ ያለቀው ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ከ22 ዓመታት ገደማ በኋላ ነበር።

ቀጥሎ፣ ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ቤተ መቅደሱን ለማስዋብ ያደረገውን ጉዞ እንመለከታለን። ይህ የሆነው ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ካለቀ ከ47 ዓመታት ገደማ በኋላ ነበር። ከዚያም ዕዝራ ይህን ጉዞ ካደረገ ከ13 ዓመታት በኋላ ነህምያ የፈራረሱት የኢየሩሳሌም ግንቦች እንዲሠሩ አስተዋጽኦ አድርጓል። ክፍል አምስት እስከዚህ ጊዜ ድረስ ያለውን የ152 ዓመታት ታሪክ ይሸፍናል።