በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል—2

ከጥፋት ውኃ እስራኤላውያን ከግብፅ ነፃ እስከ ወጡበት

ከጥፋት ውኃ እስራኤላውያን ከግብፅ ነፃ እስከ ወጡበት

ከጥፋት ውኃው የተረፉት ስምንት ሰዎች ብቻ ቢሆኑም ከጊዜ በኋላ ቁጥራቸው አድጎ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሆኑ። የጥፋት ውኃው ከደረሰ ከ352 ዓመታት በኋላ አብርሃም ተወለደ። አምላክ ይስሐቅ የተባለ ወንድ ልጅ እንዲወልድ በማድረግ ለአብርሃም የገባውን ቃል እንዴት እንደጠበቀ እንማራለን። ከዚያም ይስሐቅ ከነበሩት ሁለት ልጆች መካከል አምላክ ያዕቆብን መረጠው።

ያዕቆብ 12 ወንዶች ልጆችና ጥቂት ሴቶች ልጆችን ያቀፈ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ነበረው። የያዕቆብ 10 ወንዶች ልጆች ታናሽ ወንድማቸውን ዮሴፍን ስለ ጠሉት በግብፅ ባሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ሸጡት። ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ በግብፅ አገር ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ገዥ ሆነ። ከባድ ረሃብ በደረሰ ጊዜ ዮሴፍ ወንድሞቹ ልባቸው ተለውጦ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ ፈተናቸው። በመጨረሻም፣ የያዕቆብ መላው ቤተሰብ ማለትም እስራኤላውያን ወደ ግብፅ ሄደው በዚያ መኖር ጀመሩ። ይህ የሆነው አብርሃም ከተወለደ ከ290 ዓመታት በኋላ ነበር።

ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን በግብፅ ምድር 215 ዓመታት አሳለፉ። ዮሴፍ ከሞተ በኋላ በዚያው በግብፅ አገር ባሪያዎች ሆኑ። ከጊዜ በኋላ ሙሴ ተወለደና አምላክ እስራኤላውያንን ከግብፅ ነፃ ለማውጣት ተጠቀመበት። በክፍል ሁለት ውስጥ የ 857 ዓመታት ታሪክ ተካቷል።