ምዕራፍ አሥራ አንድ
መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው?
1, 2. ብዙ ሰዎች የትኛውን ጥያቄ ይጠይቃሉ?
ኃይለኛ ጎርፍ አንድን መንደር አወደመ። መሣሪያ የታጠቀ አንድ ሰው፣ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተኩስ ከፍቶ ብዙ ሰዎችን አቆሰለ፤ የሞቱ ሰዎችም አሉ። አምስት ልጆች ያሏት አንዲት እናት በካንሰር በሽታ ሕይወቷ አለፈ።
2 ብዙ ሰዎች እንዲህ ያሉ አደጋዎች ወይም አሳዛኝ ሁኔታዎች ሲከሰቱ “ይህ ሁሉ መከራ የሚደርሰው ለምንድን ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። ብዙዎች ዓለም በጥላቻና በመከራ የተሞላው ለምን እንደሆነ ግራ ይገባቸዋል። አንተስ እንዲህ ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ?
3, 4. (ሀ) ዕንባቆም የትኞቹን ጥያቄዎች ጠይቋል? (ለ) ይሖዋ ምን መልስ ሰጠው?
3 መጽሐፍ ቅዱስ፣ በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት ያላቸው ሰዎችም እንኳ እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን እንዳነሱ ይናገራል። ለምሳሌ ነቢዩ ዕንባቆም ይሖዋን እንዲህ ሲል ጠይቆት ነበር፦ “ለምን በደል ሲፈጸም እንዳይ ታደርገኛለህ? ጭቆናንስ ለምን ዝም ብለህ ታያለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ የሚፈጸመው ለምንድን ነው? ጠብና ግጭትስ ለምን በዛ?”—ዕንባቆም 1:3
4 በዕንባቆም 2:2, 3 ላይ እንደተገለጸው፣ አምላክ ዕንባቆም ላነሳቸው ጥያቄዎች መልስ የሰጠ ከመሆኑም ሌላ ሁኔታውን እንደሚያስተካክል ቃል ገብቷል። ይሖዋ ሰዎችን በጣም ይወዳል። መጽሐፍ ቅዱስ “እሱ ስለ እናንተ ያስባል” በማለት ይናገራል። (1 ጴጥሮስ 5:7) እንዲያውም አምላክ መከራን እኛ ከምንጠላው በላይ ይጠላል። (ኢሳይያስ 55:8, 9) ታዲያ በዓለም ላይ መከራ የበዛው ለምንድን ነው? የዚህን ጥያቄ መልስ እስቲ እንመልከት።
መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው?
5. አብዛኞቹ የሃይማኖት መሪዎች መከራን በተመለከተ ምን ይላሉ? መጽሐፍ ቅዱስስ ምን ይላል?
5 አብዛኛውን ጊዜ ፓስተሮች፣ ቄሶችና የሃይማኖት መሪዎች ‘በሰዎች ላይ መከራና ሥቃይ የሚደርሰው የአምላክ ፈቃድ ስለሆነ ነው’ ብለው ያስተምራሉ። አንዳንዶች ደግሞ አሳዛኝ ሁኔታዎችን ጨምሮ በሰዎች ላይ የሚደርሱትን ነገሮች በሙሉ አምላክ አስቀድሞ እንደወሰነና ይህ የሆነበትን ምክንያት ፈጽሞ መረዳት እንደማንችል ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ ‘ሕፃናትም ሆኑ ትላልቅ ሰዎች የሚሞቱት አምላክ ከእሱ ጋር እንዲሆኑ ስለሚፈልግ ነው’ ይላሉ። ሆኖም ይህ እውነት አይደለም። በሰዎች ላይ መጥፎ ነገር የሚያመጣው ይሖዋ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ “‘ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በደል ይፈጽማል’ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው!” በማለት ይናገራል።—ኢዮብ 34:10
6. ብዙ ሰዎች በዓለም ላይ ያለውን መከራ ሁሉ ያመጣው አምላክ እንደሆነ የሚሰማቸው ለምንድን ነው?
6 ብዙ ሰዎች ‘ምድርን የሚገዛው አምላክ ነው’ የሚል እምነት ስላላቸው በዓለም ላይ ያለውን መከራ ሁሉ ያመጣው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ይሁንና በምዕራፍ 3 ላይ እንደተመለከትነው የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው።
7, 8. በዓለም ላይ መከራ የበዛው ለምንድን ነው?
7 መጽሐፍ ቅዱስ “መላው ዓለም . . . በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው” ይላል። (1 ዮሐንስ 5:19) የዚህ ዓለም ገዢ የሆነው ሰይጣን አረመኔና ጨካኝ ነው። “መላውን ዓለም እያሳሳተ” ነው። (ራእይ 12:9) ብዙዎች የሰይጣንን ባሕርይ እያንጸባረቁ ነው። ዓለም በውሸት፣ በጥላቻና በጭካኔ ሊሞላ የቻለበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው።
8 ይሁንና በዓለም ላይ መከራ የበዛው በዚህ ምክንያት ብቻ አይደለም። አዳምና ሔዋን በአምላክ ላይ ካመፁ በኋላ ኃጢአትን ለልጆቻቸው አወረሱ። ሰዎች ኃጢአትን ስለወረሱ አንዳቸው ሌላውን መክብብ 4:1፤ 8:9) አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሰዎች “መጥፎ ጊዜና ያልተጠበቁ ክስተቶች ያጋጥሟቸዋል።” (መክብብ 9:11) በመጥፎ ጊዜ የማይሆን ቦታ ላይ በመገኘታቸው ለአደጋ ይጋለጣሉ፤ ወይም መከራና ሥቃይ ይደርስባቸዋል።
ያሠቃያሉ። ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ሰዎች በልጠው መታየት ይፈልጋሉ። በመሆኑም እርስ በእርስ ይጋጫሉ፣ ይዋጋሉ እንዲሁም አንዳቸው ሌላውን ይጨቁናሉ። (9. አምላክ መከራን ያላስወገደበት በቂ ምክንያት አለው የምንለው ለምንድን ነው?
9 ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ መከራ አያመጣም። በዓለም ላይ ለሚካሄደው ጦርነት እንዲሁም በየቦታው ለሚፈጸመው ወንጀልና ግፍ ተጠያቂው አምላክ አይደለም። እንደ ምድር ነውጥ፣ አውሎ ነፋስና ጎርፍ የመሳሰሉ አደጋዎች እንዲከሰቱ የሚያደርገውም እሱ አይደለም። ይሁንና ‘ይሖዋ ሁሉን ቻይ አምላክ ከሆነ ይህ ሁሉ መከራ ሲደርስ ዝም ብሎ የሚያየው ለምንድን ነው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። አምላክ በጣም እንደሚያስብልን እናውቃለን፤ ይህን ማወቃችን ‘መከራን ያላስወገደበት በቂ ምክንያት አለው’ ብለን እንድንደመድም ያደርገናል።—1 ዮሐንስ 4:8
አምላክ መከራ እንዲደርስብን የፈቀደው ለምንድን ነው?
10. ሰይጣን ይሖዋን ምን ብሎ ከሶታል?
10 ዲያብሎስ በኤደን የአትክልት ስፍራ አዳምንና ሔዋንን አሳስቷቸዋል። ሰይጣን አምላክን ‘ክፉ ገዢ ነው’ ሲል ከሶታል። አዳምንና ሔዋንን ጥሩ የሆነ ነገር እንደከለከላቸው ተናግሯል። የአምላክ አገዛዝ እንደማያስፈልጋቸው እንዲሁም ከይሖዋ ይልቅ ለእሱ ቢገዙ እንደሚጠቀሙ ሊያሳምናቸው ፈልጎ ነበር።—ዘፍጥረት 3:2-5፤ ተጨማሪ ሐሳብ 27ን ተመልከት።
11. ለየትኛው ጥያቄ መልስ ማግኘት ይኖርብናል?
11 አዳምና ሔዋን በይሖዋ ላይ ዓመፁ። ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር ራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ ይሖዋ፣ አዳምና ሔዋን እንደተሳሳቱና ለእኛ የሚጠቅመውን የሚያውቀው እሱ እንደሆነ ማሳየት የሚችለው እንዴት ነው?
12, 13. (ሀ) ይሖዋ አዳምንና ሔዋንን ወዲያውኑ ያላጠፋቸው ለምንድን ነው? (ለ) ይሖዋ፣ ሰይጣን የዚህ ዓለም ገዢ እንዲሆን እንዲሁም የሰው ልጆች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ የፈቀደው ለምንድን ነው?
12 ይሖዋ አዳምንና ሔዋንን ወዲያውኑ አላጠፋቸውም። ከዚህ ይልቅ ልጆች እንዲወልዱ ፈቅዶላቸዋል። ይህም ልጆቻቸው የራሳቸውን ምርጫ እንዲያደርጉ በር ከፍቷል፤ ይሖዋ ለእሱ አለዚያም ለሰይጣን እንዲገዙ ምርጫ ሰጥቷቸዋል። የይሖዋ ዓላማ ምድር ፍጹም በሆኑ ሰዎች እንድትሞላ ነው፤ ዲያብሎስ ምንም ቢያደርግ የይሖዋ ዓላማ መፈጸሙ አይቀርም።—13 ሰይጣን ይሖዋን የከሰሰው በሚሊዮን በሚቆጠሩ መላእክት ፊት ነው። (ኢዮብ 38:7፤ ዳንኤል 7:10) በመሆኑም ይሖዋ፣ ሰይጣን ያነሳው ክስ እውነት መሆን አለመሆኑ እንዲታይ በቂ ጊዜ ሰጥቷል። የሰው ልጆችም በሰይጣን አመራር ሥር ሆነው የራሳቸውን መስተዳድር በማቋቋም ያለአምላክ እርዳታ ስኬታማ መሆን ይችሉ እንደሆነ እንዲያሳዩ ጊዜ ሰጥቷል።
14. ይሖዋ ጊዜ መስጠቱ ምን ነገር እንዲረጋገጥ አድርጓል?
14 የሰው ልጆች በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ራሳቸውን ለማስተዳደር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም። ሰይጣን ውሸታም መሆኑ ተረጋግጧል። የሰው ልጆች ያለአምላክ እርዳታ ሊሳካላቸው አይችልም። ነቢዩ ኤርምያስ “ይሖዋ ሆይ፣ የሰው መንገድ በራሱ እጅ እንዳልሆነ በሚገባ አውቃለሁ። አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም” በማለት ይህን በግልጽ ተናግሯል።—ኤርምያስ 10:23
ይሖዋ ይህን ያህል ጊዜ የታገሠው ለምንድን ነው?
15, 16. (ሀ) ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ ለረጅም ጊዜ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው? (ለ) ይሖዋ ሰይጣን ያስከተለውን ችግር ያላስተካከለው ለምንድን ነው?
15 ይሖዋ፣ በሰው ልጆች ላይ ለረጅም ጊዜ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው? መጥፎ ነገሮችን የማያስወግደው ለምንድን ነው? የሰይጣን አገዛዝ ለሰው ልጆች ጥቅም እንደማያስገኝ
ለማረጋገጥ ጊዜ መስጠት አስፈልጓል። የሰው ልጆች የተለያዩ የአገዛዝ ሥርዓቶችን ቢሞክሩም ስኬታማ ሊሆኑ አልቻሉም። በሳይንስና በቴክኖሎጂ ከፍተኛ እድገት ያደረጉ ቢሆንም ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ጦርነት በዝቷል፤ እንዲሁም የፍትሕ መጓደል፣ ድህነትና ወንጀል ተስፋፍቷል። ያለአምላክ እርዳታ ራሳችንን በተሳካ ሁኔታ ማስተዳደር አንችልም።16 ይሁንና ይሖዋ ጣልቃ ገብቶ ሰይጣን ያስከተለውን ችግር ለማስተካከል አልሞከረም። እንዲህ ማድረግ የሰይጣንን አገዛዝ እንደመደገፍ ይቆጠራል፤ ይሖዋ ደግሞ እንዲህ እንደማያደርግ የታወቀ ነው። በተጨማሪም ይሖዋ አሁን ያሉትን ችግሮች ቢያስተካክል፣ ሰይጣን እንዳለው የሰው ልጆች በተሳካ ሁኔታ ራሳቸውን ማስተዳደር እንደቻሉ አድርገው ያስቡ ነበር። ሆኖም ይህ ውሸት ነው፤ ይሖዋ ይህን ውሸት የሚደግፍ ነገር አያደርግም። ይሖዋ ፈጽሞ አይዋሽም።—ዕብራውያን 6:18
17, 18. ይሖዋ፣ ሰይጣን ያስከተለውን ጉዳት ለማስተካከል ምን እርምጃ ይወስዳል?
17 ይሖዋ፣ ሰይጣንና ሰዎች ማመፃቸው ያስከተለውን ጉዳት ሙሉ በሙሉ ማስተካከል ይችላል? አዎ። አምላክ ማድረግ የማይችለው ነገር የለም። ይሖዋ፣ ሰይጣን የሰነዘረው ክስ በተሟላ ሁኔታ ምላሽ ካገኘ በኋላ እርምጃ ይወስዳል። በዚያን ጊዜ አምላክ ምድርን ወደ ገነትነት ይለውጣል፤ በዚህ መንገድ የአምላክ ዓላማ ይፈጸማል። “በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ” ከሞት ይነሳሉ። (ዮሐንስ 5:28, 29) ሰዎች ፈጽሞ አይታመሙም እንዲሁም አይሞቱም። ኢየሱስ፣ ሰይጣን ያመጣውን መጥፎ ነገር ሁሉ ያስወግዳል። ይሖዋ በኢየሱስ አማካኝነት ‘የዲያብሎስን ሥራ ያፈርሳል።’ (1 ዮሐንስ 3:8) ይሁንና ይሖዋ ወዲያውኑ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ስለታገሠ አመስጋኞች ነን። ምክንያቱም እሱን ማወቅ ችለናል፤ እንዲሁም እሱ ገዢያችን እንዲሆን እንደምንፈልግ ማሳየት የምንችልበት አጋጣሚ አግኝተናል። (2 ጴጥሮስ 3:9, 10ን አንብብ።) ይሖዋ መከራ ቢደርስብንም እንኳ መጽናት እንድንችል ይረዳናል።—ዮሐንስ 4:23፤ 1 ቆሮንቶስ 10:13ን አንብብ።
18 ይሖዋ ለእሱ እንድንገዛ አያስገድደንም። ለሰው ልጆች የመምረጥ ነፃነት ሰጥቷቸዋል። ይህ ውድ ስጦታ ለእኛ ምን ጥቅም እንዳለው እስቲ እንመልከት።
የመምረጥ ነፃነትህን የምትጠቀምበት እንዴት ነው?
19. ይሖዋ ምን ውድ ስጦታ ሰጥቶናል? ለዚህ ስጦታ አመስጋኞች መሆን ያለብንስ ለምንድን ነው?
19 ይሖዋ ውድ ስጦታ ይኸውም የመምረጥ ነፃነት ስለሰጠን ከእንስሳት በጣም የተለየን ነን። እንስሳት የሚንቀሳቀሱት በደመ ነፍስ ነው፤ እኛ ግን በመረጥነው መንገድ የመኖር ነፃነት ተሰጥቶናል፤ ይሖዋም በራሳችን ፍላጎት ተነሳስተን ስናመልከው ይደሰታል። (ምሳሌ 30:24) በተጨማሪም የተሠሩበትን ዓላማ ብቻ እንደሚያከናውኑ ማሽኖች አይደለንም። የፈለግነውን ዓይነት ሰው የመሆን፣ የፈለግነውን ጓደኛ የመምረጥ እንዲሁም ሕይወታችንን በፈለግነው መንገድ የመጠቀም ነፃነት አለን። ይሖዋ ደስተኞች እንድንሆን ይፈልጋል።
20, 21. አሁን ልታደርገው የምትችለው ከሁሉ የተሻለ ምርጫ ምንድን ነው?
20 ይሖዋ እንድንወደው ይፈልጋል። (ማቴዎስ 22:37, 38) አንድ አባት፣ ልጁ ተገዶ ሳይሆን ከልቡ ተነሳስቶ “እወድሃለሁ” ሲለው በጣም እንደሚደሰት ሁሉ ይሖዋም ከልብ ተነሳስተን ስንወደው ደስ ይለዋል። ይሖዋን የምናገለግለው በምርጫችን ነው። ሰይጣንም ሆነ አዳምና ሔዋን ይሖዋን ላለማገልገል መርጠዋል። የአንተስ ምርጫ ምንድን ነው?
21 ይሖዋን ለማገልገል ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አምላክን ለማስደሰትና ሰይጣንን ለመቃወም መርጠዋል። (ምሳሌ 27:11) ታዲያ አምላክ መከራን ሁሉ ካስወገደ በኋላ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር አሁን ምን ማድረግ ይኖርብሃል? የሚቀጥለው ምዕራፍ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል።