በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በሚሊዮን የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ፍጡራን

በሚሊዮን የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ፍጡራን

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ መንፈሳዊ አካሎች እንዳሉ ይናገራል። ይሖዋ ራሱ መንፈስ ነው።—ዮሐንስ 4:24፤ 2 ቆሮንቶስ 3:17, 18

ይሖዋ በጽንፈ ዓለም ብቻውን ይኖር የነበረበት ጊዜ ነበር። ከዚያ በኋላ መላእክት የሚባሉ መንፈሳዊ አካሎችን መፍጠር ጀመረ። መላእክት ከሰዎች የበለጠ ኃይልና እውቀት ያላቸው ፍጡራን ናቸው። ይሖዋ ብዙ መላእክት ፈጥሯል። የአምላክ አገልጋይ የነበረው ዳንኤል መቶ ሚሊዮን የሚያክሉ መላእክት በራእይ አይቷል።—ዳንኤል 7:10፤ ዕብራውያን 1:7

እነዚህ መላእክት የተፈጠሩት አምላክ ምድርንም እንኳ ከመፍጠሩ በፊት ነበር። (ኢዮብ 38:4-7) ከእነሱ መካከል አንዳቸውም ቢሆን በአንድ ወቅት በምድር ላይ ኖሮ በኋላ የሞተ ሰው መንፈስ አልነበረም።

ታላቁ መንፈስ ይሖዋ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ መንፈሳዊ አካሎችን ፈጥሯል