በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ገነቲቷ ምድር

ገነቲቷ ምድር

ይሖዋ ሰይጣን ያደረሰውን ጉዳት በሙሉ ያስወግዳል። ይሖዋ መላዋን ምድር እንዲያስተዳድር ኢየሱስን ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። በእሱ አገዛዝ ሥር ምድር ወደ ገነትነት ትለወጣለች።—ዳንኤል 7:13, 14፤ ሉቃስ 23:43

ይሖዋ የሚከተሉትን ነገሮች እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፦

  • የተትረፈረፈ ምግብ፦ “ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤ አምላክ፣ አዎ፣ አምላካችን ይባርከናል።” “በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል፤ በተራሮችም አናት ላይ በብዛት ይኖራል።”—መዝሙር 67:6፤ 72:16

  • ጦርነት አይኖርም፦ “ኑና የይሖዋን ሥራዎች እዩ፤ በምድርም ላይ አስደናቂ ነገሮችን እንዴት እንዳከናወነ ተመልከቱ። ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።”—መዝሙር 46:8, 9

  • ክፉ ሰዎች አይኖሩም፦ “ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ . . . ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤ በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤ እነሱ ግን በዚያ አይገኙም።”—መዝሙር 37:9, 10

  • በሽታ፣ ሐዘን፣ ወይም ሞት አይኖርም፦ “በዚያን ጊዜ የዓይነ ስውራን ዓይን ይገለጣል፤ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ጆሮም ይከፈታል። በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤ የዱዳም ምላስ በደስታ እልል ይላል።”—ኢሳይያስ 35:5, 6

    “አምላክ ራሱም ከእነሱ ጋር ይሆናል። እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።”—ራእይ 21:3, 4

ይሖዋ እንደ ሰይጣንና እንደ አጋንንቱ አይዋሽም። ቃል የገባው ተስፋ በሙሉ ሳይፈጸም አይቀርም። (ሉቃስ 1:36, 37) ይሖዋ ይወድሃል፣ በሚያዘጋጃት ገነት ውስጥ እንድትኖርም ይፈልጋል። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙትን አስደናቂ እውነቶች በይበልጥ ለማወቅ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ተገናኝ። እውነትን በሕይወትህ በሥራ ላይ ካዋልክ ለሐሰት፣ ለአጉል እምነትና ለድንቁርና ባሪያ ከመሆን ነፃ ትወጣለህ። ኢየሱስ እንዳለው “እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል።”—ዮሐንስ 8:32