“ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ የሚደረገው ጦርነት” ቀርቧል!
ምዕራፍ 19
“ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ የሚደረገው ጦርነት” ቀርቧል!
1. (ሀ) ብሔራት በቅርቡ ሁሉን የሚችለው አምላክ “በይሖዋ የጦርነት መጽሐፍ” ውስጥ ምንን እንዲጽፍ ያስገድዱታል? ያስ መጽሐፍ ምን ነበር? (ለ) ያ መጽሐፍ ወደ ታላቁ ፍጻሜው የሚደርሰው በየትኛው ጦርነት ነው?
ብሔራት ከረጅም ጊዜ በኋላ በመጨረሻው ሁሉን የሚችለው አምላክ “(በይሖዋ) የጦርነት መጽሐፍ” ውስጥ ታላቁን መደምደሚያ ምዕራፍ እንዲጽፍ የሚያስገድዱበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል። (ዘኁልቁ 21:14) ይህ መጽሐፍ ይሖዋ ስለ ሕዝቡ ሲል ያደረጋቸውን ውጊያዎች የያዘ እውነተኛ መዝገብ ነበር። ሙሴ እንዳነበበው ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። መጽሐፉ የሚጀምረው አብርሃም ሎጥን ይዘው በነበሩት ነገሥታት ላይ ባደረገው የተሣካ ጦርነት ሳይሆን አይቀርም። (ዘፍጥረት 14:1–16, 20) አሁን ግን በቅርቡ “(የይሖዋ) የጦርነት መጽሐፍ” ከሁሉም የበለጠ ክብራማ ስለ ሆነው ድል የሚገልጽ አንድ አዲስ ምዕራፍ ተጨምሮለት ወደ ታላቅ ፍጻሜው ይደርሳል። ይህም ለዚህ የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ የሆነው በአርማጌዶን “ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ የሚደረገው ጦርነት” ይሆናል። (ራእይ 16:14, 16) መላው “መጽሐፍ” ሁሉን የሚችለው አምላክ በውጊያ ወይም በጦርነት ተሸንፎ እንደማያውቅ ያሳያል።
2, 3. (ሀ) ክርስትና ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ ይሖዋ ወታደራዊ “ጦርነት” ስለ ማድረጉ የትኛው ነገር እውነት ነው? (ለ) በዘመናችን ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ሲል እንዲዋጋ የሚያነሣሣው ምንድን ነው?
2 እውነት ነው፤ ክርስትና ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ይሖዋ ከወታደራዊ ጦርነቶች በተለየ በሌላ መንገድ ሕዝቡን ጠብቆአል። ይሖዋ በሙሴ ሕግ ሥር
ለነበሩት የእስራኤል ሕዝብ እንዳደረገው ለክርስቲያን ምስክሮቹ በፍጹም ተዋግቶ አያውቅም። ይሁን እንጂ በቅርቡ በዘመናችን ላሉት ውስን አገልጋዮቹ ሲል በወታደራዊ መንገድ የሚዋጋበት ጊዜ ይመጣል። ያንን ጦርነት በአርማጌዶን የሚቀሰቅሰው ምን ይሆናል?3 የአምላክ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ታላቂቱ ባቢሎን ትጠፋለች። ሰይጣን ዲያብሎስና የታላቂቱ ባቢሎን ሃይማኖት የለሽ አጥፊዎች ከጥፋት የተረፈው ሃይማኖታዊ ቡድን የይሖዋ ምስክሮች ብቻ እንደሆኑ ሲመለከቱ ይናደዳሉ። የዓለም መሪዎች ዓለምን አምላክ የለሽ ለማድረግ ወደሚያልሙት ግብ ገና አልደረሱም። ስለዚህ አሁን የአጽናፈ ዓለም የበላይ ገዥነቱን በካዱትና በሚቃወሙት በይሖዋ አምላኪዎች ላይ አጠቃላይ ጥቃት ለማድረስ ይነሳሉ! በዚህም መንገድ ከአምላክ ጋር የሚዋጉ ይሆናሉ።— ራእይ 17:14, 16፤ ከሥራ 5:39 ጋር አወዳድር።
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ” ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደገና ጀመረ
4. (ሀ) ይሖዋ ለጎግ ጥቃት ምላሽ የሚሰጠው እንዴት ነው? (ለ) ያስ ምላሽ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ” ከሚለው ስም ጋር በመስማማት ምንን የሚያረጋግጥ ይሆናል?
4 በይሖዋ ሕዝብ ላይ ጥቃት እንዲደረግ የሚያነሣሣውና ዕቅድ የሚያወጣው ምሳሌያዊው የማጎጕ ጎግ ሰይጣን ዲያብሎስ ይሆናል። ጎግ አምላክ የለሽ ጭፍራውን የይሖዋን ሕዝቦች ለማጥፋት፣ ለመዝረፍና ለማጥቃት ሲያነሣሣ በሕዝቅኤል 38:2, 12, 18–20 እንደተተነበየው ይሖዋ ጣልቃ ይገባና ለሕዝቡ ይዋጋል። ይሖዋ የሚሰጠው ምላሽ በዘካርያስ 14:3 ላይም ተተንብዮአል:- “[ይሖዋም (አዓት)] ይወጣል፣ በሰልፍም ቀን እንደተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል።” በዚህም መንገድ የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ለሁሉም ዘመናዊ ብሔራት ልክ በጥንት እስራኤል ዘመን እንደነበረው አሁንም ተዋጊ አምላክ መሆኑን ያስመሠክራል፤ በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ተመዝግቦ እንደሚገኘው 260 ጊዜ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ” ተብሎ ተገልጿል።— መዝሙር 24:10፤ 84:12 አዓት
5, 6. (ሀ) አሁን ምን ጦርነት ይነሣል? ሰማያዊውን ሠራዊት ወደ ውጊያ የሚያስከትተው ማን ይሆናል? (ለ) ወደ ውጊያ ስለሚዘምቱት ሰማያዊ ሠራዊት ሐዋርያው ዮሐንስ ምን ዘገባ ይሰጣል?
5 “ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ የሚደረገው ጦርነት” ሲደርስ ያንን ቀን ለይቶ የሚያሳውቅ ‘የጦርነት’ ጊዜ ይሆናል። ይሖዋ ለጦር አዛዡ ለኢየሱስ ክርስቶስ ጀምር የሚል ምልክት ይሰጠዋል። እርሱና እልፍ አእላፍ የሆኑ ሰማያዊ የመላዕክት ሠራዊት በጦር ፈረሶች ላይ እንደሚጋልቡ ተዋጊዎች ወደ ውጊያው ይገባሉ። (ይሁዳ 14, 15) ሐዋርያው ዮሐንስ ልክ እንደ አንድ የጦርነት ዜና አጠናቃሪ በመሆን የይሖዋ የጦር አዛዥ “ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ በሚደረገው ጦርነት” ጠላቶቹን ደምስሶ ድል ስለማግኘቱ የሚገልጽ የቅድሚያ ዘገባ ይሰጠናል:-
6 “ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፣ እነሆም አምባላይ ፈረስ፣ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፣ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም። ዓይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፣ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ፣ . . . በሰማይም ያሉት ጭፍሮች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር። አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል። በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ የሚል ስም አለው።”— ራእይ 19:11–16
7. ምሳሌያዊ የአምላክ ቁጣ የወይን መጥመቂያ መረገጡ ለብሔራት ምን ትርጉም አለው?
7 ንጉሣዊው የጦር አዝማች ኢየሱስ ክርስቶስ በአርማጌዶን ጦርነት ሰማያዊውን ሠራዊት በተባበሩት ጠላቶች ሁሉ ላይ ድል ወደሚጐናጸፍበት ፍልሚያ ያስከትታል። ያንን የጦር ሜዳ ወደ አንድ ትልቅ የወይን መጥመቂያ ይለውጠዋል! ይህ የነገሥታት ንጉሥ “ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል” ስለተባለ ይህ ነገር ብሔራት ሙሉ በሙሉ እንደሚጨፈለቁ ያሳያል። እንደ በሰሉ የወይን ፍሬዎች እጅግ ታላቅ ወደ ሆነው “መጥመቂያ” ይጣሉና ‘ሁሉን የሚችለው አምላክ ቍጣ’ እየተጫነ ይጨፈልቃቸዋል። ሰማያዊው ሠራዊትም ‘ታላቁን የአምላክ ቁጣ ወይን መጥመቂያ’ በመርገጡ ሥራ ይተባበራሉ።—8. ይሖዋ የጦር ዘዴዎቹን የሚገልጸው እንዴት ነው?
8 በምድር ያሉት የይሖዋ ምስክሮች በጎግ “ጭፍራ” ላይ “ሰይፍ” አያነሱም፤ ይህን የሚያደርገው ይሖዋ ነው። ይህ የእርሱ ውጊያ ነው! ይህ በሳይንስ የመጠቀ ዓለም እርሱ ሲዋጋ አሁን በመጨረሻ ይመለከታል! እስቲ የጦር ዘዴዎቹን ሲገልጻቸው አድምጡ:- “በተራሮቼ ሁሉ በእርሱ (በጎግ) ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፣ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፣ ይላል [ልዑሉ ጌታ ይሖዋ (አዓት)] በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ አሕዛብ ላይ አዘንባለሁ። ታላቅ እሆናለሁ እቀደስማለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ፤ እኔም [ይሖዋ (አዓት)] እንደሆንሁ ያውቃሉ።”— ሕዝቅኤል 38:21–23
ጠላትን ለማጥቃት የሚያገለግሉት መለኮታዊ መሣሪያዎች
9. ይሖዋ በጠላቶቹ ላይ የሚጠቀምባቸው አንዳንድ የጦር መሣሪያዎች ምንድን ናቸው?
9 የጦር መሣሪያዎችን በሚመለከት ይሖዋ እንደ ዶፍ ዝናብ፣ ሞትን ሊያስከትል የሚችል መጠን ያለው የበረዶ ድንጋይ፣ የሚወረወር የእሳትና የዲን ዝናብ፣ ከመሬት ውስጥ የሚፈልቅ ውሃና የሚያስተጋባ መብረቅ በመሳሰሉት የተፈጥሮ ኃይሎች ይጠቀማል። አምላክ ጠላቶቹን ለመግደል የሚጠቀምበት መሣሪያ በሚያንጸባርቅበት ጊዜ ብርሃኑ በቀንና በሌሊት በጣም ኃይለኛ ስለሚሆን ጸሐይና ጨረቃ ከዚያ በኋላ ዕንባቆም 3:10, 11) ይሖዋ ለውጊያው ሊጠቀምባቸው የሚችል ብዙ የተፈጥሮ ኃይሎች አሉት።— ኢያሱ 10:11፤ ኢዮብ 38:22, 23, 29
ብርሃንን ለመስጠት እንደማያስፈልጉ መስለው ይታያሉ። ብርሃን በመስጠት ኃይል አንጸባራቂዎቹ የይሖዋ ፍላጻዎች የበለጠ በድምቀት እንዲታዩ በመደረጉ ምክንያት እነርሱ እንደ ብርሃን ሰጪ ሆነው ስለማያገለግሉ ቀጥ ብለው እንደቆሙ ያህል ይሆናል። (10. በዘካርያስ 14:12 መሠረት በመጪው “የውጊያ ቀን” ላይ ይሖዋ በምን ሌላ ነገር ይጠቀማል?
10 በመጭው ‘የውጊያ ቀን’ ይሖዋ በቸነፈርና ‘በመቅሰፍት’ ጭምር ይጠቀማል። ስለዚህ ሁኔታ ነቢዩ ዘካርያስ እንደሚከተለው በማለት ጽፎአል:- “[ይሖዋም (አዓት)] ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀስፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፣ ዓይኖቻቸው በዓይነ ስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፣ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።”— ዘካርያስ 14:12
11. የይሖዋን ሕዝብ እያጠቁ ያሉትን ተዋጊዎች “መቅሰፍት” ሲመታቸው ምን ነገር ይሆናል?
11 “መቅሰፍቱ” ቃል በቃልም ይሁን ወይም አይሁን አስደንጋጭ ዛቻዎችን ለማውጣት የሚከፈቱትን አፎች ዝም ያሰኛል! ምላሶች ይበሰብሳሉ! የማየት ኃይል ያቆማል፣ ስለዚህ ክፉ ዓይን ያላቸው ወራሪዎች ጥቃት ሊሰነዝሩ የሚችሉት በጭፍን ብቻ ይሆናል። ዓይኖች ይበሰብሳሉ! የኃያል ተዋጊዎች ጡንቻም በድን በመሆን መሬት ላይ ተጋድመው ሳይሆን ገና በእግሮቻቸው ቆመው እያሉ ይዝለፈለፋሉ። አጽማቸውን የሸፈነው ሥጋም ይበሰብሳል!— ከዕንባቆም 3:5 ጋር አወዳድር።
12. “መቅሰፍቱ” የጠላትን የጦር ሠፈሮችና መሣሪያዎች የሚነካው እንዴት ነው?
12 “መቅሰፍቱ” በድንገት ወታደራዊ ሰፈሮቻቸውን ይመታል። ለጥቃት የተዘጋጀው ተንቀሳቃሽ መሣሪያ ምንም እንዳይሠራ ሆኖ እንዳይንቀሳቀስ ይደረጋል! (ዘካርያስ 14:15፤ ከዘፀአት 14:24, 25 ጋር አወዳድር) የጦር መሣሪያቸው እንዴት ዋጋ ቢስ እንደሚሆን ለማመልከት የዘካርያስ 14:6 ቃላት እንዲህ ይላሉ:- “በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።” በእነርሱ ላይ የአምላክን ሞገስ የሚያስገኝ ምንም ሰማያዊ ብርሃን አይበራም። የዘመናዊው ሳይንስ ሰው ሰራሽ ብርሃኖች የይሖዋን ሞገስ ማጣታቸውን የሚያሳየውን ጨለማ አያስወግዱትም። ተንቀሳቃሽ ማሽኖች ልክ በቅዝቃዜ እንደረጉ ያህል የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
13. ይሖዋ በጥቃት ፈጻሚዎቹ በሚያስነሳው ሽብር ላይ ምን ሌላ ነገር ይጨምራል?
13 ይህ ሁሉ ነገር ብቻ እንኳ በጣም አስደንጋጭ ነው! ዘካርያስ 14:13
ይሁን እንጂ ከሽብሩ በተጨማሪ አምላክ ለጥቃት በተዘጋጁት መካከል ግራ መጋባትን ይፈጥራል። በይሖዋ ምስክሮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የፈጠሩት አንድነት ይንኮታኮታል። በሮማ የትግል ማሳያ ስታዲየሞች በራሳቸው ላይ ዓይንን የሚከልል ቁር ይደፉ እንደነበሩት ግላዲያተሮች እርስ በርሳቸው ሳይተያዩ ይመታታሉ። እርስ በርሳቸው ሲተራረዱም ሞት የሚያስከትለው ግራ መጋባት ይስፋፋል።—14. (ሀ) በዚያን ጊዜ እልቂቱ ምን ያህል ስፋት ይኖረዋል? ወፎችና አራዊትስ ከይሖዋ ድል ጥቅሞች ተካፋይ የሚሆኑት እንዴት ነው? (ለ) በሕይወት የሚተርፉት “በይሖዋ ለተገደሉት” ምን ዓይነት ዝንባሌ ይኖራቸዋል?
14 የቀኖች ሁሉ ቀን በሆነው በዚያን ቀን የሚኖረው እልቂት ከፍተኛ ይሆናል፤ ምክንያቱም በዚያ ጦርነት ውስጥ ከጎግ ወገን የሚሰለፉት ኃይሎች ብዙ ይሆናሉ። (ራእይ 19:19–21) ይህ በእርግጥም ምድር አቀፍ ጦርነት ይሆናል፤ ምክንያቱም የትኛውም የምድር ክፍል ከጥፋት አያመልጥም። ከዚህም በላይ በአርማጌዶን የሚሞቱት እነርሱን ለማስታወስ ምልክቶች በሚደረጉባቸው መቃብሮች ውስጥ አይቀበሩም። ሁሉም ዓይነት ወፎችና የዱር አራዊት ከአምላክ ድል ጥቅሞች ተካፋይ ይሆናሉ፤ በዚያም በመሬት ላይ እንደ ማዳበሪያ ሆኖ ከሚቀረው፣ ከማይለቀስለት፣ ከማይቀበረው፣ በሕይወት ለሚተርፉት ከሚያስጠላው ከብዙ የተዝረከረከ በድን ምድርን ለማጽዳት ይረዳሉ። (ሕዝቅኤል 39:1–5, 17–20፤ ራእይ 19:17, 18) “በይሖዋ የተገደሉት” ለራሳቸው ለዘላለም መጥፎ ስም ያተርፋሉ።— ኤርምያስ 25:32, 33፤ ኢሳይያስ 66:23, 24
የይሖዋ ስም ግርማ ይለብሳል
15. በዚያን ጊዜ ምን ከፍተኛ ሁኔታ ይፈጸማል? በይሖዋስ ስም ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል?
15 በዚህ መንገድ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ” በጦር አዝማቹ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለራሱ ሕዝቅኤል 38:23፤ 39:6, 7) ይሖዋ ለራሱ “(በይሖዋ) የጦርነት መጽሐፍ” ውስጥም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ከተጠቀሰው ከማንኛውም ነገር የሚበልጥ ስም ያተርፋል። (ኢሳይያስ 63:12–14) ይሖዋ ‘ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ በሚደረገው ጦርነት’ በሚያገኘው አስደንጋጭ ድል ይሖዋ የተባለው ስሙ ምንኛ የተዋበ ይሆናል! ያንን ስም የሚያፈቅሩት ሁሉ በዚያን ጊዜ ምስጋናውን በመዘመር ለዘላለም በደስታ ያመሰግኑታል!
የማይጠፋ ክብር ያገኛል። ያን ጊዜ በአጽናፈ ዓለም ታሪክ ውስጥ ትልቁ ክንዋኔ ይፈጸማል፤ እርሱም የይሖዋ የበላይ ገዥነት መረጋገጥና የቅዱስ ስሙ መቀደስ ነው። (16. “ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ የሚደረገው ጦርነት” በጣም መቅረቡን ስንመለከት “እጅግ ብዙ ሰዎች” ስለተባሉት ምን ጸሎት ይቀርባል?
16 እንግዲያው አቤቱ የሠራዊቱ ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሣዊ ልጅህን ኢየሱስ ክርስቶስን ከጎንህ አድርገህ የውጊያ እርምጃህን ጀምር! (መዝሙር 110:5, 6) “ሁሉን በሚችለው አምላክ ታላቅ ቀን ላይ በሚደረገው ጦርነት” በንጉሡ ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለምታገኘው ተወዳዳሪ የማይገኝለት ድል በምድር ላይ ያሉት ታማኝ ምስክሮችህ ደስተኛ ምስክሮች ይሁኑ። “እጅግ ብዙ ሰዎች” የሆኑትም ለዘላለም ምስክሮችህ እንዲሆኑ ‘ከታላቁ መከራ በሕይወት ይውጡ።’ (ራእይ 7:14) በአንተ ፍቅራዊ እንክብካቤ ስር በመሆን ጦርነት ወደ ሌለበት ድል አድራጊው “የሰላም መስፍንህ” ወደሚገዛበት የሺህ ዓመት ግዛት በሕይወት ተርፈው ይግቡ። ከሙታን ለሚነሡት ሁሉ የሚታይ ምስክር ይሁኑ። የአጽናፈ ዓለም የበላይነት ያንተ ነውና ሉዓላዊነትህ በዚህ መንገድ ይረጋገጥ። “በይሖዋ የጦርነት መጽሐፍ” ውስጥ የመጨረሻውንና ታላቁን ምዕራፍ ስለምትጽፍ እናመሰግንሃለን። ይህ የአንተ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ድል በአጽናፈ ዓለም የታሪክ መዝገብ ውስጥ ለዘላለም ተመዝግቦ ይኑር!
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 156, 157 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ” በብሔራት ላይ ጦርነት ይከፍታል