ኅልውናዋ ስጋት ላይ የወደቀው “ባቢሎን” ጥፋት ይጠብቃታል
ምዕራፍ 4
ኅልውናዋ ስጋት ላይ የወደቀው “ባቢሎን” ጥፋት ይጠብቃታል
1. (ሀ) “ባቢሎን” የሚለው ቃል ትርጉሙ ምንድን ነው? በዚህ ስም የምትጠራዋንስ ከተማ የመሠረታት ማን ነው? (ለ) ምኞቱ ትልቅ የነበረው ናምሩድ የጀመረው ምን ዓይነት የግንባታ እቅድ ነው? ከምንስ ውጤት ጋር?
የዛሬው ዓለም በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በሃይማኖታዊ ሁኔታ ዝብርቅርቍ ወጥቷል። በእንግሊዝኛ “ኮንፊውዥን” ወይም ግራ መጋባት ወይም ዝብርቅ ተብሎ የተተረጎመው የመጽሐፍ ቅዱሱ የዕብራይስጥ ቃል “ባቢሎን” ነው። በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ባቢሎን ባቤል ተብላ ተጠርታለች፤ ይህም ስም “ዝብርቅርቁ የወጣ” ማለት ነው። በዚህ ስም የምትጠራው ከተማ በይሖዋ ላይ ዓምጾ በተነሣው በናምሩድ የተቆረቆረች ነበረች። (ዘፍጥረት 10:8–10 አዓት) ምኞቱ ትልቅ በሆነው በናምሩድ መሪነት ስር የነበሩ ሰዎች ይሖዋን በመናቅ እስከ ሰማይ የሚደርስ አንድ ግንብ መገንባት ጀመሩ። ይሖዋም አብረው ለመሥራት ሙከራ በሚያደርጉበት ጊዜ እርስ በርሳቸው ለመግባባት እንዳይችሉ የሠራተኞቹን አንድ ቋንቋ በማዘበራረቅ ይህንን አምላክን የሚያዋርድ ፕሮጀክት አከሸፈው።— ዘፍጥረት 11:1–9
2. (ሀ) የዓለም ኃያል መንግሥት በነበረችው በባቢሎን ላይ በ539 ከዘአበ ምን ደረሰ? ይህስ በዚህ ስም ለምትጠራ ከተማ የመጨረሻው ምዕራፍ ሆኖአልን? (ለ) ጥንታዊቷ የባቢሎን ከተማ ማን ሆና አልተገኘችም?
2 ከዚያ ብዙ ጊዜ ቆይቶ ባቢሎን በሚለው ስም የምትጠራ አንዲት አዲስ ከተማ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ እንደተቈረቈረች ተመዝግቧል። (2 ነገሥት 17:24፤ 1ዜና 9:1) በ539 ከዘአበ ባቢሎናዊው የዓለም ኃያል መንግሥት በኢሳይያስ 45:1–6 ላይ በሚገኘው የይሖዋ ትንቢት ፍጻሜ መሠረት የሜዶ ፋርስ ንጉሥ በነበረው በታላቁ ቂሮስ አማካይነት ተገልብጧል። ባቢሎን ከፍተኛ ውድቀት ቢደርስባትም እንኳ እንደ አንዲት ከተማ ሆና እንድትቀጥል ተፈቅዶላት ነበር። ከተማዋ እስከ መጀመሪያው መቶ ዘመን እንደ ዘመናችን አቆጣጠር አጋማሽ ድረስ ቆይታ እንደነበር ተገልጿል። (1 ጴጥሮስ 5:13) ይሁን እንጂ ያች የጥንት ከተማ ሐዋርያው ዮሐንስ በራእይ መጽሐፍ ምዕራፍ 17 ውስጥ የገለጻት “ታላቂቱ ባቢሎን” ሆና አልተገኘችም።
3. ታላቂቱ ባቢሎን ማን ናት?
3 በራእይ (በአፖካሊፕሱ) መጽሐፍ ውስጥ የተገለጸችው “ታላቂቱ ባቢሎን” የዓለምን የሐሰት ሃይማኖት ግዛት፣ ሕዝበ ክርስትና ተብለው የሚጠሩትን ሃይማኖቶች ሁሉ ጭምር ለማመልከት በቆመች “በቀይ አውሬ” ላይ በምትጋልብ አንዲት ጋለሞታ ሴት ተመስላለች። * (ራእይ 17:3–5) ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እርሷ በተመለከተው ራእይ መሠረት ይህች ምሳሌያዊት ድርጅት ከሁሉም ምድራዊ የፖለቲካ ገዥዎች ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ፈጽማለች። የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት የሆነችው ታላቂቱ ባቢሎን አሁንም እንኳ ሳይቀር ተጽዕኖ ማሳደር የሚያስችል ትልቅ ኃይል አላት።
“የዓለም ወዳጅ” እንጂ የአምላክ ወዳጅ አይደለችም
4. በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ታላቂቱ ባቢሎን በሰው ዘር ቤተሰብ በፈጸመችው ወንጀል ላይ የባሰ የጨመረችው እንዴት ነው?
4 ይሁን እንጂ ታላቂቱ ባቢሎን የምትገኝበት ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም፤ በተለይ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ ስጋት ወድቆባታል። በዚያን የጦርነት ወቅት ከዚያ በፊት በሰው ዘር ላይ በፈጸመቻቸው ወንጀሎች ላይ የባሰ ጨምራለች። የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ነን ባዮቹ የሕዝበ ክርስትና ቄሶች ወጣቶች ወደ ጦር ሜዳዎች እንዲሄዱ ሰብከውላቸዋል። ዝነኛ የነበሩት ሟቹ የፕሮቴስታንት ቄስ ሀሪ ኢመርሰን ፎስዲክ ቀደም ሲል ለጦርነት የሚደረገውን ጥረት ይደግፉ ነበር፤ በኋላ ግን እንደሚከተለው በማለት ጥፋታቸውን አምነዋል:- *
“ሌላው ቀርቶ በቤተ ክርስቲያኖቻችን ላይ የጦርነት ባንዲራ አውለብልበናል . . . በአንደኛው የአፋችን ክፍል የሰላሙን መስፍን እያሞገስን በሌላው በኩል ጦርነትን አወድሰናል።” ካህናቱና ሌሎች የሕዝበ ክርስትና ቄሶች በሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ላይ ለተዋጊ ኃይሎች ጸሎት አቅርበዋል፤ እንዲሁም ለጦር ሠራዊቱ፣ ለባሕር ኃይሉና ለአየር ኃይሉ ቡራኬ የሚሰጡ ቄሶች ሆነው አገልግለዋል።5. (ሀ) ሕዝበ ክርስትና የትኞቹ የያዕቆብ 4:4 ቃላት ወደ ልቧ አልገቡም? (ለ) በእርሷ ላይ የሚመጣው መለኮታዊ ፍርድስ ምን መሆን ይኖርበታል?
5 በእነዚህ ሃይማኖታዊ መሪዎች ስር ያለችው ሕዝበ ክርስትና በያዕቆብ 4:4 ላይ: “አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኗል” የሚሉትን ቃላት ወደ ልቧ አላስገባችም። በዚህ ምክንያት ሕዝበ ክርስትና ከሁሉም በላይ የሆነው አምላክ ጠላት በመሆን እስከዚህ ጊዜ ድረስ ቀጥላለች። መለኮታዊ ጥበቃ እንደሌላት የተረጋገጠ ነው። በዚህ ዐቢይ ምክንያት የተነሣ ኅልውናዋ ስጋት ላይ እንደወደቀ ነው። ፖለቲካዊ ወዳጆቿ የሚታመኑ አይደሉም፤ የፀረ ሃይማኖቱ ማዕበልም እያየለ ሄዷል። አምላክ “የቀባኋቸውን አትዳስሱ (አትንኩ)” ያለው እርሷን በሚመለከት አይደለም።— 1ዜና 16:22
“ሕዝቤ ሆይ፣ . . . ከእርስዋ ዘንድ ውጡ”
6, 7. (ሀ) በራእይ 18:4 ላይ ያስተጋባው ምን አጣዳፊ ጥሪ ነው? እርሱስ የቀረበው ለማን ነው? (ለ) በጥንቷ ባቢሎን ውስጥ ይማቅቁ በነበሩት አይሁዳውያን ላይ የሚሠራ ጥንታዊ፣ ነገር ግን ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጥሪ ቀርቦ የነበረውስ መቼ ነበር?
6 በዚህ የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ላይ ላሉት ቅቡዓንና ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው የሚከተለው መለኮታዊ ጥሪ በአስቸኳይ እያስተጋባ ነው:- “ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ . . . ከእርስዋ ዘንድ ውጡ።” (ራእይ 18:4) አዎን፣ የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ከሆነችው ከታላቂቱ ባቢሎን ውጡ።
7 ይህ ጥሪ በባቢሎን ምድር በስደትና በምርኮ 70 ዓመት እንዲያሳልፉ ይሖዋ ለፈረደባቸው ለአይሁዳውያን ቀሪዎች ቀርበው የነበሩትን የኤርምያስ 50:8 እና 51:6, 45 ቃላት የሚያስተጋባ ነው። እነዚህ ቃላት በ537 ከዘአበ በባቢሎን ይማቅቁ በነበሩት አይሁዶች ላይ መፈጸም የጀመሩት በትንቢት የተነገረለት ታላቁ ቂሮስ የሜዶ ፋርስ ሠራዊቱን ይዞ እየደረቀ ያለውን የኤፍራጥስ ወንዝ አቋርጦ ወደ ባቢሎን ከተማ ጥሶ ከገባ በኋላ ነው።
8. (ሀ) ታላቁ ቂሮስ ኢሳይያስ 45:1–6ን የፈጸመው እንዴት ነበር? (ለ) በታላቁ ቂሮስ የተመሰለው ኢየሱስ በዚህ የነገሮች ትንቢታዊ ምሳሌ መሠረት ማከናወን የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
8 በመጀመሪያው የግዛቱ ዓመት ላይ ታላቁ ቂሮስ በኢሳይያስ 45:1–6 ላይ ያለውን ትንቢት የሚፈጽም ሥራ አከናውኗል። በተመሳሳይም በንጉሥ ቂሮስ የተመሰለው ነገር ግን ከእርሱ እጅግ በጣም የላቀው ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ትንቢታዊ ምሳሌ መሠረት ነገሮችን አከናውኗል። ይህም የሆነው በሰማይ በይሖዋ አምላክ ቀኝ ወዳለው ንጉሣዊ ሥልጣኑ ከገባ በኋላ “የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት” በጥቅምት 1914 ባበቁበት በተቀጠረው ጊዜ ነበር። (ሉቃስ 21:24) ከ1914–1918 በተደረገው በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የመንፈሳዊ እስራኤላውያን ቀሪዎች በታላቂቱ ባቢሎንና በፖለቲካዊ ውሽሞቿ በምርኮ ስር ነበሩ።
9, 10. (ሀ) የማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በሆኑት ስምንት አባሎች ላይ ምን እርምጃ ተወስዶ ነበር? (ለ) የይሖዋን ሕዝቦች ሥራ ለማቆም ከተደረገው እንቅስቃሴ በስተጀርባ ታላቂቱ ባቢሎን እንደነበረች የሚያሳይ ምን ማረጋገጫ አለ?
9 ለምሳሌም ያህል፣ በዚያን ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የታተመው ያለቀለት ምስጢር የተባለው መጽሐፍ ሕዝብን ለዓመፅ የሚያነሣሣ ነው በሚል ሰበብ እንዲታገድ ተደርጎ ነበር። ሁለቱ የመጽሐፉ ደራሲዎች በብሩክሊን ኒውዮርክ በሚገኘው የፌዴራሉ ፍርድ ቤት ቀርበው በአትላንታ ጆርጂያ ይገኝ በነበረው በፌዴራሉ ወኅኒ ቤት ለ20 ዓመት እንዲታሰሩ ያላግባብ ተፈርዶባቸው ነበር። በተመሳሳይም የማተሚያ ማኅበሩ ፕሬዘዳንት፣ ዋና ጸሐፊውና ሦስት ሌሎች የዋናው መሥሪያ ቤት አባላት ተፈርዶባቸው ነበር። ተባባሪ ተርጓሚ የነበረውም የዚህን ግማሽ ያህል በፌዴራሉ ወኅኒ ቤት እንዲታሰር ተፈርዶበት ነበር።
10 ስለዚህ ሐምሌ 4, 1918 እነዚህ ስምንት ውስን የሆኑ ክርስቲያኖች መብታቸውን በመገፈፍ ወደ አትላንታ ጆርጂያ በባቡር እንዲሄዱ ተደረገ። በዚያን ጊዜ በብሩክሊን የመጠበቂያ ግንብ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ይገኙ የነበሩት አባላት በተቻላቸው ሁሉ ሥራውን ያንቀሳቅሱት ነበር። ለዚህ ሁኔታ ተጠያቂው ማን ነበር? ሰባክያን የጦር መሣሪያ አቀባይ ሆኑ የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ሲል መልስ ይሰጠናል:- “ጠቅላላውን ሁኔታ መመርመሩ አብያተ ክርስቲያናትና ቄሶች ከመጀመሪያው ጀምሮ ራስላውያንን (ምስክሮቹን) ለማጥፋት
ከተደረገው እንቅስቃሴ በስተጀርባ ነበሩ ወደሚለው መደምደሚያ ይመራናል። . . . የሃያ ዓመት እስራት እንደተፈረደባቸው የሚገልጸው ዜና ሲደርሳቸው የሃይማኖታዊ ጽሑፍ አዘጋጆች የሆኑት በትንንሾቹም ሆኑ በትልልቆቹ ጽሑፎቻቸው አማካኝነት በሁኔታው መደሰታቸውን ገልጸው ነበር። በትልልቆቹ ሃይማኖቶች ጋዜጦች ላይ ምንም የኀዘኔታ ቃላት ለማግኘት አልቻልኩም ነበር።”— ሬይ ኤች አብራምስ፣ ገጽ 183, 184ወደቀች፤ ነገር ግን አልጠፋችም
11, 12. (ሀ) ታላቂቱ ባቢሎን ምን ለማድረግ አቅዳ ነበር? (ለ) ለመጥፋት አያድርሳት እንጂ ምን ታላቅ ውድቀት መጣባት? (ሐ) ነፃ በወጡት የይሖዋ ሕዝቦችስ ላይ ምን ውጤት አስከተለ?
11 ይሁን እንጂ በታላቂቱ ባቢሎን ውስጥ የነበረው ደስታ ለረጅም ጊዜ የሚቀጥል አልነበረም። ታላቂቱ ባቢሎን በ1919 የፀደይ ወራት ታላቅ ውድቀት ደርሶባታል። ከዚያም ሙሉ በሙሉ ከመጥፋቷ በፊት አንዳንድ ሃይማኖታዊ ለውጦች መከሰት ነበረባቸው። ታላቂቱ ባቢሎን የይሖዋን ሕዝቦች ለዘላለም ለመደምሰስና ምርኮኛ ለማድረግ አስባ ነበር። ይሁን እንጂ በመጋቢት 1919 ለመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ስምንት ተወካዮች የእስር ቤቱ በር በግድ እንዲከፈትላቸው በመደረጉ በዋስ ተለቀዋል። ቆየት ብሎም ከተከሰሱባቸው ክሶች ሙሉ በሙሉ ነፃ ተደረጉ።
12 አሁን የታላቂቱ ባቢሎን ደስታ የደረሰበት ጠፋ። ፍርድ ቤቱ ምስክሮቹን ለመልቀቅ ያደረገውን ውሳኔ በሚመለከት ሰባክያን የጦር መሣሪያ አቀባይ ሆኑ የተባለው መጽሐፍ “ቤተ ክርስቲያኖች ፍርዱን የተቀበሉት በዝምታ ነበር” ብሏል። ሆኖም የይሖዋ ሕዝቦች የነበራቸው ደስታ ታላቅ ነበር። ዓለም አቀፉ ድርጅታቸው እንደገና ተጠናከረ። በ1919 በሲዳር ፖይንት ኦሃዮ በተደረገው ትልቅ ስብሰባቸው ላይ የማኅበሩ ፕሬዘዳንት “መንግሥቱን ማወጅ” በሚለው ንግግሩ በቦታው የነበሩትን በሺህ የሚቆጠሩ ተሰብሳቢዎች ስሜት
ለሥራ አነሳስቶት ነበር። የይሖዋ ምስክሮች በድፍረት የአምላክን መንግሥት ለሕዝብ ለማወጅ እንደገና ነፃ ሆኑ! ታላቂቱ ባቢሎን ግን ውድቀት ደረሰባት። እርግጥ ውድቀቱ ለመጥፋት አላደረሳትም። ታላቁ ቂሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሷን ድል አድርጎ ታማኝ ተከታዮቹን ነፃ አወጣቸው።13. የመንግሥታት ቃል ከዳን ማኅበር በመድረኩ ላይ ብቅ ሲል ታላቂቱ ባቢሎን ምን አደረገች?
13 በዚህ መንገድ ታላቂቱ ባቢሎን ከጦርነቱ በኋላ ወዳለው ዘመን እንድትዘልቅ ተፈቅዶላታል። የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር እንደ የዓለም ሰላም ጠባቂ አካል ተደርጎ እንዲቋቋም ሲታሰብ በአሜሪካ ይገኝ የነበረው የፌዴራሉ የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት:- “በምድር ላይ የአምላክ መንግሥት ፖለቲካዊ መግለጫ ነው” ብሎ በይፋ በማወጅ ድጋፉን ሰጥቶአል። በመጨረሻውም የታሰበው ማኅበር ሲቋቋም ታላቂቱ ባቢሎን በዚህ ምሳሌያዊ “ቀይ አውሬ” ጀርባ ላይ በመውጣት መጋለብ ጀመረች።— ራእይ 17:3
14. (ሀ) በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ታላቂቱ ባቢሎን የወሰደችው ርምጃ ምን ነበር? (ለ) ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሰው ሠራሹ የሰላም ጠባቂ ወኪል ከጥልቁ ሲወጣ ታላቂቱ ባቢሎን ምን አደረገች?
14 ይህ ውጤት አልባ ሰላም አስጠባቂ ወኪል ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተቀሰቀሰበት ጊዜ ወደ በድንነት ጥልቅ ውስጥ ሲገባ ታላቂቱ ባቢሎን የምትጋልበው አጣች። (ራእይ 17:8) ሆኖም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ ከገቡት 57 መንግሥታት ጋር አብራ ተሳትፋ ነበር። እርሷም በብዙ መቶ በሚቆጠሩና በተዘበራረቁ ሃይማኖታዊ ክፍሎችና ቡድኖች መከፋፈሏ በፍጹም ረብሿት እንደማያውቅ ሁሉ ታማኝነቷንም በተለያዩት ተዋጊ ወገኖች መካከል ማከፋፈሏ ብዙም ቅር አላሰኛትም። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ላይ ሰው ሠራሽ የሆነው ሰላም አስጠባቂ ወኪል የተባበሩት መንግሥታት በሚል ቅርጽ ከበድንነት ጥልቅ ውስጥ ሲወጣ ታላቂቱ ባቢሎን ወዲያውኑ ጀርባው ላይ ዘላ ወጣችና እርሱንም ወደ ፈለገችው አቅጣጫ ማዞር ጀመረች።
ፖለቲካዊ ኃይሎች በባቢሎን ላይ ሊዞሩባት ነው
15, 16. (ሀ) በአሁኑ ጊዜ የሰው ዘር ከፊት ለፊቱ ምን ተደቅኖበታል? (ለ) ከራእይ 17:15–18 ጋር በመስማማት ሁሉን የሚችለው አምላክ ምን ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ አድርጓል?
15 በአሁኑ ጊዜ አጠቃላዩ የሰው ዘር ዓለም አንድን አስፈሪ የሆነ እንግዳ ነገር ሊመለከት ነው። ይህም ታላቂቱ ባቢሎንን ከኅልውና ውጭ አድርጐ የመደምሰስ ዓላማ በመያዝ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ እርሷ መዞራቸው ነው። ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ ናቸው ብለው በቅንነት ለሚያምኑት ሰዎች ሁኔታው በጣም አስደንጋጭ ሊመስል ይችል ይሆናል። ይሁን እንጂ የአጽናፈ ዓለሙ የበላይ ገዥ የሆነው ይሖዋ አምላክ የፍጥረትን ግዛት በቂ ለሆነ ረጅም ጊዜ ስላቆሸሸች በመላው አጽናፈ ዓለም ውስጥ ታላቂቱ ባቢሎን ቦታ እንዳይኖራት ወስኗል። እርሷም ኃይለኛ ርምጃ ተወስዶባት መደምሰስ አለባት።
16 የእርሷን ጥፋት እንዲያስፈጽሙ አምላክ ሊፈቅድላቸው የሚችል ዝግጁ የሆኑ ኃያላን ወኪሎች ማለትም የዓለም የፖለቲካ ኃይሎች አሉ። በአምላክ መንፈስ አነሳሽነትና መሪነት የተጻፈው የራእይ መጽሐፍ ይሖዋ ወዳጆቿን በእርሷ ላይ እንደሚያስነሣባትና እነርሱም ራቁቷን እንደሚያስቀሯት፣ እንዲሁም በእርግጥ ማን መሆኗን ማለትም አጋንንት የሰፈሩባት አጭበርባሪ እንደሆነች እንደሚያጋልጧት ይተነብያል! እነርሱም በምሳሌያዊ አባባል በእሳት ያቃጥሏታል፣ የአመድም ክምር ያደርጓታል። እርሷም በማይወላውሉት የእውነተኛው አምላክ አምላኪዎች ላይ ያደረሰችውን ግፍ ይፈጽሙባታል።— ራእይ 17:15–18፤ 18:24
17. የፖለቲካ ኃይሎች የሚያገኙአቸው ፀረ ባቢሎን ድሎች ይሖዋ አምላክን ወደ ማምለክ ይመልሳቸዋልን? እንዴትስ እናውቃለን?
17 የፖለቲካ ኃይሎች ይህንን ኃይለኛ የሆነ ፀረ ሃይማኖት ርምጃ መውሰዳቸው ራእይ 17:12–14) ይሖዋ አምላክ በፈቀደላቸው ከፍተኛ የሆኑ ፀረ ሃይማኖታዊ ድሎች በጣም ይደሰቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ምን ጊዜም የይሖዋ ባላጋራ በሆነው “የዚህ የነገሮች ሥርዓት አምላክ” ይኸውም በሰይጣን ዲያብሎስ መታለላቸውን ይቀጥላሉ።— 2 ቆሮንቶስ 4:4 አዓት
ከዚያ በኋላ ይሖዋ አምላክን ለማምለክ ይመለሳሉ ማለት አይደለም። ቁጣ የተሞላ ፀረ ባቢሎን ርምጃ ስለ ወሰዱ አሁን የአምላክ ወዳጆች ሆኑ ማለትም አይደለም። እንደዚያ ባይሆን ኖሮ የራእይ መጽሐፍ ከዚያ ቀጥለው እንደሚወስዱት የሚያሳየውን ርምጃ አይወስዱም ነበር። (18, 19. (ሀ) ‘በሰላሙ መስፍን’ አማካይነት የይሖዋን አጽናፈ ዓለማዊ የበላይ ገዥነት መረጋገጥ ለማየት በሕይወት የማትቆየው ማን ናት? (ለ) ሆኖም ይሖዋ በታላቂቱ ባቢሎን ላይ ላገኘው ድል ዘላለማዊ ምስክሮቹ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
18 ታላቂቱ ባቢሎን ሁሉን በሚችለውና ከሁሉም በላይ በሆነው በይሖዋ አምላክ ቀኝ ባለውና አሁን “ኃያል አምላክ” በሆነው “የሰላም መስፍን” በኩል የሚመጣውን ታላቅ መደምደሚያ ይኸውም የይሖዋ አጽናፈ ዓለማዊ የበላይ ገዥነት ሲረጋገጥ ለማየት እስከ መጨረሻው የጥፋት ደረጃ ድረስ አትቆይም።— ኢሳይያስ 9:6
19 የይሖዋ ምስክሮች በሌላው ወገን፣ ማለትም በማይደፈረው መለኮታዊ ጥበቃ ስር ተጠልለው ይቆማሉ። (ኢሳይያስ 43:10, 12) ጻድቃን ከሆኑት ሰማያት በሚመጣው ትእዛዝ መሠረት በታዛዥነት ከታላቂቱ ባቢሎን ወጥተው ይገኛሉ። (ራእይ 18:4) ጽድቃዊ ደስታቸው በዓይናቸው በሚያዩት ነገር ወሰን የለሽ ይሆናል። ከዚያም በኋላ እነርሱ ለዘላለም የይሖዋ ምስክሮች ይሆናሉ፣ ታላቂቱ ባቢሎንን በማጥፋት ማንነቱን ማረጋገጡን በሚመለከት ለዘላለም ለመመስከር ይችላሉ።— ራእይ 19:1–3
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
^ አን.3 ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት በመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትንንሽ ጽሑፎች ማኅበር የታተመውን “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች!” የአምላክ መንግሥት ትገዛለች! የሚለውን መጽሐፍ ገጽ 468–500 ተመልከት።
^ አን.4 ለአንደኛው የዓለም ጦርነት ቄሶች ስለሰጡት ድጋፍ ሰባክያን የጦር መሣሪያ አቀባይ ሆኑ በተባለው በሬይ ኤች አብራምስ (በኒውዮርክ በ1933) በተዘጋጀው መጽሐፍ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል። መጽሐፉ እንዲህ ሲል ይገልጻል:- “ቄሶች ለጦርነቱ ስሜት የሞላበት መንፈሳዊ ቦታና የሚገፋፋ ኃይል ሰጥተውታል። . . . ጦርነቱ ራሱ የአምላክን መንግሥት በምድር ላይ ለማስፋፋት የሚያገለግል ቅዱስ ጦርነት ነው ተብሎ ተሰበከ። አንድ ሰው ሕይወቱን ለአገሩ መስጠቱ ሕይወቱን ለአምላክና ለመንግሥቱ እንደመስጠት ያህል ተቆጥሮ ነበር። አምላክና አገር ተመሳሳይ ተደርገው ይታዩ ነበር። . . . በዚህ ረገድ ጀርመኖችና ተባባሪዎቻቸው ተመሳሳይ ነበሩ። እያንዳንዱ ወገን አምላክን የራሱ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ያምን ነበር። . . . አብዛኞቹ መንፈሳዊ መምህራን በጣም የተጧጧፈ ውጊያ በሚደረግበት ቦታም እንኳ ቢሆን ኢየሱስ ወታደሮቹን ወደ ድል በመምራት ግምባር ቀደም ተዋጊ እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ ምንም አልተቸገሩም። . . . በዚህ መንገድ ቤተ ክርስቲያን የጦርነቱ ሂደት መሠረታዊ ክፍል ሆናለች። . . . (የቤተ ክርስቲያን) መሪዎች ራሳቸውን ለጦርነቱ አመቺ አድርገው ለማዘጋጀት ምንም ጊዜ አላጠፉም። ጦርነቱ በታወጀ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በአሜሪካ የሚገኘው የፌዴራሉ የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት የተሟላ ትብብር ለማድረግ ልዩ ልዩ ዕቅዶች ነደፈ። . . . አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ከተጠየቁት በጣም አልፈው ሄዱ። ለተመዝጋቢዎቹ ወታደሮች የምልመላ ጣቢያዎች ሆኑ።” — ገጽ 53, 57, 59, 63, 74, 80, 82
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]