በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“እጅግ ብዙ ሰዎች” ወደ አምላክ ድርጅት የሚወስደውን “ጐዳና” ያዙ

“እጅግ ብዙ ሰዎች” ወደ አምላክ ድርጅት የሚወስደውን “ጐዳና” ያዙ

ምዕራፍ 16

“እጅግ ብዙ ሰዎች” ወደ አምላክ ድርጅት የሚወስደውን “ጐዳና” ያዙ

1, 2. ኢሳይያስ ምዕራፍ 35 መንፈሳዊ ተፈጻሚነት ያገኘው መቼ ነው? የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮችስ ምን መግለጫ ይሰጣሉ?

‘በሰላሙ መስፍን’ የሺህ ዓመት ግዛት ውስጥ ታላቂቱ ባቢሎን ከመጥፋትዋ በፊት አሁን ተፈጻሚነት በማግኘት ላይ የሚገኙት ብዙዎቹ የኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ገጽታዎች በሰው ልጆች ላይ ቃል በቃል ይንፀባረቃሉ። በመንፈሳዊ መንገድ ሲከናወን የሚቆየው ነገር ያለጥርጥር በሥጋዊ መንገድም ይፈጸማል። የአምላክ አገልጋዮች ከታላቂቱ ባቢሎን ምርኮ በመመለሳቸው የዚህ ትንቢት ዋነኛ መንፈሳዊ ተፈጻሚነት አሁን እየታየ ነው። ነቢዩ ኢሳይያስ ይህንን በሚከተለው አስደሳች አገላለጽ ያብራራዋል:-

2 “ምድረበዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፣ በረሀውም ሐሴት ያደርጋል እንደ ጽጌረዳም ያብባል። እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፣ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ [የይሖዋንም (አዓት)] ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።”— ኢሳይያስ 35:1, 2

3. ወደ ስድስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ስንመለስ ባዶ የነበረው ምድር የት ነበር? እንዴትስ ሐሴትን ሊያደርግ ይችል ነበር?

3 ምድረበዳውና ደረቁ ምድር በረሀውም የሚገኙት የት ነበር? በስድስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ በይሁዳ መንግሥት ግዛት ውስጥ ይገኙ ነበር። ከ537 ከዘአበ ያ ምድር ለ70 ዓመታት ባድማ ሆኖና ያለ ነዋሪዎች ቆይቶ ነበር። ይሁን እንጂ ምድረበዳ ሐሴት ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው? የቀድሞ ነዋሪዎቹ ወደ እርሱ መመለሳቸው አስፈላጊ ነበር። ከነበረበት ዝቅተኛ ሁኔታ ከፍ ሊደረግና አስደሳች መልክ ያላቸው የሊባኖስ ረጅም ተራሮች ክብር ሊሰጠው ታስቦ ነበር።

ምሳሌያዊ የዔድን ገነትን ማስገኘት

4, 5. (ሀ) በዘመናችን ተትቶ የነበረ አንድ ምድር ተመሳሳይ ለውጥ ያደረገው መቼ ነበር? ለምንስ? (ለ) የቅቡዓን ቀሪዎች መልሶ የመገንባት እንቅስቃሴዎች ያስገኙት ምንን ነበር? (ሐ) ኢሳይያስ 35:5–7 የታደሰውን መንፈሳዊ ሁኔታቸውን የገለጸው እንዴት ነው?

4 በመንፈሳዊ ሁኔታ ምድሪቱ በአምላክ እንደተተወች ከሚያሳየው መልኳ የይሖዋን ሞገስ እንደገና ማግኘቷን ወደሚያረጋግጥ ሁኔታ የመለወጡ ዘመናዊ ተመሳሳይነት በ1919 መፈጸም ጀምሯል። ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው የተመለሱት የይሖዋ ሕዝቦች በዚያን ጊዜ በተከፈተው የሰላም ወቅት ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ቆርጠው ነበር። ታላቁ ቂሮስ ኢየሱስ ክርስቶስና አባቱ ይሖዋ አምላክ ነፃ የወጡትን የመንፈሳዊ እስራኤላውያን ቀሪዎች ከ537 ከዘአበ በኋላ ወደ ምድራቸው የተመለሱት የጥንት እስራኤል ቀሪዎች የይሖዋን ቤተ መቅደስ ከመገንባታቸው ጋር ተመሳሳይ የሆነውን አስደናቂ ሥራ ሰጣቸው። ከ1919 በኋላ የተከናወኑ መልሶ የመገንባት እንቅስቃሴዎች ምሳሌያዊ የዔድን ገነትን አስገኝተዋል።

5 ይህም በሚከተሉት የኢሳይያስ 35 ቃላት ውስጥ ተተንብዮአል:- “በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል። በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፣ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረበዳ ውኃ፣ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና። ደረቂቱ ምድር ኩሬ፣ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆ ደንገልም ይሆንበታል።”— ኢሳይያስ 35:5–7

6. ዘመናዊቷ የኤዶም አምሳያ መኖሯ ምንን አላገደውም? በዛሬው ጊዜ እንደገና ከተደራጁት ቀሪዎች ጋር በደስታ የሚጮኹት እነማን ናቸው?

6 የዘመናዊቷ የኤዶም አምሳያ መኖር መንፈሳዊ እስራኤላውያን በኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ፍጻሜ መሠረት ወደ ገነታዊ ሁኔታ መመለሳቸውን አላገደውም። ስለዚህ ዘመናዊ ኤዶማውያን የተመለሱት የመንፈሳዊ እስራኤላውያን ቀሪዎችና ቁጥራቸው እየጨመረ ያለው “እጅግ ብዙ ሰዎች” እንዳደረጉት የሚደሰቱበት ምንም ምክንያት የላቸውም። “እጅግ ብዙ ሰዎች” የተባሉት የይሖዋን ዘመናዊ ምስክሮች መንፈሳዊ ገነት በመጠበቅ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው።

7. የቀሪዎቹ የማስተዋል ዓይኖች ከ1914 በፊት በፍጹም ያላዩት ነገር ምን ነበር? ይሁን እንጂ ‘ዕውር’ ዓይኖቻቸው ተከፈቱላቸውን?

7 ከአሕዛብ ዘመን ፍጻሜ በፊት የመንፈሳዊ እስራኤላውያን የመረዳት ዓይኖች በ1914 የሚፈነዳው የዓለም ችግር አብቅቶ ከእነርሱ መካከል ቀሪዎቹ ገና በሕይወት እንደሚቆዩ ለማየት በፍጹም አልተከፈቱም ነበር። ከዚህም ሌላ እነርሱና የ“ሌሎች በጐች” ክፍል የሆኑ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ስለ አምላክ መሲሐዊ መንግሥት መቋቋም ዓለም አቀፍ ምስክርነት የመስጠት መብት በማግኘት እንደሚባረኩ አልተረዱም ነበር። ስለዚህ በመንፈሳዊ ዕውር የነበሩት የቀሪዎቹ ዓይኖች በ1919 እንዲከፈቱ ተደረጉ፤ እነዚህ የተከፈቱ ዓይኖች ከፊታቸው ያለውን ጊዜ ሲመለከቱ እንዴት ያለ ግሩም ተስፋ ታያቸው!

8. በሴዳር ፖይንት ኦሀዮ የተደረጉት ሁለት ትልልቅ ስብሰባዎች እንደገና በተደራጁት ቀሪዎች መንፈሳዊ ጆሮዎችና ምላሶች ላይ ምን ውጤት ነበራቸው?

8 በ1919 እና በ1922 በሴዳር ፖይንት ኦሀዮ ባደረጓቸው ስብሰባዎቻቸው ላይ በፊታቸው ስለተዘረጋው ሥራ ተነገራቸው። በፊታቸው ላለው ሥራ ተዘጋጁ። መንፈሳዊ ጆሮቻቸውም የሚነሽጠውን የአምላክን መንግሥት መልእክት ለመስማትና እርሱን የማወጁን አስፈላጊነት ለመረዳት ተከፍተው ነበር። ለረጅም ጊዜ ሲጸልዩለት ለነበረው መንግሥት እንደ ምስክሮች ሆነው ለማገልገል በተገቢ መንገድ ልክ እንደሚዳቋ ዘልለው ነበር። እስከዚህን ጊዜ ድረስ ዲዳ የነበረው ምላሳቸውም በሰማይ ላይ ሥልጣን ስለያዘው ስለ ሰማያዊው መሲሐዊ መንግሥት በደስታ መጮኽ ጀመረ።— ራእይ 14:1–6

9. በመንፈሳዊ ሁኔታ ውኃ በምድረበዳ የፈለቀው እንዴት ነበር?

9 አዎን፣ ሁኔታው አስቀድሞ ደረቅና ጠፍ በነበረ መንፈሳዊ መሬት ላይ ውኃ እንደፈለቀ ያህል ሆኖ ነበር፤ ስለዚህ አሁን ሁሉም ነገር በጣም ስለ ለመለመ ፍሬ ለመስጠት የተዘጋጀ ለምለም ሜዳ መስሎ ነበር። ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው የተመለሱት የይሖዋ ሕዝብ በጋለ ሁኔታ ተደስተውና ወደ ከፍታዎች በኃይል እንደሚወጣ ሚዳቋ ጥንካሬ ተሰምቷቸው ነበር! በእርግጥም በ1914 በክርስቶስ መመራት ስለጀመረችው ስለተቋቋመችው የአምላክ መንግሥት የሚገልጹት የእውነት ውኃዎች ከፍተኛ እርካታን በማምጣት እየጨመረ በሚመጣ ኃይል ጐርፈዋል።— ኢሳይያስ 44:1–4

የቅድስና “ጐዳና”

10, 11. (ሀ) ይህ አርኪ የሆነ ለውጥ ምንን ያመለክታል? (ለ) ቀሪዎቹ ወደ መንፈሳዊው ገነታቸው የደረሱት በየትኛው መንገድ ነው? ይህንንስ ኢሳይያስ 35:8, 9 የሚገልጸው እንዴት ነው?

10 ከዚህ በላይ ያለው የሚያመለክተው ምንድን ነው? ይህንን ነው:- በመጀመሪያ ቅቡዓኑ በኋላም የ“ሌሎች በጐች” ክፍል የሆኑት “እጅግ ብዙ ሰዎች” ከታላቂቱ ባቢሎን ወጥተው የአምላክ መንግሥት ምስክሮች ሆነዋል። ሆኖም ወደ መለኮታዊው ሞገስ የሚመለሱትና ወደዚህ መንፈሳዊ ገነት የሚያመሩት በየትኛው መንገድ ነበር? የአቅኚነት መንፈስ የነበራቸውን ብዙ እስራኤላውያን አምላክ ወደ ሰጣቸው የትውልድ አገራቸው አብረው በአንድነት እንዲጓዙ ለማስቻል አንድ ሰፊ የሆነ ትልቅ መንገድ እንደተከፈተላቸው ያህል ሆኖ ነበር። አነቃቂ የሆነው የኢሳይያስ ትንቢት ይህንን ያመለክታል:-

11 “በዚያም ጐዳናና መንገድ ይሆናል እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐንም ያልሆኑ አያልፉበትም፣ ለንጹሐን ግን ይሆናል፤ ተላላፊዎችና ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም። አንበሳም አይኖርበትም፣ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም።”— ኢሳይያስ 35:8, 9

12. የአንደኛው የዓለም ጦርነት መፈጸም ወዲያውኑ ለቀሪዎቹ ‘ጐዳናውን’ ከፈተላቸውን? 1919 በገባ በአራተኛው ቀን ላይ ምን ሆነ?

12 የአንደኛው የዓለም ጦርነት መፈጸሙ ወዲያውኑ ዘመናዊውን “ጐዳና” አላስከፈተም። ስምንቱ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ገና በእስር ላይ ነበሩ፤ የምስክርነቱም ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ ቀዝቅዞ ነበር። ጥር 4, 1919 በፒትስበርግ ፔንስልቬንያ በተደረገው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጄ ኤፍ ራዘርፎርድ ታስሮ የቆየ ቢሆንም እንኳ ንጹሕ የሆነ የልዑል አምላክ አገልጋይ ስለመሆኑ እርግጠኛ በመሆን በዚያው ሥልጣን እንዲቀጥል ተመረጠ።

13, 14. ለቀሪዎቹ ምሳሌያዊ “ጐዳና” እንደ ተከፈተ የሚያመለክቱ በ1919 የሆኑት ነገሮች ምንድን ናቸው? በዚያስ ጐዳና ላይ የተጓዙት እነማን ናቸው?

13 መጋቢት 25, 1919 እርሱና ሰባት እስረኛ ጓደኞቹ ተለቀቁ፤ ቆይቶም ሙሉ በሙሉ ከክስ ነፃ ተደረጉ። የመስከረም 15, 1919 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 283 ላይ የማኅበሩ ቢሮዎች ከጥቅምት 1, 1919 ጀምሮ እንደገና ከፒትስበርግ በ124 ኮሎምቢያ ሃይትስ ወደሚገኘው የብሩክሊን ቤቴል እንደሚዛወሩ የሚገልጽ የሚያበረታታ ዜና ይዞ ነበር። ከዚያም በታህሣሥ 15, 1919 የመጠበቂያ ግንብ እትም ላይ ይህ በወር ሁለት ጊዜ የሚታተም ጽሑፍ እንደገና በብሩክሊን ኒውዮርክ እንደሚታተም ተገለጸ።

14 ስለዚህ ለደስተኞቹ የአምላክ አገልጋዮች ምሳሌያዊው ጐዳና የተከፈተው በ1919 ነበር። በይሖዋ ዓይን ቅዱስ ለመሆን የሚፈልጉት በዚያ “ጐዳና” ማለትም “በቅድስና መንገድ” ላይ የተጓዙት ነበሩ። ትክክለኛ ዓላማ፣ ንጹሕ የሆነ የልብ ግፊት የሌለው ማንም ሰው በዚያ ምሳሌያዊ “የቅድስና መንገድ” አልሄደም፤ ስለዚህም መለኮታዊውን ሞገስ ማግኘት ወደሚችልበት ሁኔታ አልደረሰም።

15. “እጅግ ብዙ ሰዎች” በምሳሌያዊው ጐዳና ውስጥ ለመግባታቸው የሚታይ ማስረጃ የሚሆነው ምንድን ነው?

15 ሰኔ 1, 1935 በዋሽንግተን ዲ ሲ በተደረገ በአንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ከተባሉት ውስጥ 840 የሚሆኑት ‘በጐዳናው’ ውስጥ መግባት ለመጀመራቸው የሚታይ ማስረጃ ለማቅረብ በውኃ ተጠምቀዋል። አሁንም ቁጥራቸው እየጨመረ ያለ በሚልዮን የሚቆጠሩ የእነርሱ አባላት ቁጥራቸው እየቀነሰ ከሚሄደው ከቅቡዓን ቀሪዎች ጋር በመተባበር ላይ ናቸው። በአሁኑ ጊዜም በሰላምና አስደሳች በሆነ ጓደኝነት ‘በጐዳናው’ ላይ ይጓዛሉ። በሰማይ በሚገኘው ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ እርዳታ ያላቸውን አንድነት ምንም ነገር እንዳይበጥስባቸውም ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል።

16. በምሳሌያዊ አባባል በዚህ ጐዳና ላይ አንበሳ ወይም ሌላ ነጣቂ አውሬ የሌለው እንዴት ነው?

16 በምሳሌያዊ አባባል አንበሳ ወይም ሌላ ነጣቂ አውሬ በዚህ ጐዳና ላይ አይገኝም። ይህም ሲባል ቅቡዓን ቀሪዎችና ‘እጅግ ብዙ ሰዎችን’ የሚያግድ ወይም የሚያስፈራራ ምንም ነገር አይኖርም ማለት ነው። መድረሻቸውን ጽዮን በማድረግ ነፃ አውጪያቸው ታላቁ ቂሮስ አሁን በከፈተላቸው መንገድ ላይ በትምክህት ጉዞ ጀመሩ።

17. (ሀ) ወደዚህ “የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ” ጠልቀን ብንገባም እንኳ ጐዳናው አሁንም ክፍት ነውን? (ለ) ወደ “ቅድስና መንገድ” እየገቡ ያሉት እነማን ናቸው? ይህንን ያደረጉትስ እንዴት ነው?

17 ዛሬ ወደዚህ ‘የነገሮች ሥርዓት መደመደሚያ’ ውስጥ በጣም ጠልቀን በገባንበት ወቅት ላይም ቢሆን ያ “ጐዳና” ክፍት እንደሆነ ነው። ታላቁ ቂሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ሳቢያ ባቢሎን ወደቀች የሚለው መልእክት ሲደርሳቸው አድናቂ የሆኑ ብዙ ሕዝቦች እርምጃ ወስደዋል። ከእርስዋም በመሸሽ ወደ መንፈሳዊው የገነት መንገድ፣ “የቅድስና መንገድ” ገብተዋል።— ኤርምያስ 50:8

18. የኢሳይያስ 35 የመጨረሻ ጥቅስ አሁን ያለውን የይሖዋ ታማኝ ምስክሮች ሁኔታ የሚገልጸው እንዴት ነው? ለዚህ ትንቢት መፈጸምስ ምስጋና የሚገባው ማን ነው?

18 የኢሳይያስ ምዕራፍ 35 መዝጊያ ጥቅስ እንደሚገልጸውም በቃላት ሊገለጽ የማይችል ደስታ እያገኙ ነው:- “[ይሖዋም (አዓት)] የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፣ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።” ከይሖዋ አምላክ ጋር በሚስማማ መንገድ ባለመሄዳቸው ይሰማቸው የነበረው ኀዘንና ትካዜ ከ1919 ጀምሮ ሸሽቷል። ኀዘንና ትካዜ ወደ ይሖዋ ታማኝና ደስተኛ ምስክሮች እንደገና አልተመለሱም። ደማቁን የኢሳይያስ ምዕራፍ 35⁠ን ትንቢት ምስጋና በሚገባው መንገድ ለፈጸመው እውነትን ለሚናገረው አምላክ ለይሖዋ ምስጋና ይድረሰው!

[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]