በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዛሬ ላለው ለሚታየው የአምላክ ድርጅት ታማኝ መሆን

ዛሬ ላለው ለሚታየው የአምላክ ድርጅት ታማኝ መሆን

ምዕራፍ 18

ዛሬ ላለው ለሚታየው የአምላክ ድርጅት ታማኝ መሆን

1, 2. በመዝሙር 50:5 ላይ የሚገኘውን ጥቅስ ልንረዳው የሚገባን እንዴት ነው?

በመዝሙር 16:10 ላይ “ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፣ [ታማኝህንም (አዓት)] መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም” ተብሎ ተጽፎአል። በመዝሙር 50:5 ላይም “በመሥዋዕት የተደረገውን ቃል ኪዳኔን ያቆሙትን ታማኞቼን ወደ እኔ ሰብስቡ” (አዓት) ተብሎ ተጽፎአል። እነዚህ የይሖዋን ቃል ኪዳን ያቆሙት “መሥዋዕት” የሚሆኑት ናቸውን? አይደሉም። እነዚህ ታማኞች ከአምላክ ጋር ስምምነት ለማድረግ እንዲችሉ ሥጋዊ አካላቸውን በመስጠት ራሳቸውን “መሥዋዕት” አያደርጉም።

2 ታዲያ ቃል ኪዳኑ የቆመው እንዴት ነው? ነፍሱ በሲኦል ባልተተወችው፣ ነገር ግን ከሙታን በተነሣው “ታማኝ” በሆነው “መሥዋዕት” አማካኝነት ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ የመዝሙር 16:10 ቃላት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንደሚሠሩ በማሳየት እንዲህ አለ:- “[ዳዊት] ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፣ [እርሱ በሲኦል እንዳልተተወ (አዓት)] ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሳው።”— ሥራ 2:25, 27, 31, 32

3. በመዝሙር 50:5 ላይ በሚገኘው ትእዛዝ መሠረት የተሰበሰቡት እነማን ናቸው? ለአምላክ ታማኝ ሆነው ለመገኘት ከልብ መገፋፋት ያለባቸውስ ለምንድን ነው?

3 ይህ ከሞት የተነሳው ኢየሱስ የአዲሱ ቃል ኪዳን መካከለኛ ነው፣ አዲሱ ቃል ኪዳን የጸደቀውም በእርሱ መስዋዕት መሠረት ነው። (ዕብራውያን 9:15, 17) ታዲያ በመዝሙር 50:5 ላይ በሚገኘው ትዕዛዝ መሠረት የሚሰበሰቡት እነማን ናቸው? በእርሱ መስዋዕት አማካኝነት በተደረገው አዲስ ቃል ኪዳን ውስጥ ያሉት የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ናቸው። ይሖዋ ላዘጋጀላቸው ለዚህ ተወዳዳሪ ለማይገኝለት መሥዋዕት ካላቸው ምስጋና የተነሣ ለእርሱ ታማኝ ሆነው ለመገኘት ከውስጥ መገፋፋት ይኖርባቸዋል።

4, 5. (ሀ) ሰይጣን ዲያብሎስ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የይሖዋን የሚታይ ድርጅት ለማጥፋት ባደረጋቸው ሙከራዎች ምን ለማድረግ ተሳክቶለታል? (ለ) የማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት የተዛወረው ወዴት ነበር? ለምንስ? (ሐ)በዘመናችን ከመዝሙር 137:1 ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ታማኝ የሆኑት ቀሪዎች የአምላክን ድርጅት የመሰናከል ሁኔታ ሲመለከቱ ስሜታዊ ሁኔታቸው ወይም አመለካከታቸው ምን ነበር?

4 የይሖዋ መንግሥት በ1914 በሰማይ ስትቋቋም ብሔራት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ በመግባት ያችን መንግሥት በመቃወም በኃይል ተቆጡ፤ አምላክም ይህንን ፈቅዶታል። (መዝሙር 2:1, 2) ሰይጣን ዲያብሎስ የሚታየውን የይሖዋ ድርጅት ክፍል ለማጥፋት ያንን የዓለም ጦርነት ሊጠቀምበት ሙከራ አድርጎ ነበር። የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና የትንንሽ ጽሑፎች ማኅበር ፕሬዝዳንትን በአትላንታ ጆርጂያ በሚገኘው የፌደራሉ ወህኒ ቤት ለማሳሰር ተሳክቶለት ነበር። ከእርሱም ጋር ሌሎች ሰባት የማኅበሩ ተወካዮች ታስረው ነበር።

5 በስደት ምክንያት በብሩክሊን ኒው ዮርክ የሚገኘው የማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በፒትስበርግ ፔንስልቫኒያ ወደሚገኝ የኪራይ ሕንፃ ተዛውሮ ነበር። ይህ የተደረገው የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት መታተም እንዲቀጥል ለማድረግ ነበር። ታማኞቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰማያዊ ክብር እንደሚጎናጸፉ ይጠበቅ ነበር። ይሁን እንጂ እነዚያ የቀሪዎቹ ክፍል የይሖዋ ድርጅት እንደዚያ ተጨቍኖና ሥራው ተሰናክሎ ሲመለከቱ ወደ ማልቀስ አዘንብለው ነበር።— መዝሙር 137:1

በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ ያሳዩት ታማኝነት

6–8. የማኅበሩ ፕሬዘዳንት ጄ. ኤፍ. ራዘርፎሮድ ታስሮ በነበረበት ወቅት ለይሖዋ ድርጅት ታማኝ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

6 በዚህ የእስር ጊዜ ውስጥ ለይሖዋ ድርጅት ያለውን ታማኝነት በማሳየት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ፕሬዝዳንት ጄ.ኤፍ ራዘርፎርድ ታህሣሥ 25, 1918 ታማኝ የይሖዋ አገልጋይ ለነበረው ለጄ.ኤ.ቦሕኔት አንድ ልዩ ደብዳቤ ጽፎ ነበር። የተጻፈውም በእርሱ ስም ሆኖ በፒትስበርግ ይገኝ ወደነበረው የማኅበሩ ቢሮ ነበር። ራዘርፎርድ እንደሚከተለው ሲል ጽፎ ነበር:-

7 “ከባቢሎን ጋር ለመስማማትና አቋሜን ለማላላት እምቢ በማለቴና ጌታዬን በታማኝነት ለማገልገል በመሞከሬ በእስር ቤት ውስጥ እገኛለሁ፤ ለዚህም አመስጋኝ ነኝ። . . . አቋሜን አላልቼ ከአውሬው ጋር ከመስማማት ወይም ተሸንፎ ነፃ ከመሆንና የመላውን ዓለም ውዳሴ ከማግኘት ይልቅ የእርሱን ሞገስና ፈገግታ በማግኘት በእስር ቤት መሆንን እመርጣለሁ። ለጌታ የታማኝነት አገልግሎት ሲባል መሰቃየቱ የተባረከና ጣፋጭ የሆነ ተሞክሮ ነው። በመንግሥቱ ውስጥ ከሁሉም ነገሮች በላይ የአባታችንን ፈገግታ ከሁሉም ነገር እናስበልጣለን። ይህም በሁሉም የአምላክ ልጅ አእምሮ ውስጥ የመጨረሻው ከፍተኛ ነገር መሆን ይገባዋል። በዚያ አንድ የሚያደርገንን ሕብረት በጉጉት እንጠብቃለን። ሁላችሁንም እንደገና ለማየት ብናፍቅም ደስተኛ ነኝ። የወረዳ ስብሰባውና የማኅበሩ ዓመታዊ ስብሰባ እየቀረቡ ነው። የክርስቶስ መንፈስ በስብሰባዎቹ ላይ የሚገኙትን ልብ ሁሉ ይሙላ . . .

8 “ገና ብዙ የሚሠራ ሥራ አለ። በዚህ ሥራ መሳተፍ ትልቅ ክብር ነው። እርሱን ከማንም አስበልጠው በከፍተኛ ደረጃ የሚወዱት ብቻ ናቸው ታማኝ ሊባሉ የሚችሉት። ይህ የክብር ሥራ የሚሰጠውም ለእነርሱ ነው። . . . ከዚህ አስደሳች ቀን በፊት በከፍተኛ ጥረት ምስክርነት መሰጠት ይኖርበታል። . . . ያለፉት ዘዴዎችና መንገዶች ብቃቶቹን አያሟሉም፣ ሆኖም ጌታ በራሱ የበጎነት መንገድ የሚያስፈልገውን ያዘጋጃል። . . . ይህ የእስር ቤት ተሞክሮ ከወንድም ራስል ይልቅ ለእኛ ተጠብቆ በመቆየቱ ደስተኛ ነኝ። ለዓመፃ ያለኝ ጥላቻ፣ ለጽድቅ ያለኝ ፍቅርና ሌሎችን ለመርዳት ያለኝ ፍላጐት የአሁኑን ያህል ሆኖ አያውቅም። . . . የጽዮን ድል ቀርቦአል።”

‘ለደስታቸው ዋና ምክንያት’ የአምላክ ድርጅት ነበረች

9. ታስረው የነበሩት የማኅበሩ ተወካዮች የትኛውን የመዝሙራዊ ዝንባሌ አንፀባርቀው ነበር?

9 የይሖዋ አገልጋዮች በዓለም ውስጥ ታማኝ እንዳልሆኑ፣ እንደ ከዳተኞችና የአገር ፍቅር እንደሌላቸው ተደርገው ቢቆጠሩም የይሖዋን ድርጅት አልተዉም። በዚያ ተጽዕኖ ስር አቋማቸውን አላልተው ለመስማማት እምቢ ብለዋል። የአምላክን ድርጅት ከመርሳትና ይህን ድርጅት ከእንግዲህ ‘ለደስታቸው ዋናው ምክንያት’ ማድረጋቸውን ከመተው ይልቅ ቀኝ እጃቸው ቢከዳቸውና ዲዳ ቢሆኑ ይመርጣሉ።— መዝሙር 137:5, 6 አዓት

10, 11. (ሀ) ታማኝ ቀሪዎች ስለ ምን ነገር ጸልየዋል? ኤዶምን በሚመለከትስ የትኞቹን የመዝሙራዊው ቃላት ለመናገር ተገፋፍተው ነበር? (ለ) የሚታየው የይሖዋ ድርጅት ጠላቶች ምን ለማድረግ ችለው ነበር? እነዚህ ጠላቶች ምንን ፈጽሞ አልጠበቁም ነበር?

10 የይሖዋ ጠላቶች በአጽናፈ ዓለማዊ ድርጅቱ ምድራዊ ተወካዮች ላይ በተወሰደው እርምጃ ክፋት የተቀላቀለበት ደስታ ተሰምቷቸው ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ውርደት በድርጅቱ ላይ በመድረሱ የይሖዋ አገልጋዮች የእርሱ የበቀል ቀን እንዲመጣ ይጸልዩ ነበር። መዝሙራዊው የጥንትዋን ኤዶም በመጥቀስ የተናገራቸውን ቃላት አስታውሰው ነበር:- “አቤቱ [ይሖዋ (አዓት)] በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ:- እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉትን።” (መዝሙር 137:7፤ ገላትያ 4:26) ይሖዋ ሚስት መሰል ድርጅቱን በጣም ስለሚወዳት የዲያብሎስ ድርጅት ክፍል የሆኑት በምድራዊ ድርጅቱ ውስጥ ባሉት ታማኞች ላይ የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን አይረሳም።

11 የሁኔታው ውጪያዊ መልክ እነዚህ የታላቂቱ ባቢሎን ፖለቲካዊ ደጋፊዎች የምትታየውን የይሖዋን ድርጅት ‘እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርስዋት ነበር።’ ከአፈር ተነስታ ዛሬ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሆና እንደሚያዩዋት በፍጹም አልጠበቁም ነበር።

የተበቃዩ ደስታ

12. (ሀ) በጥንትዋ ባቢሎን ውስጥ ምርኮኛ የነበሩትን የይሖዋን ሕዝቦች ነፃ የሚያወጣው ማን ሆኖ ተገኘ? መዝሙር 137:8, 9 ሙሉ በሙሉ የሚያመለክተው እርሱን ነውን? (ለ) እነዚህ ጥቅሶች ስለ አምላክ ምድራዊ ድርጅት ተበቃይ ምን ትንቢት ተናግረዋል?

12 ይሖዋ ከጥንትዋ የዓለም ኃያል ከባቢሎን ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት የፋርሱን መሪ ቂሮስን ተጠቀመበት። ይሁን እንጂ ሙሉ ትርጉሙ ከተወሰደ የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት የሆነችውን ታላቂቱ ባቢሎንን በሚመለከቱት በመዝሙር 137 የመዝጊያ ቃላት ውስጥ የተጠቀሰው ቂሮስ አይደለም:- “አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ ስለተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ (ደስተኛ) ነው። ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ (ደስተኛ) ነው።”— መዝሙር 137:8, 9

13, 14. በመዝሙር 137:8, 9 ላይ የተጠቀሰው “ደስተኛ” ታላቂቱ ባቢሎንን የሚያጠፉትን የፖለቲካ ኃይሎች ሊያመለክት የማይችለው ለምንድን ነው?

13 ይህ “ደስተኛ” የተባለው ማን ይሆን? “ደስተኛ” የተባሉት አሮጊቷ ጋለሞታዊ የሃይማኖት ሥርዓት ለረጅም ጊዜ ተመችቷት ስትጋልበው በቆየችው “አውሬ” ራስ ላይ የሚገኙት ምሳሌያዊ “አሥር ቀንዶች” ናቸውን? አይደሉም፤ ምክንያቱም የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ፖለቲካዊ አጥፊዎች እርስዋን የሚያጠፉአት ለእውነተኛው አምላክ ንጹህ አምልኮ መንገድ ለመጥረግ አይደለም። እንዲሁም ይህንን የሚያደርጉት ለመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ክብር ብለው አይደለም። ታዲያ እነዚህ በመዝሙራዊው የተገለጸውን “ደስተኛ” ለመሆን የሚችሉት እንዴት ነው?

14 የዚህ ዓለም የፖለቲካ ኃይሎች ይህንን ፀረ ሃይማኖት ሥራ የሚፈጽሙት ለይሖዋ አምላኪዎች ካላቸው ፍቅር የተነሳ አይደለም። ለምን እንደዚያ እንላለን? ምክንያቱም ጨርሶ አምላክ የለሽ የሆነ ዓለም ለማምጣት ባላቸው ውጥን ላይ የይሖዋ ምስክሮች ደንቃራ ሆነው ይቆሙባቸዋል። ስለዚህ የፖለቲካው ኃይሎች የምሥክሮቹን አምላክ ዓላማ ለመፈጸም መሣሪያ ብቻ ሆነው ያገለግላሉ።— ራእይ 17:17

15. የፖለቲካ ኃይሎችን ማን ያነሣሣቸዋል? በማንስ አማካኝነት?

15 እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች የዓለምን የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ለማጥፋት በቀጥታ ሊያገለግሉ ቢችሉም የሚያንቀሳቅሳቸው ይሖዋ አምላክ ነው። እንዴት? ሥልጣንን በተቀበለው በንጉሣዊ ልጁ በታላቁ ቂሮስ በኢየሱስ ክርስቶስ ይጠቀማል። በዚህም ምክንያት በመዝሙራዊው የተተነበየለት “ደስተኛ” በመንግሥታዊ ሥልጣኑ ላይ የሚገኘው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!

16. ይሖዋ የባቢሎንን “ልጆች” የሚያጠፋው እንዴት ነው?

16 ይሖዋ በአንድ በኩል ታማኞቹን እየጠበቀ የሐሰት ትምህርት የሚያስፋፋውን የጋለሞታ መሰሉን ሃይማኖታዊ ድርጅት “ልጆች” ይዞ እንደ “ዓለት” በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በሚመራው በማይበገረው የይሖዋ መንግሥት ላይ ይፈጠፍጣቸዋል።

17. (ሀ) በኢሳይያስ 61:1, 2 መሠረት ኢየሱስ በአምላክ መንፈስ ከተቀባ በኋላ ምን ማወጅ ነበረበት? (ለ) ዛሬስ እወጃው የሚከናወነው እንዴት ነው?

17 ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ደጋፊው በሆነው አምላክ መንፈስ የተቀባው “የይሖዋን የበጎ ፈቃድ ዓመት ለማወጅ” ብቻ ሳይሆን “የአምላካችንን የበቀል ቀን” ጭምር ለማወጅ ነበር። (ኢሳይያስ 61:1, 2 አዓትሉቃስ 4:16–21) ይሖዋ በዘመናችን ማለትም በዚህ የነገሮች ሥርዓት “የመጨረሻ ቀኖች” ውስጥ ታማኝ አገልጋዮቹ ለአሕዛብ ሁሉ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን በመላው ምድር ላይ “የአምላካችንን የበቀል ቀን” እንዲያውጁ በማድረግ ላይ ነው። በዚህም አዋጅ ነጋሪነት ላይ በራእይ 7:9–17 አስቀድሞ እንደተተነበየው ከቀሪዎቹ ጋር ቁጥራቸው እያደገ የሚሄደው “እጅግ ብዙ ሰዎች” የሆኑ የኢየሱስ ክርስቶስ በግ መሰል ደቀመዛሙርት ተባብረዋል።

18. የአምላክ ታማኞች በምን ደስታ ይካፈላሉ?

18 እነዚህ በሙሉ ማለትም ቀሪዎቹና “እጅግ ብዙ ሰዎች” በራእይ 18:4 ላይ ያለውን መላዕክታዊ ትእዛዝ ፈጽመዋል። ከታላቂቱ ባቢሎን ወጥተዋል። ይህ እርምጃ አስቸኳይ የሆነው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ከአርማጌዶን በፊት ሃይማኖታዊ “ልጆችዋ” ከመፈጥፈጣቸውና ‘በአውሬው’ እና ‘በአሥር ቀንዶቹ’ አማካኝነት ከመጥፋታቸው በፊት ከታላቂቱ ባቢሎን መሸሽ ስላለባቸው ነው። እነዚህ ታማኞች ከታላቁ ቂሮስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ደስታ ተካፋዮች ይሆናሉ። እንደሚከተለው በማለትም ከሰማያት ጋር ድምፃቸውን ያስተባብራሉ:- “እናንተ ሰዎች ያህን አመስግኑ! ፍርዶቹ እውነተኛና ጻድቅ ስለሆኑ ማዳንና ክብር ኃይልም ለአምላካችን ይገባዋል። በዝሙትዋ ምድርን ባበላሸችው በታላቋ ጋለሞታ ላይ ፍርዱን አስፈጽሞአልና።”— ራእይ 19:1, 2 አዓትከኤርምያስ 51:8–11 ጋር አወዳድር።

19. በአሁኑ ጊዜ ታማኝ ቀሪዎች የሚያገኙት ደስታ ምንድን ነው? ከዚህ የሚበልጥ ምን ታላቅ ደስታ ይጠብቃቸዋል?

19 ከ1919 ወዲህ ይሖዋ ለሕዝቡ “ታላቅ ነገርን” አድርጓል። (መዝሙር 126:1–3) ሕዝቡን ነፃ ለማስለቀቅ ያለውን ኃይሉን በጕልህ በማሳየት “የታመነ አምላክ” መሆኑን ስላረጋገጠላቸው ከጭቆና ነፃ የተደረጉት ቀሪዎች እስከ ዛሬ ድረስ ከልብ ደስ ይላቸዋል። (ዘዳግም 7:9) እነርሱ በጥልቅ ተደስተዋል። ይሁን እንጂ ከዚህ የሚበልጥ ታላቅ ደስታ ይጠብቃቸዋል። ይህም የሚፈጸመው በመግዛት ላይ ያለው ንጉሠ ነገሥት ታላቁ ቂሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም የዲያብሎሳዊ ድርጅት “ልጆች” በሚያደቅቅበት ጊዜ የደስታው ተካፋይ ሲሆኑ ነው።

20. ከቅቡዓን ቀሪዎች ደስታ እነማን ጭምር እየተካፈሉ ነው? ለምንስ?

20 በሚልዮን የሚቆጠሩ የቀድሞ የታላቂቱ ባቢሎን “ምርኮኞች” ኃይለኛው ጥፋትዋ ከመምጣቱ በፊት ከዚህች ከተፈረደባት ሃይማኖታዊ ድርጅት እንዲሸሹ እርዳታ ተደርጎላቸዋል። ከዚህ የተነሣ የ“ሌሎች በጎች” ክፍል የሆኑ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ሊመጡ ችለዋል። ቁጥራቸውም አሁን በመላው ምድር ላይ ከ3, 700, 000 በላይ ሆኖአል። ከዓለም አቀፍዋ የሐሰት ሃይማኖት ጥፋት የሚድኑት ሰዎች ቁጥር አልተወሰነም። ለይሖዋ ድርጅት ታማኝ በመሆናቸው ከቀሪዎቹ ጋር በመተባበር ይሖዋ በሃይማኖታዊቷ ታላቂቱ ባቢሎን ላይ የሚያመጣውን የይሖዋን የበቀል ቀን በማወጅ ከደስታቸው እየተካፈሉ ነው።

21. ስለ ታላቂቱ ባቢሎንና ስለ ምርኮኞቿ ሊኖረን የሚገባው ዝንባሌ ምንድን ነው?

21 እንግዲያው ከዚህች የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ጋር ተስማምቶ ለመኖር አቋማችሁን በምንም ዓይነት አታላሉ። እርስዋ እያሽቆለቆለች በምትሄድበት በአሁኑ ጊዜ ወደ እርሷ በፍጹም አትመለሱ። ታላቁ ቂሮስ አስደሳች ድሉን ከማግኘቱ በፊት ጥፋት ከተፈረደበት ከዚህ ሥርዓት ውስጥ እንዲወጡ የምንችለውን ያህል ብዙ የታላቂቱ ባቢሎን ምርኮኞችን መርዳታችንን እንቀጥል።

[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]