በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በስተ ግራ፦ አንዲት እህት በ1930ዎቹ መገባደጃ የወንድም ራዘርፎርድን የተቀዳ ንግግር ስታስደምጥ፣ አላባማ፣ ዩ ኤስ ኤ፤ በስተ ቀኝ፦ ስዊዘርላንድ

ክፍል 1

የመንግሥቱ እውነት​—መንፈሳዊ ምግብ ማቅረብ

የመንግሥቱ እውነት​—መንፈሳዊ ምግብ ማቅረብ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ አንድ ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ ትርጉሙን ሲረዳ ፊቱ በደስታ ሲፈካ ታያለህ። ከዚያም “መጽሐፍ ቅዱስ ምድር ገነት ሆና በዚያ ለዘላለም መኖር እንደምንችል ይናገራል ማለት ነው?” ብሎ ይጠይቃል። የአገልግሎት ጓደኛህ ፈገግ ብሎ “ያነበብከው ጥቅስ ይህን አያሳይም?” ይለዋል። ተማሪው በአድናቆት ስሜት ተውጦ ራሱን እየነቀነቀ “ከዚህ በፊት ይህን አለማወቄ ይገርማል!” ይላል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ የአምላክ ስም ይሖዋ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰማ ተመሳሳይ ስሜት ተሰምቶት እንደነበር ታስታውሳለህ።

እንዲህ ያለ ተሞክሮ አጋጥሞህ ያውቃል? ብዙዎቹ የአምላክ አገልጋዮች ይህን የመሰለ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች፣ የእውነት እውቀት ምን ያህል ውድ ስጦታ እንደሆነ እንድናስታውስ ያደርጉናል! እስቲ ቆም ብለህ አስብ፦ አንተ ይህን ስጦታ ልታገኝ የቻልከው እንዴት ነው? በዚህ ክፍል ውስጥ ይህን ጉዳይ እንመረምራለን። የአምላክ ሕዝቦች እየደመቀ የሚሄድ መንፈሳዊ ብርሃን ያገኙበት መንገድ የአምላክ መንግሥት እውን መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። የዚህ መንግሥት ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ባለፉት አንድ መቶ ዓመታት የአምላክ ሕዝቦች እውነትን እንዲማሩ አስፈላጊውን ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ምዕራፍ 3

ይሖዋ ዓላማውን ይገልጣል

አምላክ ባወጣው የመጀመሪያ ዓላማ ላይ መንግሥቱ ተካቶ ነበር? ኢየሱስ ከመንግሥቱ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ብርሃን የፈነጠቀው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 4

ይሖዋ ስሙን ከፍ ከፍ አድርጎታል

የአምላክ መንግሥት ከይሖዋ ስም ጋር በተያያዘ ምን አከናውኗል? የአምላክን ስም በመቀደስ ረገድ በግለሰብ ደረጃ ድርሻ ማበርከት የምትችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 5

ንጉሡ ስለ መንግሥቱ የሚገልጽ ብርሃን እንዲፈነጥቅ አደረገ

ስለ አምላክ መንግሥት፣ ስለ ገዥዎቹና ተገዥዎቹ እንዲሁም ታማኝ መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ይበልጥ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ እንድታገኝ እንጋብዝሃለን።