በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 16

ለአምላክ ያለህን ፍቅር አሳይ

ለአምላክ ያለህን ፍቅር አሳይ

ከጓደኛህ ጋር ያለህን ወዳጅነት ጠብቀህ ለማቆየት ከእርሱ ጋር መነጋገር ይኖርብሃል። እርሱ ሲናገር ታዳምጠዋለህ እርሱም አንተ ስትናገር ያዳምጥሃል። በተጨማሪም ስለ ወዳጅህ ጥሩ ነገሮችን ለሌሎች ትናገራለህ። ከአምላክ ጋር ወዳጅ መሆንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል መርምር:-

በጸሎት አማካኝነት ከይሖዋ ጋር ዘወትር ተነጋገር። “በጸሎት ጽ[ና]።”—ሮሜ 12:12

የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን አንብብ። “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”—2 ጢሞቴዎስ 3:16

ስለ አምላክ ሌሎችን አስተምር። “ሂዱና አሕዛብን ሁሉ . . . ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።”—ማቴዎስ 28:19, 20

ከአምላክ ወዳጆች ጋር ተቀራረብ። “ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል።”—ምሳሌ 13:20

በመንግሥት አዳራሽ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ ተገኝ። “ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ . . . እንመካከር።”—ዕብራውያን 10:24, 25

የመንግሥቱን ሥራ ደግፍ። “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ።”—2 ቆሮንቶስ 9:7