በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 15

የአምላክ ወዳጆች መልካም የሆነውን ያደርጋሉ

የአምላክ ወዳጆች መልካም የሆነውን ያደርጋሉ

የምታደንቀውና የምታከብረው ወዳጅ ካለህ እርሱን ለመምሰል ትጥራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ቸር [“ጥሩ፣” NW] ቅንም ነው” በማለት ይናገራል። (መዝሙር 25:8) የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ጥሩና ቅን መሆን አለብን። “እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ [“የምትመስሉ፣” NW] ሁኑ” በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ኤፌሶን 5:1, 2) ይህን ከምናደርግባቸው መንገዶች አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው:-

ሌሎችን እርዳ። “ለሰው ሁሉ . . . መልካም እናድርግ።”—ገላትያ 6:10

ጠንክረህ ሥራ። “የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፣ ነገር ግን በዚያ ፈንታ . . . በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።”—ኤፌሶን 4:28

በአካልም ሆነ በሥነ ምግባር ንጹሕ ሁን። “በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።”—2 ቆሮንቶስ 7:1

የቤተሰብ አባሎችህን በፍቅርና በአክብሮት ያዝ። “እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፣ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ። ልጆች ሆይ፣ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ።”—ኤፌሶን 5:33–6:1

ሌሎችን አፍቅር። “ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለሆነ . . . እርስ በርሳችን እንዋደድ።”—1 ዮሐንስ 4:7

የአገሩን ሕግ አክብር። “ነፍስ ሁሉ [ለመንግሥት] ይገዛ። . . . ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፣ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን።”—ሮሜ 13:1, 7