በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 8

የአምላክ ጠላቶች እነማን ናቸው?

የአምላክ ጠላቶች እነማን ናቸው?

የአምላክ ቀንደኛ ጠላት ሰይጣን ዲያብሎስ ነው። ሰይጣን በይሖዋ ላይ ያመፀ መንፈሳዊ ፍጡር ነው። ሰይጣን ከአምላክ ጋር መዋጋቱንና በሰዎች ላይ ከፍተኛ መከራ ማድረሱን ቀጥሎበታል። ሰይጣን ክፉ ነው። እርሱ ውሸታምና ነፍሰ ገዳይ ነው።—ዮሐንስ 8:44

ሌሎች መንፈሳዊ ፍጡራን ከሰይጣን ጋር አብረው በአምላክ ላይ ዓመፁ። መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ፍጥረታት አጋንንት በማለት ይጠራቸዋል። እንደ ሰይጣን ሁሉ አጋንንትም የሰው ልጆች ጠላት ናቸው። ሰዎችን መጉዳት ደስ ይላቸዋል። (ማቴዎስ 9:32, 33፤ 12:22) ይሖዋ ሰይጣንንና አጋንንቱን ለዘላለም ያጠፋቸዋል። በሰዎች ላይ ችግር መፍጠራቸውን የሚቀጥሉት ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው።—ራእይ 12:12

የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ከፈለግህ ሰይጣን እንድታደርግ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ማድረግ የለብህም። ሰይጣንና አጋንንቱ ይሖዋን አይወዱትም። እነሱ የአምላክ ጠላቶች ናቸው፤ አንተም የአምላክ ጠላት እንድትሆን ይፈልጋሉ። ከሰይጣን ወይም ከይሖዋ ማንን ማስደሰት እንደምትፈልግ መምረጥ ይኖርብሃል። የዘላለም ሕይወት የምትፈልግ ከሆነ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ መምረጥ አለብህ። ሰይጣን ሰዎችን የሚያታልልበት በርካታ ዘዴዎችና መንገዶች አሉት። ብዙ ሰዎች በእርሱ እየተታለሉ ነው።—ራእይ 12:9