በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

ለየት ያሉ ስብሰባዎች

የቤቴል አገልግሎት ቤቴል ገብተው ማገልገል የሚፈልጉ ዕድሜያቸው 35 ዓመትና ከዚያ በታች የሆነ የተጠመቁ አስፋፊዎች ዓርብ ከሰዓት በኋላ ከቤቴል አመልካቾች ጋር በሚደረገው ስብሰባ ላይ መገኘት አለባቸው። ይህ ስብሰባ የሚደረግበት ቦታና ሰዓት በቅድሚያ በማስታወቂያ ይገለጻል።

የመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት አገልግሎታቸውን የማስፋት ፍላጎት ያላቸው ከ23 እስከ 65 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አቅኚዎች፣ ለመንግሥቱ ወንጌላውያን በተዘጋጀው ትምህርት ቤት መካፈል ከሚፈልጉ አመልካቾች ጋር እሁድ ከሰዓት በኋላ በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይህ ስብሰባ የሚደረግበት ቦታና ሰዓት አስቀድሞ በማስታወቂያ ይገለጻል።

ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

አስተናጋጆች አስተናጋጆች የተመደቡት እናንተን ለመርዳት ነው። ስለዚህ መኪና ማቆምን፣ በመተላለፊያዎች ላይ መቆምን፣ ወንበር መያዝንና ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ የሚሰጧችሁን መመሪያ በመከተል እባካችሁ ሙሉ በሙሉ ተባበሯቸው።

ጥምቀት የተለየ ዝግጅት ካልተደረገ በቀር ተጠማቂዎቹ የሚቀመጡት ከመድረኩ ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ ይሆናል። የጥምቀት እጩዎች ቅዳሜ ጠዋት የሚቀርበው የጥምቀት ንግግር ከመጀመሩ በፊት በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ መገኘት አለባቸው። እያንዳንዱ ተጠማቂ ለጥምቀት ተስማሚ የሆነ ልብስና ፎጣ ይዞ መምጣት አለበት።

መዋጮዎች ስብሰባው አስደሳች ብሎም ይበልጥ ወደ ይሖዋ እንድንቀርብ የሚረዳን እንዲሆን ለማድረግ ሲባል ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ በቂ ወንበሮች እንዲሁም የድምፅ መሣሪያዎችና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች እንዲኖሩ ዝግጅት ተደርጓል። በፈቃደኝነት የምታደርጉት መዋጮ እነዚህን ወጪዎች ለመሸፈን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን ሥራ ለመደገፍ አስተዋጽኦ ያበረክታል። የመዋጮ ሣጥን የሚል ምልክት በግልጽ የተጻፈባቸው ሣጥኖች በስብሰባው ቦታ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች ላይ ተቀምጠዋል። የምታደርጉትን መዋጮ ሁሉ ከልብ እናደንቃለን። የበላይ አካሉ የአምላክን መንግሥት ዓላማ ለማራመድ በልግስና ለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናውን ይገልጻል።

የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ ይህ ዝግጅት የተደረገው ድንገት ለሚያጋጥም የጤና ችግር ብቻ እንደሆነ እባካችሁ አስታውሱ።

ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች የሚቀመጡበት ቦታ ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ክፍል መምጣት አለባቸው። ዕቃ ከጠፋባችሁ ወደዚህ ክፍል በመሄድ ንብረታችሁን ጠይቃችሁ መውሰድ ትችላላችሁ። ከወላጆቻቸው የጠፉ ልጆች ወደዚህ ክፍል መወሰድ አለባቸው። ይሁን እንጂ ይህ ክፍል የሕፃናት መዋያ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። እባካችሁ ልጆቻችሁን በቅርብ ተከታተሏቸው እንዲሁም ከአጠገባችሁ እንዳይርቁ ጠብቋቸው።

ወንበር እባካችሁ ለሌሎች አሳቢነት አሳዩ። ወንበር መያዝ የሚቻለው ከእናንተ ጋር በመኪና ለሚመጡ፣ አብረዋችሁ ለሚኖሩ ወይም በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ለምታስጠኗቸው ሰዎች ብቻ መሆኑን አስታውሱ። እባካችሁ በአጠገባችሁ ባሉት ወንበሮች ላይ ዕቃዎቻችሁን አታስቀምጡ።

የፈቃደኛ አገልግሎት ከክልል ስብሰባው ጋር በተያያዘ በሚከናወኑ የተለያዩ ሥራዎች መካፈል ከፈለጋችሁ እባካችሁ ለፈቃደኛ አገልግሎት ክፍል አመልክቱ።

በይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል የተዘጋጀ