በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምሥራቹ ለምትኖርበት ማኅበረሰብ የሚያስገኘው ጠቀሜታ

ምሥራቹ ለምትኖርበት ማኅበረሰብ የሚያስገኘው ጠቀሜታ

ምሥራቹ ለምትኖርበት ማኅበረሰብ የሚያስገኘው ጠቀሜታ

“የክርስትና እምነት መመሪያዎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ አይደሉም። በዚህ ውስብስብ በሆነ ዓለም ውስጥ ጥሩ ውጤት ሊያስገኙ አይችሉም።” በዛሬው ጊዜ እንዲህ ያሉ አስተያየቶችን መስማት እንግዳ ነገር አይደለም። ይሁን እንጂ የሕንድ መሪ የነበሩት ሞሃንዳስ ኬ ጋንዲን እና ሊዮ ቶልስቶይን የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ እንደተናገራቸው ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ከፍተኛ ጥቅም እንዳላቸው ተናግረዋል። እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሚገኙት የሥነ ምግባር ትምህርቶች ከፍ ያለ ግምት የሰጡት ለምንድን ነው?

የኢየሱስ የተራራ ስብከት የሚናገረው መንፈሳዊ ነገሮችን ስለመፈለግ እንዲሁም ገር፣ ሰላም ፈጣሪ፣ መሐሪና ጽድቅ ወዳድ ስለመሆን ነው። ግድያን ብቻ ሳይሆን በሌሎች ላይ ክፉኛ መቆጣትን እንዲሁም ምንዝርን ብቻ ሳይሆን የፍትወት ሐሳብ ማውጠንጠንን ያወግዛል። ቤተሰብ እንዲፈራርስና ልጆች ችግር ላይ እንዲወድቁ የሚያደርገውን ፍቺን እንደ ቀላል ነገር መመልከት ተገቢ እንዳልሆነ ይገልጻል። ‘የሚጠሉንን እንኳን እንድንወድ፣ ችግረኞችን እንድንረዳ፣ በሌሎች ላይ ምሕረት በጎደለው መንገድ ከመፍረድ እንድንቆጠብና ሌሎች ለእኛ እንዲያደርጉልን የምንፈልገውን ነገር እኛም ለእነሱ እንድናደርግ’ ይመክረናል። እነዚህን ምክሮች በሙሉ በሥራ ላይ ማዋል ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛል። እነዚህን ምክሮች ተግባራዊ የሚያደርጉ ሰዎች በበዙ መጠን የምትኖርበት ማኅበረሰብ እየተሻሻለ ይሄዳል!

የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ረገድ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኙት ትምህርት ለትዳር አክብሮት እንዲኖራቸው አድርጓቸዋል። ልጆቻቸውን በትክክለኛ መመሪያዎች ያሠለጥናሉ። ለቤተሰብ ሕይወት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ። አንድነት ያለው ቤተሰብ ለማኅበረሰብ፣ እንዲያም ሲል ለአገር ትልቅ ሀብት ነው። የቤተሰብ ትስስር መላላትና የሥነ ምግባር ልቅነት መስፋፋት ኃያላን ለሆኑ የዓለም መንግሥታት መውደቅ ምክንያት እንደሆነ ብዙ የታሪክ ማስረጃዎች ያሳያሉ። የይሖዋ ምሥክሮች በሚያስተምሩት ትምህርት የተነሳ በክርስትና መመሪያዎች የሚመሩ ግለሰቦችና ቤተሰቦች እየተበራከቱ በሄዱ መጠን በማኅበረሰብህ ውስጥ የሚፈጸመው ዓመፅ፣ የሥነ ምግባር ብልግናና ወንጀል እየቀነሰ ይሄዳል።

ለተለያዩ ማኅበረሰቦችና አገሮች ከባድ ራስ ምታት ከሆኑባቸው ችግሮች አንዱ የዘር ጥላቻ ነው። በአንጻሩ ግን ሐዋርያው ጴጥሮስ “አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና የጽድቅ ሥራ የሚሠራ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው” በማለት ተናግሯል። ጳውሎስም “ሁላችሁም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ኅብረት በመፍጠር አንድ ሰው በመሆናችሁ በአይሁዳዊና በግሪካዊ፣ በባሪያና በነፃ ሰው እንዲሁም በወንድና በሴት መካከል ልዩነት የለም” ሲል ጽፏል። (የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35፤ ገላትያ 3:28) የይሖዋ ምሥክሮች ይህን አምነው ይቀበላሉ። በዋና መሥሪያ ቤታቸው፣ በየቅርንጫፍ ቢሮዎቻቸውም ሆነ በየጉባኤዎቻቸው የተለያየ ዘርና የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች በአንድ ላይ ይኖራሉ እንዲሁም አብረው ይሠራሉ።

በአፍሪካ አንዳንድ ጎሳዎች በመካከላቸው ግጭት ስላለ ምንም ነገር አብረው በሰላም ማከናወን አይችሉም። ይሁን እንጂ በእነዚህ አካባቢዎች በሚደረጉ የይሖዋ ምሥክሮች ትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ከተለያዩ ጎሳዎች የተውጣጡ ሰዎች ፍጹም በሆነ ወዳጅነትና ስምምነት አብረው ይበላሉ፣ አብረው ያድራሉ እንዲሁም በአንድነት አምልኮታቸውን ያካሂዳሉ። የመንግሥት ባለሥልጣናት ይህን ሲመለከቱ በጣም ይደነቃሉ። የኒው ዮርኩ አምስተርዳም ኒውስ በነሐሴ 2, 1958 እትሙ ላይ እውነተኛ ክርስትና ሰዎችን አንድ የማድረግ ኃይል እንዳለው የሚያሳይ ዘገባ አውጥቶ ነበር። ለዚህ ዘገባ መነሻ የሆነው ቀደም ሲል የተጠቀሰው በኒው ዮርክ ሲቲ የተካሄደውና ከሩብ ሚሊዮን የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች የተገኙበት ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ነበር።

“በየቦታው በሁሉም ዓይነት የኑሮ ደረጃ የሚገኙና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ጥቁሮች፣ ነጮችና የሩቅ ምሥራቅ ሰዎች አንድ ላይ ተደባልቀው በነፃነት ሲጫወቱ ይታያል። . . . ከ120 አገሮች የተውጣጡት ለአምልኮ የመጡ የይሖዋ ምሥክሮች አብረው በሰላም በመኖርና አምልኳቸውን በማካሄድ፣ ይህን በቀላሉ እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ለአሜሪካውያን አሳይተዋል። . . . ስብሰባው ሰዎች እንዴት አብረው ሊሠሩና ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚያሳይ ድንቅ ምሳሌ ነበር።”

ብዙ ሰዎች የክርስትና እምነት መመሪያዎች በዚህ ዘመናዊ ዓለም ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ አይደሉም ይሉ ይሆናል። ይሁንና ከዚህ የተሻለ ውጤት ሊያስገኝ የቻለ ወይም የሚችል ምን ሌላ ነገር አለ? በዛሬው ጊዜ እነዚህ የክርስትና እምነት መመሪያዎች ተግባራዊ የሚደረጉ ከሆነ ለምትኖርበት ማኅበረሰብ ጥቅም የሚያስገኙ ከመሆናቸውም በላይ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሁሉም ‘ብሔራት፣ ነገዶችና ሕዝቦች’ የሰው ልጆችን በሚያስተዳድረው የአምላክ መንግሥት ሥር ለሚያገኙት አንድነት መሠረት ይሆናሉ።—ራእይ 7:9, 10

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

የትኛውም ዓይነት ዘርና የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች በአንድነት ይሠራሉ

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

የክርስትና እምነት መመሪያዎች ተግባራዊ ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህ የተሻለ ውጤት ያስገኘ ምን ሌላ ነገር አለ?