በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምን ብለው ያምናሉ?

ምን ብለው ያምናሉ?

ምን ብለው ያምናሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች የሰማያትና የምድር ፈጣሪ እንዲሁም ሁሉን ቻይ አምላክ በሆነው በይሖዋ ያምናሉ። በዙሪያችን ባለው አጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚታዩት በረቀቀ ጥበብ የተሠሩ ድንቅ ፍጥረታት ራሳቸው፣ ሁሉን ነገር ወደ ሕልውና ያመጣ ከፍተኛ የሆነ የማሰብ ችሎታና ኃይል ያለው ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ናቸው። የሰዎች ባሕርይ በሠሯቸው ነገሮች ላይ እንደሚንጸባረቅ ሁሉ የይሖዋ አምላክ ባሕርያትም በሠራቸው ነገሮች ላይ ተንጸባርቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚናገረው “የማይታዩት ባሕርያቱ ይኸውም ዘላለማዊ ኃይሉና አምላክነቱ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል።” በተጨማሪም ያላንዳች ድምፅ ወይም ቃል “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ።”—ሮም 1:20፤ መዝሙር 19:1-4

ሰዎች ምንም ዓላማ ሳይኖራቸው የሸክላ ዕቃ ወይም ቴሌቪዥን ወይም ኮምፒውተር አይሠሩም። ምድርም ሆነች በምድር ላይ ያሉ ዕፅዋትና እንስሳት ሰዎች ከሠሯቸው ነገሮች ይበልጥ በጣም አስደናቂ ናቸው። በትሪሊዮን የሚቆጠሩ ሴሎች ያሉት የሰው አካል አሠራር ልንረዳ ከምንችለው በላይ እጅግ የተወሳሰበ ነው፤ የምናስብበት አንጎላችን ብቻ እንኳ መገመት ከምንችለው በላይ አስደናቂ ነው! ሰዎች ከአምላክ ፍጥረታት ጋር ሲነጻጸሩ ከቁብ ሊቆጠሩ የማይችሉትን ሥራዎች የሚሠሩት በዓላማ ከሆነ ይሖዋ አምላክ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍጥረታቱን የፈጠረበት ዓላማ እንደሚኖረው የተረጋገጠ ነው። ምሳሌ 16:4 “እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለራሱ ዐላማ ሠርቶአል” ይላል።

ይሖዋ ምድርን የፈጠረው በዓላማ እንደሆነ ለመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ጥንዶች ከተናገረው ሐሳብ መረዳት ይቻላል፤ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ . . . የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ግዟቸው” በማለት ተናግሮ ነበር። (ዘፍጥረት 1:28) እነዚህ ባልና ሚስት ባለመታዘዛቸው ምክንያት ለምድርም ሆነ በውስጧ ለሚኖሩ ዕፅዋትና እንስሳት ፍቅራዊ እንክብካቤ በሚያደርጉ ጻድቅ ቤተሰቦች ምድርን ሊሞሉ አልቻሉም። ይሁን እንጂ እነሱ ይህን ማድረግ አለመቻላቸው የይሖዋን ዓላማ አያከሽፈውም። በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ካለፉ በኋላ የተጻፉት መጻሕፍት እንደሚጠቁሙት አምላክ “ምድርን ያበጃት . . . ባዶ እንድትሆን” አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ “የሰው መኖሪያ” እንድትሆን ነው። ምድር የተፈጠረችው እንድትጠፋ ሳይሆን ‘ለዘላለም ጸንታ እንድትኖር ነው።’ (ኢሳይያስ 45:18፤ መክብብ 1:4) ይሖዋ ለምድር ያወጣው ዓላማ መፈጸሙ አይቀርም፤ ምክንያቱም “ዐላማዬ የጸና ነው፤ ደስ የሚያሰኘኝንም ሁሉ አደርጋለሁ” ብሏል።—ኢሳይያስ 46:10

በመሆኑም የይሖዋ ምሥክሮች ምድር ለዘላለም ጸንታ እንደምትኖር ያምናሉ፤ በተጨማሪም ምድራችን ውብ የሰው ልጆች መኖሪያ እንድትሆን ይሖዋ ካለው ዓላማ ጋር የሚስማማ አቋም ያላቸው በሕይወት ያሉም ሆኑ የሞቱ ሰዎች በሙሉ በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ እንዳላቸው ያምናሉ። ሁሉም የሰው ልጆች በአዳምና በሔዋን የተነሳ ፍጽምና የጎደላቸው ሆነው በመወለዳቸው ኃጢአተኞች ናቸው። (ሮም 5:12) መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይናገራል፦ “ኃጢአት የሚከፍለው ደሞዝ ሞት ነው።” “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም።” “ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።” (ሮም 6:23፤ መክብብ 9:5፤ ሕዝቅኤል 18:4, 20) ታዲያ ሙታን ዳግም ሕያው ሆነው ከምድራዊው በረከት ተካፋይ ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው? በክርስቶስ ኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ብቻ ነው፤ ምክንያቱም እሱ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። በእኔ እንደሚያምን በተግባር የሚያሳይ ሁሉ ቢሞት እንኳ እንደገና ሕያው ይሆናል” ብሏል። “በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል።”—ዮሐንስ 5:28, 29፤ 11:25፤ ማቴዎስ 20:28

ይህ የሚፈጸመው እንዴት ነው? ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ ማወጅ የጀመረው ‘የመንግሥት ምሥራች’ ይህ እንዴት እንደሚፈጸም ይገልጻል። (ማቴዎስ 4:17-23) ይሁንና ዛሬ የይሖዋ ምሥክሮች በጣም ልዩ በሆነ መንገድ ምሥራቹን በመስበክ ላይ ናቸው።

[በገጽ 13 ላይ የሚገኝ ሰንጠረዠ]

የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ?

እምነት ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል 2 ጢሞ. 3:16, 17

ከመሆኑም ሌላ እውነት ነው 2 ጴጥ. 1:20, 21፤ ዮሐ. 17:17

መጽሐፍ ቅዱስ ከሰዎች ወግ የበለጠ ማቴ. 15:3፤ ቆላ. 2:8

እምነት የሚጣልበት ነው

የአምላክ ስም ይሖዋ ነው መዝ. 83:18 NW፤ ኢሳ. 26:4 NW፤

ኢሳ. 42:8 NW፤ ዘፀ. 6:3 የ1879 ትርጉም

ክርስቶስ የአምላክ ልጅ ነው፤ ማቴ. 3:17፤ ዮሐ. 8:42፤ 14:28

እንዲሁም ከአምላክ ያንሳል ዮሐ. 20:17፤ 1 ቆሮ. 11:3፤ 15:28

ክርስቶስ የመጀመሪያው የአምላክ ቆላ. 1:15፤ ራእይ 3:14

ፍጥረት ነው

ክርስቶስ የሞተው ቀጥ ባለ እንጨት ላይ ገላ. 3:13፤ ሥራ 5:30

እንጂ በመስቀል ላይ አይደለም

የክርስቶስ ሰብዓዊ ሕይወት ታዛዥ ለሆኑ ማቴ. 20:28፤ 1 ጢሞ. 2:5, 6

የሰው ልጆች ቤዛ ሆኖ ተከፍሏል 1 ጴጥ. 2:24

ክርስቶስ አንድ ጊዜ ያቀረበው መሥዋዕት ሮም 6:10፤ ዕብ. 9:25-28

በቂ ሆኗል

ክርስቶስ ከሞት የተነሳው 1 ጴጥ. 3:18፤ ሮም 6:9

የማይሞት መንፈሳዊ አካል ሆኖ ነው ራእይ 1:17, 18

ክርስቶስ በሥልጣኑ ላይ የሚገኘው ዮሐ. 14:19፤ ማቴ. 24:3

በመንፈሳዊ ሁኔታ ነው 2 ቆሮ. 5:16፤ መዝ. 110:1, 2

የምንኖረው ‘በመጨረሻው ማቴ. 24:3-14፤ 2 ጢሞ. 3:1-5

ዘመን ላይ ነው’ ሉቃስ 17:26-30

በክርስቶስ የሚመራው መንግሥት ኢሳ. 9:6, 7፤ 11:1-5

ምድርን በጽድቅና በሰላም ያስተዳድራል ዳን. 7:13, 14፤ ማቴ. 6:10

ይህ መንግሥት በምድር ላይ መዝ. 72:1-4

ፍጹም ተስማሚ የሆነ ራእይ 7:9, 10, 13-17፤ 21:3, 4

የኑሮ ሁኔታ እንዲኖር ያደርጋል

ምድር ፈጽሞ አትጠፋም መክ. 1:4፤ ኢሳ. 45:18

ወይም ሰው አልባ አትሆንም መዝ. 78:69

አምላክ የአሁኑን ሥርዓት በአርማጌዶን ራእይ 16:14, 16፤ ሶፎ. 3:8

በሚደረገው ጦርነት ያጠፋል ዳን. 2:44፤ ኢሳ. 34:2፤ 55:10, 11

ክፉዎች ለዘላለም ይጠፋሉ ማቴ. 25:41-46፤ 2 ተሰ. 1:6-9

አምላክ ሞገሱን የሚያሳያቸው ሰዎች ዮሐ 3:16፤ 10:27, 28፤ 17:3

የዘላለም ሕይወት ያገኛሉ ማር. 10:29, 30

ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደው ማቴ. 7:13, 14፤ ኤፌ. 4:4, 5

መንገድ አንድ ብቻ ነው

ሰዎች የሚሞቱት ሮም 5:12፤ 6:23

በአዳም ኃጢአት ምክንያት ነው

የሰው ነፍስ ከሞት በኋላ ሕዝ. 18:4፤ መክ. 9:10

ከሕልውና ውጪ ትሆናለች መዝ. 6:5፤ 146:4፤ ዮሐ. 11:11-14

ሲኦል የሰው ልጆች መቃብር ነው ኢዮብ 14:13

ራእይ 20:13, 14 የ1954 ትርጉም

የሞቱ ሰዎች የትንሣኤ ተስፋ አላቸው 1 ቆሮ. 15:20-22

ዮሐ. 5:28, 29፤ 11:25, 26

ከአዳም የወረስነው ሞት ይቀራል 1 ቆሮ. 15:26, 54፤ ራእይ 21:4

ኢሳ. 25:8

ወደ ሰማይ ሄደው ከክርስቶስ ጋር የሚገዙት ሉቃስ 12:32፤ ራእይ 14:1, 3

144,000ዎቹ የታናሹ መንጋ 1 ቆሮ. 15:40-53፤ ራእይ 5:9, 10

አባላት ብቻ ናቸው

እነዚህ 144,000 ሰዎች የአምላክ መንፈሳዊ 1 ጴጥ. 1:23፤ ዮሐ. 3:3

ልጆች ሆነው ዳግም ይወለዳሉ ራእይ 7:3, 4

አምላክ ከመንፈሳዊ እስራኤል ጋር ኤር. 31:31፤ ዕብ. 8:10-13

አዲስ ቃል ኪዳን ገብቷል

የክርስቶስ ጉባኤ የተገነባው ኤፌ. 2:20፤ ኢሳ. 28:16

በራሱ በክርስቶስ ላይ ነው ማቴ. 21:42

ጸሎት መቅረብ ያለበት በክርስቶስ በኩል ዮሐ. 14:6, 13, 14፤ 1 ጢሞ. 2:5

ለይሖዋ ብቻ ነው

ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም ዘፀ. 20:4, 5፤ ዘሌ. 26:1

ተገቢ አይደለም 1 ቆሮ. 10:14፤ መዝ. 115:4-8

ከመናፍስታዊ ድርጊቶች መራቅ ያስፈልጋል ዘዳ. 18:10-12፤ ገላ. 5:19-21

ዘሌ. 19:31

ሰይጣን በዓይን የማይታይ 1 ዮሐ. 5:19፤ 2 ቆሮ. 4:4

የዚህ ዓለም ገዥ ነው ዮሐ. 12:31

አንድ ክርስቲያን ሃይማኖቶችን ለመቀላቀል 2 ቆሮ. 6:14-17፤ 11:13-15

በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ገላ. 5:9፤ ዘዳ. 7:1-5

ተካፋይ መሆን የለበትም

ክርስቲያኖች ከዓለም ያዕ. 4:4፤ 1 ዮሐ. 2:15

የተለዩ መሆን ይገባቸዋል ዮሐ. 15:19፤ 17:16

ከአምላክ ሕግ ጋር የማይጋጩ ማቴ. 22:20, 21

ሰብዓዊ ሕጎችን መታዘዝ ይገባል 1 ጴጥ. 2:12፤ 4:15

በአፍም ሆነ በደም ሥር ዘፍ. 9:3, 4፤ ዘሌ. 17:14

ደምን ወደ ሰውነት ማስገባት ሥራ 15:28, 29

የአምላክን ሕግ መጣስ ነው

የመጽሐፍ ቅዱስን የሥነ ምግባር 1 ቆሮ. 6:9, 10፤ ዕብ. 13:4

ሕግጋት መታዘዝ ይገባል 1 ጢሞ. 3:2፤ ምሳሌ 5:1-23

የሰንበት ሕግ የተሰጠው ዘዳ. 5:15፤ ዘፀ. 31:13

ለእስራኤል ብቻ ሲሆን ሮም 10:4፤ ገላ. 4:9, 10

ከሙሴ ሕግ ጋር ቀርቷል ቆላ. 2:16, 17

በልዩ የማዕረግ ስም የሚጠራ ማቴ. 23:8-12፤ 20:25-27

የቀሳውስት ክፍል መኖሩ ተገቢ አይደለም ኢዮብ 32:21, 22 NW

ሰው የተገኘው በፍጥረት እንጂ ኢሳ. 45:12፤ ዘፍ. 1:27

በዝግመተ ለውጥ አይደለም ማቴ. 19:4

ክርስቶስ አምላክን በማገልገል ረገድ 1 ጴጥ. 2:21፤ ዕብ. 10:7

ልንከተለው የሚገባ ምሳሌ ትቶልናል ዮሐ. 4:34፤ 6:38

ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ ማር. 1:9, 10፤ ዮሐ. 3:23

በመጥለቅ መጠመቅ ራስን ሥራ 19:4, 5

ለአምላክ መወሰንን ያመለክታል

ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ሮም 10:10፤ ዕብ. 13:15

በደስታ ለሕዝብ ይመሠክራሉ ኢሳ. 43:10-12

[በገጽ 12 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ምድር . . . የፈጠራት ይሖዋ ነው . . . የሰው ልጅ ይንከባከባታል . . . ለዘላለም መኖሪያ ትሆናለች