በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አስደሳች ግብዣ ቀርቦልሃል

አስደሳች ግብዣ ቀርቦልሃል

አስደሳች ግብዣ ቀርቦልሃል

በዚህ ብሮሹር አማካኝነት አንዳንድ ሐሳቦች ልናካፍልህ በመቻላችን በጣም ደስ ብሎናል። ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት በመቻልህ እንደተደሰትክ ተስፋ እናደርጋለን። በአቅራቢያህ ወደሚገኘው የመንግሥት አዳራሽ መጥተህ እንድትጎበኘን እንጋብዝሃለን። በዚያ ተገኝተህ ስብሰባዎቻችን እንዴት እንደሚካሄዱ መመልከት ትችላለህ። በክርስቶስ መንግሥት አገዛዝ ሥር ምድር ገነት እንደምትሆን የሚገልጸውን ምሥራች ለሌሎች ለማካፈል የምናደርገውን ጥረት ማስተዋል ትችላለህ።

አምላክ የሚከተለውን ተስፋ ሰጥቶናል፦ “አምላክ በገባው ቃል መሠረት አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እንጠባበቃለን፤ በእነዚህም ውስጥ ጽድቅ ይሰፍናል።” (2 ጴጥሮስ 3:13) ይህ ተስፋ ከተሰጠ ብዙ መቶ ዓመታት አልፈዋል። ፍጻሜውን የሚያገኝበት ጊዜ በጣም እየተቃረበ ነው። በዓለም ላይ የሚታዩት ሁኔታዎች ይህን ያመለክታሉ።

ሐዋርያው ጳውሎስ ‘ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስናይ እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ አንድ ላይ መሰብሰባችንን ቸል አንበል’ ብሏል። (ዕብራውያን 10:24, 25) ከእኛ ጋር በመሰብሰብ ጳውሎስ የሰጠውን ምክር በሥራ ላይ እንድታውል እንጋብዝሃለን።