በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለም አቀፋዊው ድርጅታቸውና የሚያከናውኑት ሥራ

ዓለም አቀፋዊው ድርጅታቸውና የሚያከናውኑት ሥራ

ዓለም አቀፋዊው ድርጅታቸውና የሚያከናውኑት ሥራ

በዓለም ዙሪያ ከ230 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ የሚከናወነውን የምሥክርነት ሥራ ለመምራትና ለማስተባበር የሚያስችሉ የተለያዩ መዋቅሮች አሉ። ዋናውን አመራር የሚሰጠው በብሩክሊን፣ ኒው ዮርክ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ያለው የበላይ አካል ነው። የበላይ አካሉ በየቦታው ከሚገኙ የቅርንጫፍ ቢሮ ተወካዮች ጋር እንዲመካከሩ በየዓመቱ ተወካዮችን ይልካል። በየቅርንጫፍ ቢሮው በእነሱ ሥር በሚገኙ አገሮች የሚከናወነውን ሥራ የሚከታተሉ ከሦስት እስከ ሰባት አባላት ያሏቸው የቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴዎች አሉ። አንዳንድ ቅርንጫፍ ቢሮዎች የኅትመት ሥራ የሚያከናውኑ ሲሆን የተወሰኑት ቅርንጫፍ ቢሮዎች በጣም ትላልቅ የሆኑና ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው የማተሚያ መሣሪያዎች አሏቸው። በእያንዳንዱ ቅርንጫፍ ቢሮ ሥር የሚገኘው አገር ወይም አካባቢ በአውራጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን አውራጃዎቹ ደግሞ በወረዳዎች ተከፋፍለዋል። እያንዳንዱ ወረዳ 20 የሚያክሉ ጉባኤዎችን ያካትታል። አንድ የአውራጃ የበላይ ተመልካች በአውራጃው ውስጥ የሚገኙትን ወረዳዎች በየተራ ይጎበኛል። በእያንዳንዱ ወረዳ በየዓመቱ ሁለት ትላልቅ ስብሰባዎች ይደረጋሉ። በተጨማሪም በየወረዳው የሚያገለግሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች አሉ፤ አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች በእሱ ወረዳ ውስጥ ያሉትን ጉባኤዎች በአብዛኛው በዓመት ሁለት ጊዜ የሚጎበኝ ሲሆን በአንድ ጉባኤ ውስጥ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች ለእነሱ በተመደበው ክልል ውስጥ የሚያከናውኑትን የስብከት ሥራ በማደራጀትና አብሯቸው በመሥራት እገዛ ያደርግላቸዋል።

በአካባቢህ የሚገኘው ጉባኤና የመሰብሰቢያ አዳራሹ አንተ ለምትኖርበት ማኅበረሰብ የምሥራቹን ለመስበክ እንደ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። ለእያንዳንዱ ጉባኤ የተመደበው አካባቢ በትናንሽ ክልሎች ተሸንሽኖ ካርታ ላይ ይሰፍራል። እነዚህ ክልሎች ለእያንዳንዱ የይሖዋ ምሥክር የሚመደቡ ሲሆን ክልሉ የተመደበለት ግለሰብ በየቤቱ የሚኖሩትን ሰዎች አግኝቶ ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል። አንዳንዶቹ ጉባኤዎች ጥቂት አባላት ያሏቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ እስከ 200 የሚደርሱ አባላት ሊኖራቸው ይችላል፤ በሁሉም ጉባኤዎች ውስጥ የተለያዩ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ኃላፊነት የሚሰጣቸው ሽማግሌዎች ይኖራሉ። የምሥራቹን የሚሰብክ እያንዳንዱ ግለሰብ በይሖዋ ምሥክሮች ድርጅት ውስጥ ትልቅ ግምት ይሰጠዋል። በዋናው መሥሪያ ቤትም ሆነ በቅርንጫፍ ቢሮ አሊያም በጉባኤ የሚያገለግል እያንዳንዱ የይሖዋ ምሥክር ሰዎች ወደሚገኙባቸው ቦታዎች በመሄድ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ለሌሎች ይሰብካል።

የዚህ የስብከት ሥራ እንቅስቃሴ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ሪፖርት ከተደረገ በኋላ በየዓመቱ በሚዘጋጀው የዓመት መጽሐፍ ላይ አንድ ላይ ተጠናቅሮ ይወጣል። ይህ ሪፖርት ስለ ይሖዋና በክርስቶስ ኢየሱስ ስለሚተዳደረው የአምላክ መንግሥት ምሥክርነት በመስጠት ረገድ በየዓመቱ ምን እንደተከናወነ በዝርዝር ያሳያል። በቅርቡ ከ18,000,000 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮችና ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች በየዓመቱ በሚከበረው የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ተገኝተዋል። የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ ከ1.6 ቢሊዮን የሚበልጥ ሰዓት ያሳልፋሉ፤ በተጨማሪም በየዓመቱ ወደ 300,000 የሚጠጉ አዳዲስ ሰዎች ይጠመቃሉ። ከዚህም ሌላ የይሖዋ ምሥክሮች በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ጽሑፎችን ለሌሎች ሰዎች ያበረክታሉ።