በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መደምደሚያ

መደምደሚያ

የዚህ ብሮሹር ዓላማ፣ የይሖዋ ምሥክሮችን ሃይማኖታዊ እምነቶች በሙሉ ማስረዳት አይደለም። ከዚህ ይልቅ የይሖዋ ምሥክሮች የሚያምኑባቸውን አንዳንድ መመሪያዎች ማብራራትና የተማሪህ ወላጅ ወይም ወላጆች የይሖዋ ምሥክር ከሆኑ የቤተሰቡ እምነት በተማሪው አመለካከት ላይ የሚያመጣውን ለውጥ በሚገባ እንድትገነዘብ መርዳት ነው።

የይሖዋ ምሥክሮች ለልጆቻቸው መንፈሳዊ እድገት ትልቅ ትኩረት ይሰጣሉ። ይህ ደግሞ ልጆቻቸው በሌሎች መስኮችም እድገት እንዲያደርጉ እንደሚረዳቸው ይተማመናሉ። የሚያምኑባቸው ነገሮችና የሚከተሏቸው መመሪያዎች ሕይወታቸው ትርጉም ያለው እንዲሆን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ከመሆኑም በላይ በዕለት ተዕለት ሕይወት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመቋቋም ይረዷቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ የትምህርት ፍላጎት እንዲኖራቸውና ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ ድርሻ የሚያበረክቱ ዜጎች እንዲሆኑ ያነሳሷቸዋል።

የይሖዋ ምሥክሮች በሕይወት ውስጥ ያሉትን እውነታዎች ተቀብለው ለመኖር ጥረት ስለሚያደርጉ ለትምህርት ከፍተኛ ግምት ይሰጣሉ። ስለዚህ አቅማቸው በፈቀደ መጠን ከአንተ ጋር ተባብረው ለመሥራት ይጥራሉ። ከዚህም ሌላ በቤታቸውም ሆነ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የአምልኮ ቦታዎቻቸው፣ ልጆቻቸው ከአስተማሪዎች ጋር ተባብረው በመሥራት ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማበረታቻ መስጠታቸውን ይቀጥላሉ።