በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልጆች፤ ወጣቶች

ልጆች፤ ወጣቶች

አምላክ ለልጆች ያለው አመለካከት

ይሖዋ ልጆችንና ወጣቶችን ከፍ አድርጎ እንደሚመለከታቸው ያሳየው እንዴት ነው?

ዘዳ 6:6, 7፤ 14:28, 29፤ መዝ 110:3፤ 127:3-5፤ 128:3, 4፤ ያዕ 1:27

በተጨማሪም ኢዮብ 29:12፤ መዝ 27:10፤ ምሳሌ 17:6⁠ን ተመልከት

በተጨማሪም “ቤተሰብ” የሚለውን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 1:27, 28—ይሖዋ ምድር በሰው ልጆች እንድትሞላ ባወጣው የመጀመሪያ ዓላማ ላይ ልጅ መውለድ ቁልፍ ሚና አለው

    • ዘፍ 9:1—ከጥፋት ውኃ በኋላ ምድር ዳግመኛ በሰዎች እንድትሞላ አምላክ የሰጠው ትእዝዝ እንዲፈጸም ልጅ መውለድ ትልቅ ድርሻ አለው

    • ዘፍ 33:5—ታማኙ ያዕቆብ፣ ልጆቹ በአምላክ ቸርነት ያገኛቸው ስጦታዎች እንደሆኑ ተሰምቶታል

    • ማር 10:13-16—ኢየሱስ እንደ አባቱ ልጆችን ይወዳል

ይሖዋ ልጆችን ስለሚበድሉ ወይም መጠቀሚያ ስለሚያደርጉ ሰዎች ምን ይሰማዋል?

ትናንሽ ልጆች የትልቅ ሰውን ኃላፊነት እንዲወጡ መጠበቅ ተገቢ እንዳልሆነ የሚያሳዩት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው?

ዘኁ 1:3፤ 1ቆሮ 13:11

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 33:12-14—ያዕቆብ ልጆቹ አቅም እንደሌላቸውና ከአዋቂ ሰው እኩል መራመድ እንደማይችሉ ተረድቶላቸዋል

ልጆች ላይ ለሚደርሰው መከራ ተጠያቂው አምላክ ነው?

ኢዮብ 34:10፤ ያዕ 1:13፤ 1ዮሐ 5:19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 5:18, 20, 23-25—ኢየሱስ የበሽታ መንስኤ ኃጢአት እንደሆነ ተናግሯል

    • ሮም 5:12—ሐዋርያው ጳውሎስ የኃጢአትና የሞት መንስኤ ምን እንደሆነ አስረድቷል

በልጆችም ሆነ በአዋቂዎች ላይ የሚደርሰው መከራ እንደሚያበቃ ይሖዋ ምን ማረጋገጫ ሰጥቷል?

አንድ ልጅ ጥሩ ምሳሌ የማይሆኑ ወላጆች ስላሳደጉት ወይም በልጅነቱ ስለተበደለ፣ አዋቂ ሲሆን ከሌሎች ያነሰ ይሆናል ወይም የወላጆቹን ስህተት ይደግማል ማለት ነው?

ዘዳ 24:16፤ ሕዝ 18:1-3, 14-18

በተጨማሪም ዘዳ 30:15, 16⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ነገ 18:1-7፤ 2ዜና 28:1-4—የሕዝቅያስ አባት ልጆቹን መሥዋዕት እስከማድረግ የደረሰ ክፉ ሰው ነበር፤ ሕዝቅያስ ግን ታማኝና ግሩም ንጉሥ ሆኗል

    • 2ነገ 21:19-26፤ 22:1, 2—ኢዮስያስ፣ አባቱ አምዖን ክፉ ሰው ቢሆንም በጣም ጥሩ ንጉሥ መሆን ችሏል

    • 1ቆሮ 10:11, 12—ሐዋርያው ጳውሎስ ከሌሎች ስህተት መማርና ተመሳሳይ ስህተት ከመፈጸም መቆጠብ እንደምንችል ተናግሯል

    • ፊልጵ 2:12, 13—ሐዋርያው ጳውሎስ የራሳችንን መዳን መፈጸም በዋነኝነት የእኛ ኃላፊነት እንደሆነ ተናግሯል

ልጆችና ወጣቶች ያሉባቸው ኃላፊነቶች

ይሖዋ ፈሪሃ አምላክ ካላቸው ወላጆቻቸው ጋር ለሚኖሩ ልጆች ምን አመለካከት አለው?

1ቆሮ 7:14

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 19:12, 15—የሎጥ ልጆች የመላእክትን ጥበቃ ማግኘት የቻሉበት አንዱ ምክንያት አባታቸው ጻድቅ መሆኑ ነው

ልጆች አምላክን የሚፈሩ ወላጆች ስላሳደጓቸው ብቻ ያለምንም ጥረት በአምላክ ፊት ጥሩ አቋም እንደሚኖራቸው ሊጠብቁ ይገባል?

ምሳሌ 20:11፤ ሕዝ 18:5, 10-13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘሌ 10:1-3, 8, 9—የሊቀ ካህናቱ አሮን ልጆች በስካር ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ተቀስፈዋል

    • 1ሳሙ 8:1-5—ሳሙኤል ጻድቅ ነቢይ ቢሆንም ልጆቹ ምግባረ ብልሹ ነበሩ

ልጆች የአምላክን ሞገስ ማግኘት ከፈለጉ ምን ማድረግ አለባቸው?

ልጆች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ያለባቸው ለምንድን ነው?

ዘዳ 31:12, 13፤ ዕብ 10:24, 25

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 15:32-38—ከኢየሱስ አድማጮች መካከል ትናንሽ ልጆችም ይገኙበታል

ይሖዋ ልጆች እንዲያገለግሉት እንደሚፈልግ በምን እናውቃለን?

መዝ 8:2፤ 148:12, 13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 17:4, 8-10, 41, 42, 45-51—ወጣቱ ዳዊት፣ አንድን ግዙፍና ጨካኝ ሰው ድል በማድረግ ስሙን እንዲያስከብር ይሖዋ ተጠቅሞበታል

    • 2ነገ 5:1-15—ይሖዋ በአንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጅ በመጠቀም እስራኤላዊ ያልሆነን የሠራዊት አለቃ ስለ እውነተኛው አምላክ እንዲማር ረድቶታል

    • ማቴ 21:15, 16—ኢየሱስ፣ ልጆች መሲሑን ለማወደስ ያደረጉትን ጥረት አድንቋል

ይሖዋ የማያምኑ ወላጆች ላሏቸው ልጆች ምን አመለካከት አለው?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘኁ 16:25, 26, 32, 33—ይሖዋ በነቢዩ ሙሴና በሊቀ ካህናቱ አሮን ላይ ባመፁት ሰዎች ላይ የወሰደው የፍርድ እርምጃ ቤተሰቦቻቸውንም ነክቷል

    • ዘኁ 26:10, 11—ዓመፀኛው ቆሬ በሞት ቢቀጣም ልጆቹ ለአምላክ ታማኝ በመሆናቸው ከጥፋት ተርፈዋል

በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶች ጓደኞቻቸውን በጥበብ መምረጥ ያለባቸው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 13:20፤ 1ቆሮ 15:33

በተጨማሪም 2ጢሞ 3:1-5⁠ን ተመልከት

ክርስቲያን ወጣቶች ምን ዓይነት ጓደኞችን መምረጥ አለባቸው?

2ጢሞ 2:22

በተጨማሪም “ወዳጅነት” የሚለውን ተመልከት