በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሕሊና

ሕሊና

ይሖዋ ለሁሉም ሰዎች ሕሊና እንደሰጣቸው የሚያሳየው ምንድን ነው?

ሮም 2:14, 15

በተጨማሪም 2ቆሮ 4:2⁠ን ተመልከት

አንድ ሰው በመጥፎ ድርጊቱ መግፋቱ በሕሊናው ላይ ምን ውጤት ያመጣል?

1ጢሞ 4:2፤ ቲቶ 1:15

በተጨማሪም ዕብ 10:22⁠ን ተመልከት

ትክክለኛውን ነገር እያደረግን እንዳለ ስለተሰማን ብቻ ትክክል ነን ማለት ነው?

ዮሐ 16:2, 3፤ ሮም 10:2, 3

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 18:1-3፤ 19:1, 2—ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ክፉውን ንጉሥ አክዓብን በማገዝ የሞኝነት ድርጊት በመፈጸሙ ይሖዋ ተግሣጽ ሰጥቶታል

    • ሥራ 22:19, 20፤ 26:9-11—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ የክርስቶስን ተከታዮች ማሳደድና መግደል ትክክል እንደሆነ ያሰበበት ወቅት እንደነበረ ተናግሯል

ሕሊና በተገቢው መንገድ እንዲሠራ ማሠልጠን የሚቻለው እንዴት ነው?

2ጢሞ 3:16, 17፤ ዕብ 5:14

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 24:2-7—ንጉሥ ዳዊት፣ ይሖዋ በቀባው በንጉሥ ሳኦል ላይ አግባብ ያልሆነ ነገር ከማድረግ እንዲቆጠብ ሕሊናው ረድቶታል

ኃጢአተኛ ሰዎች በአምላክ ፊት ንጹሕ ሕሊና ሊኖራቸው የሚችለው እንዴት ነው?

ኤፌ 1:7፤ ዕብ 9:14፤ 1ጴጥ 3:21 1ዮሐ 1:7, 9፤ 2:1, 2

በተጨማሪም ራእይ 1:5⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢሳ 6:1-8—ይሖዋ ለነቢዩ ኢሳይያስ ኃጢአቱ ይቅር እንደሚባል አረጋግጦለታል

    • ራእይ 7:9-14—እጅግ ብዙ ሕዝብ፣ የማንጻት ኃይል ባለው የክርስቶስ መሥዋዕት አማካኝነት በአምላክ ፊት ንጹሕ ተደርገው መታየት ችለዋል

በአምላክ ቃል የሠለጠነ ሕሊና የሚሰጠውን መመሪያ ችላ ማለት የሌለብን ለምንድን ነው?

ሥራ 24:15, 16፤ 1ጢሞ 1:5, 6, 19 1ጴጥ 3:16

በተጨማሪም ሮም 13:5⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 2:25፤ 3:6-13—አዳምና ሔዋን ሕሊናቸውን ባለመስማታቸው፣ ይሖዋን አለመታዘዝ የሚያስከትለውን ኀፍረት ለመቀበል ተገድደዋል

    • ነህ 5:1-13—ገዢው ነህምያ፣ የአምላክን ሕጎች የሚጥሱና ከፍተኛ ወለድ የሚጠይቁ አይሁዳውያን ወገኖቹን ሕሊናቸውን እንዲሰሙ መክሯቸዋል

ሕሊናው በሚገባ ያልሠለጠነ ወንድማችንን እንዳናሰናክል መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ከሕሊናችን ጋር በተያያዘ ግባችን ምን ሊሆን ይገባል?