በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መንግሥታት

መንግሥታት

እውነተኛ ክርስቲያኖች ሙሉ ድጋፋቸውን የሚሰጡትና ታማኝ የሚሆኑት ለየትኛው መንግሥት ነው?

ማቴ 6:9, 10, 33፤ 10:7፤ 24:14

በተጨማሪም ዳን 7:13, 14⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 89:18-29—ስለ መሲሐዊው ንጉሥ በተሰጠው መግለጫ ላይ ይሖዋ ለመሲሑ በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደሚሰጠው ተገልጿል

    • ራእይ 12:7-12—በመጨረሻዎቹ ቀናት መጀመሪያ ላይ መሲሐዊው ንጉሥ መግዛት ይጀምራል፤ ሰይጣንን ከሰማይ ያባርራል

የክርስቶስ ቅቡዓን ተከታዮች ከአምላክ መንግሥት ጋር በተያያዘ ምን ድርሻ ተሰጥቷቸዋል?

ክርስቲያኖች ሰብዓዊ መንግሥታትን ያከብራሉ

መንግሥት ያወጣቸውን ሕጎች የምንታዘዘውና ግብር የምንከፍለው ለምንድን ነው?

ሮም 13:1-7፤ ቲቶ 3:1፤ 1ጴጥ 2:13, 14

በተጨማሪም ሥራ 25:8⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 22:15-22—ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ ‘ግብር መክፈል አለባቸው ወይስ የለባቸውም?’ ለሚለው ጥያቄ በዘዴ መልስ ሰጥቷል

ስደት ቢደርስብንም እንኳ አጸፋ የማንመልሰው ለምንድን ነው?

ዮሐ 18:36፤ 1ጴጥ 2:21-23

በተጨማሪም “ስደት” የሚለውን ተመልከት

ክርስቲያኖች ገለልተኞች ናቸው

ክርስቲያኖች ለመንግሥት ሥልጣን አክብሮት ቢኖራቸውም መንግሥታት የይሖዋን ትእዛዝ የሚያስጥስ ነገር በሚጠይቁበት ወቅት የማይታዘዙት ለምንድን ነው?

ሥራ 4:18-20፤ 5:27-29

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 3:1, 4-18—ሦስት ዕብራውያን ወጣቶች ከአምላክ ሕግ ጋር የሚጋጭን የባቢሎን ሕግ አልታዘዙም

    • ዳን 6:6-10—አረጋዊው ነቢይ ዳንኤል ጸሎት ላይ የተጣለውን የመንግሥት እገዳ አልታዘዘም

ኢየሱስ ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆንን በተመለከተ ለተከታዮቹ ምን ምሳሌ ትቷል?

ጣዖት አምልኮን በሚከለክለው የአምላክ ሕግ ላይ ማሰላሰላችን ገለልተኛ እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው?

ዘፀ 20:4, 5፤ 1ቆሮ 10:14፤ 1ዮሐ 5:21

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 3:1, 4-18—ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ ማርዱክ ለተባለው የሐሰት አምላክ ሳይሆን አይቀርም ምስል አቆመ፤ እንዲሁም ተገዢዎቹ በሙሉ ለምስሉ አምልኮ እንዲያቀርቡ አዘዘ

ክርስቲያኖች በጦርነት እንዲሳተፉ ትእዛዝ ሲሰጣቸው የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች መመሪያ ይሆኗቸዋል?

ኢሳ 2:4፤ ዮሐ 18:36

በተጨማሪም መዝ 11:5⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 26:50-52—ኢየሱስ ተከታዮቹ በዓለም ጦርነት ላይ እጃቸውን እንደማያስገቡ ግልጽ አድርጓል

    • ዮሐ 13:34, 35—አንድ ክርስቲያን እንዲህ ብሎ ራሱን መጠየቅ ይችላል፦ ‘በሌላ አገር ያሉ ሰዎችን ምናልባትም የገዛ መንፈሳዊ ወንድሞቼንና እህቶቼን ለመውጋት መሣሪያ ባነሳና ብገድል ይህን የኢየሱስ ትእዛዝ አክብሬያለሁ ሊባል ይችላል?’

ክርስቲያኖች በመንግሥት ላይ ተቃውሞ ሲነሳ በተቃውሞው የማይሳተፉት ለምንድን ነው?

በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች በመንግሥት ላይ ዓምፃችኋል ወይም ሁከት አስነስታችኋል ተብለው በሐሰት ቢከሰሱ ሊገርመን የማይገባው ለምንድን ነው?

ሉቃስ 23:1, 2፤ ዮሐ 15:18-21

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 16:19-23—ሐዋርያው ጳውሎስና ሲላስ በስብከቱ ሥራ የተነሳ እንግልት ደርሶባቸዋል